ምነው ፋኑዬ ከዳኸኝ
ደጀኔ ነህ ብዬ ባንተ ስናኝ
ሳስብህ ልቤ ይባባል
አይኔ መንታ መንታ ያነባል
ጁላ ነው ያታለለኝ
ጥቁር ክላሽ ሰርቋል ቢለኝ
አሳሳተኝ አሳሳተኝ
አረ በቁሜ ቀበረኝ
ከደጀኔ ጋር አጣላኝ
አንዴ ፋኖ ተበትኗል
አንዴ ገዳም ከትመዋል
እያለ ሲንገዋለል
ፋኑዬ ድንገት አጠቃኝ
አከርካሪዬን ሰበረኝ
ክንግድህስ ምን ተስፋ አለኝ
መሆኔ ነው የዱባይ መናኝ
የሃጥያቴን ፍሬ ልብላ
ያፈሰስኩት ደም እየፈላ
አደረገኝ ነኹላላ
ነፍስህ አትማር ጁላ
ምርኮኛ የታራክ አተላ