በዚህ አለም ታሪክ የሰዉ ልጆች ሃገር ኣቁመዉ መንግስት መስርተዉ በዛ ሃገር ዉስጥ እንደ ኣንድ ቤተሰብ የመኖር ጥበብን ሳይፈጥሩ በፊት እንደ እንስሳ ሜዳ ላይ ተበታትነዉ ይኖሩ ነበር።
ቤትም የመስራት ጥበብን ሳይጀምሩ በፊት እንደ እንስሳ ሜዳ እና ዱር ዉስጥ ይኖሩ ነበር።
ቤት ሰርቶ እንደ ቤተሰብ መኖርን ሆነ ሃገር መስርተዉ የሃገሩ ዜጎች ሁሉ እንደ ኣንድ የፖለትካ ማህበረሰብ ወይም ወገን መኖር ጥበቦችን የፈጠሩትን ኣለማድነቅ ኣይቻልም።
ኢትዮጵያ ለዚህ የሚደነቁ የጥበብ ምሳሌዎች በዚህ አለም ላይ ቀዳሚ ናት ቢባል ማጋነን ኣይመስለኝም።
ባጢ ወይም ባጥ ብሎ ቤት ማለት፣ ዳሲ ወይም ዳስ ብሎ ሃዉስ ማለት፣ ሔረ ወይም ሔር ብሎ እግዝኣብሔር የሚሉ ቃላትን ታሪኮች ማጥናት ብቻ በቂ የመነሻ ምስክሮች ናቸዉ ብዬ ኣስባለሁ። ከኢትዮጵያ ዉጪ ነምን ዱር ኤጌ ቀበ ቱሬ የሚል አባባል መኖሩን ኣላዉቅም።
ስለዚህም ኢትዮጵያ ጥንታዊ ታሪክ ያላት ሃገር ስለሆነች ሉዓላዊነቷ ተከብሮ እና የዜጎችዋ ሆነ ጎሳዎችዋ እኩልነት ሰፍኖ እና ተከብሮ ትኑር ስንል ቃልቻ ቃሉን ቅኝ ገዝቷል ከሚሉ ካድሬዎች ጋር መነታረክ ዓመታትን ኣስቆጥሮ ነበር።
በዚህ ዘመን ደግሞ የቃልቻ ቃሉን ቅኝ ገዝቷል ካድሬዎች ኢትዮጵያ ጥንታዊ ሃገር የሆነች፣ ከጎንደር ቃልቻ የሐረርጌ ቃልቻ ወይም ቃሉ፣ ከጎጃም ገዳም የቦረና ገዳ፣ ከትግራይ ዋቅሹም የሸዋ ዋቀ፣ ከሰሜን መራዊ የደቡብ ሞሮዋ፣ ከትግርኛ እና አማርኛ ተናጋሪ ኢትዮጵያዊያን ኦሮምኛ ተናጋሪ ኢትዮጵያዊያን ለጥንት ግብጥ ይቀርባሉ የሚሉ ጂኦግራፊን ያላጠኑ ኣዲስ ካድሬዎች የተተኩ ይመስላል።
ጎሰ ማለት እና ጎሳ ማለት በተለያዩ የኢትዮጵያ ቋንቋዎች ኣንድ ትርጉም ያላቸዉ ሲሆን የጎሳ ስም እየፈለጉ ለመከፋፈል መጣር ኢትዮጵያ ዉስጥ የመመከር አቅም ይሁን ጥልቅ ዕዉቀት የምያንሰዉ የኣንድ ግለሰብ የማይድን በሽታ የሆነ ይመስላል።
በጂኦግራፊ ምክንያት የሰሜኑ ኢትዮጵያ ክፍል ክርስትናን ቀድሞ ተቀበለ። በጂኦግራፊ ምክንያት የምስራቁ ኢትዮጵያም ክፍል እስልምናን ቀጥሎ ተቀበለ። በጂኦግራፊ ድጋፍ የደቡቡ ኢትዮጵያ ክፍል ባህሉን ይዞ ሰነበተ።
በዚህ ረጅም ታሪክ ዉስጥ በሃይማኖቶች ምክንያት ስሞች ሲለዋወጡ ኖሩ።
ኢትዮጵያ ይህን ሁሉ ታሪክ እንደ ሃገር ተገንዝባ ሃገራዊ አስተዳደሮችዋን ኣሻሽላ ብታድግ ኣፍርካ ዉስጥ ብቻ ሳይሆን በአላም ደረጃ ጠንካራ ሃገር ትሆናለች እያሉ ደጋግሞ መምከር የእራሱን ጎሳዎችን ለማያዉቅ ወይም ኣዉቆ ሀሰተኛ ጆሮ ዳባ ልበስ ሆኗል።
የጋምቤላ አፍንጫ ስር ከምትገኝ ከተማ አከባቢ ወጥቶ የኢትዮጵያ ፖለትካ ዉስጥ የገባዉ ዮሓንስ ለታ የከተማዋን የጎሳዎች ስብጥር የማያዉቅ ሆኖ ነዉ ከቦረና እና አኙዋ ጎሳዎች ተወልዶ ሁለቱም ጎሳዎች እያሉ ኦሮሞ የሚባል ጎሳ ነኝ ብሎ ለኦሮሞ ጎሳ ከሁሉም በላይ ኣዋቂ እና ተቆርቋሪ ነኝ የሚለዉ?
ለመሆኑ የደምቢ ዶሎን ከተማ ጎብኝቶ የምያዉቅ ከተማዋ የቦረና ከተማ ናት ማለት ይችላል?
መጫ እና ቱለማ ከተቋቋመ በኋላ ከዛ ዉስጥ የወጣ ነዉ የሚባል ኦነግ ዉስጥ ገብቶ ከሁሉም በላይ የኦሮሞ ጎሳ ተቆርቋሪ ነኝ የሚለዉ እንዴት ሆኖ ነዉ ቦረና ገዳችን እና ቃሉዎቻችን ሲል ዮሓንስ ለታ የክርስትና ኣራማጅ የሆነዉ?
ኢትዮጵያ ዉስጥ ክርስትናን ከእሱ ቀድሞ ከተቀበሉት በላይ ክርስትያን፣ ከመጫ እና ቱለማ በላይ ስለ ለኦሮሞ ጎሳ ኣዋቂ እና ተቆርቋሪ ነኝ የሚል በምን ተዓምር ነዉ ገዳችን እና ቃሉዎቻችን ከሚሉት ገለልተኛ የሆነዉ?
ይህ ማለት ይህ ሰዉ ስለ ኢትዮጵያ ታሪክ ጥንታዊነት፣ ስለ ኢትዮጵያ ጎሳዎች ማንነት፣ ስለ ክርስትና ወደ ኢትዮጵያ ዉስጥ አገባብ፣ ስለ ቦረና ጎሳ ገዳ እና ቃሉዎች ባህል እና ታሪክ ከመሠረቶቻቸዉ ጀምሮ የማያዉቅ ማለት ኣይዴለም?
እነዚህን ሁሉ ከመሠረቶቻቸዉ ጀምሮ ኣለማወቁ ኣሳማኝ ከሆነ ይህ ሰዉ የማን ቅጥረኛ የነበረ ነዉ?
ይህን ሁሉ ያስተዋሉ ሰዎች ካሉ ለምንድነዉ ቆም ብለዉ የእራሱን ጎሳዎችን የማያዉቅ ጎሳ ቆጣሪን ወሬ የምናስተጋባዉ ማለት የማይችሉት?