Page 1 of 1

Please find me a literate Ethiopian or Eritrean who can read and interpret these lines

Posted: 15 Sep 2025, 15:05
by Naga Tuma
መጽሓፉን ተሸካሚ ነዉ ዕዉሩ
ምዕራፍ ኣስራ ሁለት፣ ሁለት ነዉ ቁጥሩ
የዳንኤል ትንቢት ነዉ ምስጥሩ
ሬይነሳንስ ከሳሽ እንጂ ተከሳሽ ኣይዴለም ነዉ ነገሩ
እሬቻ ከሳሽ እንጂ ተከሳሽ ኣይዴለም ነዉ ነገሩ
ሳትጋደም ወለደችን ሲቀባጥሩ ስለኣልኖሩ

ጳጉሜ 5፣ 2017 ዓመተ ምህረት

Re: Please find me a literate Ethiopian or Eritrean who can read and interpret these lines

Posted: 15 Sep 2025, 15:09
by Naga Tuma
ሁሉም ነብዮች ነን ቢሉ
ቀዳሚዉ የትኛዉ ነበር ኣይሉ

ቀድሞ ትልቋን ኮከብ የበየነዉ
የጥንቷ ኢትዮጵያ ንጉስ የሆነዉ

ሳይሰነብት ለስደት የተዳረገዉ
የሴት መሠሪነትን ያስከሰሰዉ

በረሃ ዉስጥ ኳትኖ መልዓክ የሆነዉ
የእስራኤሎች ኣምላክ ንጉስ የሆነዉ

ዱረቱ ዱረት ያ ጉረ ዱበርቲ ያስባለዉ
ታዓምሩን በእጆችዋ ቀድሞ ያዋለደዉ

ትልቋን የብርሃን ኮከብ ቀድሞ የበየነዉ
ኮከብ ኣይዋሽምን ቀድሞ ያስተዋለዉ
ለዘላለሙ የማይሻር ህያዉ የሆነ ነዉ

ንስሃ ለሴቷ ምድራዊ መሠሪነት ነዉ
ይቅርታ የዘላለሙ መለኮታዊ ብይን ነዉ
ተዓምሮቹ ከሰዉ ልጅ ቁጥጥር ዉጪ ናቸዉ
ለዘላለሙ በስፍራዉ የሚመለስ ነዉ

መስከረም 3፣ 2018 ዓመተ ምህረት

Re: Please find me a literate Ethiopian or Eritrean who can read and interpret these lines

Posted: 15 Sep 2025, 15:17
by Naga Tuma
የለፋሁለት እና ብዬ ነበር ለማለት ሳይሆን በእኔ አስተሳሰብ ኢትዮጵያ መሠረታዊ እና የማይናወጥ እድገት የምትጀምረዉ ይህን ማስተዋልን ማንበብ እና ማስተማር የሚችሉ ምሁሮችን በብዛት ስታፈራ ነዉ ለማለት ነዉ።