Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Abere
Senior Member
Posts: 14742
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

የአማራ ክልል እራሱን ነጻ ካወጣ ከሦት ዓመታት በላይ ሁኗል - የጦር መሳሪያ እያንዳንዱ ቤተሰብ ነፍስ-ወከፍ ታጥቋል (ክፍል ውስጥ እንዳለ ተማሪ እስክርቢቶ በሽበሽ ነው)።

Post by Abere » 01 Oct 2025, 14:34

የአማራ ክልል እራሱን ነጻ ካወጣ ከሦት ዓመታት በላይ ሁኗል - የጦር መሳሪያ እያንዳንዱ ቤተሰብ ነፍስ-ወከፍ ታጥቋል (ክፍል ውስጥ እንዳለ ተማሪ እስክርቢቶ በሽበሽ ነው)። ዐብይ አህመድ ይሁን ወያኔ እርማቸውን ያውጡ። የታጠቀ ህዝብ ማሸነፍ አይቻልም።

መሳሪያ እና አማራ ተገናኝተው ሲዋደዱ ያምርባቸዋል። ጸረ-አማራ ደርግ ይህን አውቆ አማራን ትጥቅ አስፈታ፤ እንደ ልጁ እና እንደ ክንዱ የሚቆጠረውን መሳሪያ ገፈፈ፤ የትግሬ-ወያኔ ሌጣ የተገራ ፈረስ አገኜች እርሷም በተራዋ ተጫዎተችበት። አሁን ቅድመ-ደረግ ወደ ቀድሞው የነገስታቱ ዘመን ተመለሰ - የዐብይ አህመድ ጁላ አጋሥስ እንደ እክርቢቶ ነፍስ ወከፍ አስታጠቀው - አስታጥቄ አሉት እውነት ነው - ገለቶማ ብሏል አማራ። የአማራ ህዝብ ፀረ-ሁከት፤ ሃላፊነት ተሰምቶት እርሱን ማስተዳደር የሚችል ነው። እራሱ ለእርሱ ምስለኔ- እንደራሴ ነው። አሁን የኦነግ ብልጽግና እዘጭ እዘጭ፤ የትግሬ-ወያኔ ወልቃይት ሁመራ፤ ራያ እያሉ ማዛጋት እንደ ባለፉት አስርት አመታት ተቀምጦ ኬክ መቁረስ አይደለም - እያንዳንዱ ቤት አፈሙዝ ወድሮ ይጠብቃችኋል። አማራን በፍቅር እንጅ በጦርነት ከእንግድህ ማሸነፍ ማለት ሰማይን ተቀምጦ በድንጋይ ውርወራ እመታለሁ እንደማለት ነው። ያለቀ የደቀቀ ጉዳይ ነው - አእምሮ ላለው ይህን መረዳት እጅግ ቀላል ነው።