Page 1 of 1

እዮብ ተካልኝ አዲሱ ቢሮው እንደገባ ጠረጴዛው ላይ የIMF የለቅሶ ሪፖርቶች ተደርድረው ሲመለከት ማሞ ለምን እንደሳቀ ይገለፅለታል ..

Posted: 21 Sep 2025, 05:46
by sarcasm
በማሞ የስልጣን ዘመን የብር የመግዛት አቅም ከ100 ፐርሰንት በላይ ተዳክሞ ፣ የውጭ ምንዛሪ ጥሪት ደርቆ ፣ ኢትዮጵያን በእዳ ለIMF አስጨምድዶ ፣ በተወላገደ የገንዘብ ፖሊሲ የዋጋ ግሽበት የኑሮ ውድነት አባብሶ ፣ የሀገሪቱን ኢኮኖሚ አንኮታኩቶ ... በሚራክላዊ ፈገግታ ቦታውን ለእዮብ አስረክቦ ተሸብልሏል።

አዲሱ የብሔራዊ ባንክ ገዢ እዮብ ተካልኝም የአፀፋ ሚራክላዊ ፈገግታውን ያለስስት ለማሞ ችሮ ቦታውን ተረክቧል። ማሞ እንዲህ በደማቅ ፈገግታ ሲታይ የኢትዮጵያን የኢኮኖሚ ፖሊሲ አሻሽሎ እድገቷን ከቻይና ተርታ ያሰለፈ ምጡቅ ሪፎርመር አስመስሎታል 😁

የሆነው ሆኖ እዮብ ተካልኝ አዲሱ ቢሮው እንደገባ ጠረጴዛው ላይ የIMF የለቅሶ ሪፖርቶች ተደርድረው ሲመለከት ማሞ ለምን እንደሳቀ ይገለፅለታል ...

Please wait, video is loading...