BBC Reports: በአሁኑ ወቅት ሕዝቡ ታጣቂዎችን ይፈራል፤ በዋነኛነት ግን ይጠብቀኛል የሚለውን መንግሥትንም ይፈራል"
Posted: 16 Sep 2025, 12:45
ማንነታቸው የማይታወቁ፣ ፊታቸውን የሚሸፈኑ፣ የፖሊስ ወይም የወታደር የደንብ ልብስ የሚለብሱ፣ በመንግሥት ወይም በግል ተሽከርካሪ የሚንቀሳቀሱ ሰዎች የሚፈጽሙት አፈና ግራ መጋባትን በመስከተል ስጋትን ይፈጥራሉ።የታፈኑት ሰዎች የት እና በማን እጅ መሆናቸውን የማያውቁ ቤተሰቦች ለመደበኛዎቹ የፀጥታ ተቋማት ለሚያቀርቡት ጥያቄ የሚሰጣቸው ምላሽ "የምናውቀው ነገር የለም" የሚል መሆኑ ደግሞ ተስፋ መቁረጥ ያነግሳል።እነዚህ ሁሉ ድርጊቶች አዲስ አበባን ጨምሮ በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ውስጥ ሲከሰቱ የመንግሥት አካላት ዝምታን መምረጣቸው ደግሞ ግራ አጋቢ ሆኗል።"ይህ ድርጊት በመንግሥት መዋቅር ውስጥ ሥርዓት አልበኝነት መኖሩን የሚያሳይ ምልክት ነው::
https://www.bbc.com/amharic/articles/cdr6ljkm1z1o
https://www.bbc.com/amharic/articles/cdr6ljkm1z1o