Page 1 of 1
አስደንጋጩ የ አሜሪካ ውጭ ጉዳይ መስሪያቤት ኢትዮዽያ ላይ በኮሪደር ልማት ከለላ ስለመኢፈፀመው መንግስታዊ ዘረፋ ዘገባ
Posted: 30 Sep 2025, 19:19
by Za-Ilmaknun
እንግዲህ ኢትዮዽያ ላይ ኢንቨስት አደርጋለሁ የሚል ሁሉ ከገንዘቡ ጋር በቀላሉ እንደተፋታ እንዲያውቀው በ አሜሪካ መንግስት ደረጃ እያስጠነቀቁ ነው፣፣ እነ ኪስ አዉላቂ ቀማኛ የ ኦህዴድ ዘረ-ፈጅ ሌቦች፣ሃገር ላይ እስካሉ ድረስ፣ ቅጥፈት፣ ማጭበርበር ፣ መታገት እና መገደል እንጂ እድገት ሲናፍቅህ ይውላል፣፣
ኮሪደር እያለ የተብለጨለጨ መብራት እያሳየህ መሬትክን፣ ቤትክን፣ ሃብት ንብረትህን ይነጥቅሃል፣፣ ምንም አይነት የህግ ከለላ የለም፣ ተዘዋውሮ መስራት አይቻልም፣ ውሎ ማደር እና በልቶ መኖር ለጥቂቶች ብቻ የተፈቀደበት ሃገር፣፣
Re: አስደንጋጩ የ አሜሪካ ውጭ ጉዳይ መስሪያቤት ኢትዮዽያ ላይ በኮሪደር ልማት ከለላ ስለመኢፈፀመው መንግስታዊ ዘረፋ ዘገባ
Posted: 30 Sep 2025, 19:24
by Za-Ilmaknun
የኮሪደር ልማት ያስከተለው "መፈናቀል" የባለሀብቶችን "ፍላጎት መገደቡን" የአሜሪካ መንግሥት ሪፖርት አመለከተ
"በአስር ሺህዎች የሚቆጠሩ" ነዋሪዎች እና ንግዶች "በትንሽ ወይም ያለምንም ማስጠንቀቂያ የተባረሩበት" የኮሪደር ልማት ፕሮጀክት፤ የባለሀብቶችን መዋለ ንዋይ የማፍሰስ "ፍላጎት እንደገደበ" የአሜሪካ መንግሥት ሪፖርት ገለጸ።
ግጭቶችን እና የውጭ ምንዛሬ ተመን ልዩነት "እንደገና መስፋትን" የሚጠቅሰው ሪፖርቱ፤ የኢትዮጵያ የኢንቨስትመንት ሁኔታ "ለአሜሪካ እና ሌሎች የውጭ ንግዶች ፈታኝ ነው" በማለት ገምግሟል።
የአሜሪካ መንግሥት ይህንን ግምገማ ያሰፈረው አርብ መስከረም 16/2018 ዓ.ም. ይፋ ባደረገው ዓመታዊ የኢንቨስትመንት ሁኔታ መግለጫ ነው።
የአሜሪካ ኩባንያዎች "በመረጃ ላይ የተመሠረተ ውሳኔ እንዲያሳልፉ" በሚል በአገሪቱ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት የሚዘጋጀው ይህ ሪፖርት፤ ከ170 በላይ የሚሆኑ አገራትን የኢንቨስትመንት አመቺነት ሁኔታ ይዳስሳል።
ኢትዮጵያን የተመለከተው የመስሪያ ቤቱ ሪፖርት በስጋትነት ካነሳቸው ጉዳዮች አንዱ በአዲስ አበባ ተጀምሮ ቢያንስ በ40 የአገሪቱ ከተሞች በመካሄድ ላይ ያለውን የኮሪደር ልማት ፕሮጀክት ነው።
https://www.bbc.com/amharic/articles/ckg6er30d8po