Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Naga Tuma
Member+
Posts: 6997
Joined: 24 Apr 2007, 00:27

ሰዎች መለኮትን ፍሩ፥ ቁጥር 2

Post by Naga Tuma » 09 Sep 2025, 15:35

እርግጠኛ ነኝ ይህን አባባል ከብዙ ወራት በፊት እዚህ መድረክ ላይ ጽፌኣለሁ። ርዕሱን ለግዜዉ ማግኘት ኣልቻልኩም።

የጻፍኩትን ኣንብባችሁ የምታስታዉሱ እና ለመፈለግ በቂ ግዜ ያላችሁ ርዕሱን ማግኘት ከቻላችሁ በቅድምያ ኣመሰግናለሁ።

በቅርቡ ያስተዋልኩኝ እና ቀጥሎ የማስታዉሳችሁ ሁለት ማመን የምያዳግቱ እና ተዓምራዊ የሚመስሉ ታሪኮች ሰዎች መለኮትን ፍሩ ያልኩኝ ለእንደዚህ ዐይነት ተዓምራዊ የሚመስሉ ክስተቶች ነዉ ኣስብለዉኛል።

ኣማኝ የሆናችሁ በሙሉ እነዚህን ማመን የምያዳግቱ ተዓምራዊ የሚመስሉ ክስተቶችን ማብራራት ትችላላችሁ?

እነዚህ ሁለት ምሳሌዎች ናቸዉ እንጂ ወደ ኋላ ተመልሼ ሳሰላስል ሌሎችንም እያስተዋልኩ ይገርመኛል።

Naga Tuma
Member+
Posts: 6997
Joined: 24 Apr 2007, 00:27

Re: ሰዎች መለኮትን ፍሩ፥ ቁጥር 2

Post by Naga Tuma » 09 Sep 2025, 15:59

የመጀመርያዉን የጻፍኩኝ እዚህ ኣለ፥

ለማመን ከምያዳግቱ ታሪካዊ ገጠመኞች ኣንዱ

ኣማኝ የሆናችሁ ሁሉ መጠየቅ የምትችሉት ፌድ ኣፕ የጻፈዉ ዉስጥ እግዝኣብሔር የማይወደዉ ምን ስህተት ነበረ ማለት እና ምናልባትም ያልጠበቀዉ መልስ ተዓምራዊነት ኣለዉ ወይ ነዉ።

ያገኘዉ መልስ ዘላለማዊ ብይን ይሁን ኣይሁን መለየትን ለኣማኞች እተዋለሁ።

Naga Tuma
Member+
Posts: 6997
Joined: 24 Apr 2007, 00:27

Re: ሰዎች መለኮትን ፍሩ፥ ቁጥር 2

Post by Naga Tuma » 09 Sep 2025, 16:13

ሁለተኛዉን የጻፍኩኝ እዚህ ኣለ፥

ለማመን ከምያዳግቱ ታሪኮች፥ ቁጥር ሁለት

እዚህም ኣማኝ የሆናችሁ ሁሉ መጠየቅ የምትችሉት እኔ ሰለ ኣማኝ መሆን የጻፍኩትን ካነበበ በኋላ ሆረስ የሰጠዉ መልስ ዉስጥ እግዝኣብሔር የማይወደዉ ምን ስህተት ነበረ ማለት እና ምናልባትም ያልጠበቀዉ መልስ ተዓምራዊነት ኣለዉ ወይ ነዉ።

ያገኘዉ መልስ ዘላለማዊ ብይን ይሁን ኣይሁን መለየትን ለኣማኞች እተዋለሁ።

Naga Tuma
Member+
Posts: 6997
Joined: 24 Apr 2007, 00:27

Re: ሰዎች መለኮትን ፍሩ፥ ቁጥር 2

Post by Naga Tuma » 09 Sep 2025, 16:29

ፌድ ኣፕን እና ሆረስን የምታዉቁ ሁሉ ሁለቱም ዘላለማዊ የሆነ መለኮታዊ ብይን ኣገኙ ማለት ለሁለቱም እስከኣሁን ያልተገለጠ መለኮታዊ አሰራር ኣለ ማለት ነዉ። ኣይዴለም?

እኔ እስከኣሁን ድረስ እንደገባኝ ከሆነ የተጻፈዉ ትንቢት እና የሚፈጸመዉ የተሰደደዉ የኢትዮጵያ ኣምላክ በስፍራዉ መመለስ ነዉ።

ኣዕምሮ ያላችሁ ኣስቡ።

ኣማኝ የሆናችሁ ይገለጥልን ብላችሁ ጸልዩ ወይም መርምሩ እና የትኛዉ እንደሆነ ለዩ።

Naga Tuma
Member+
Posts: 6997
Joined: 24 Apr 2007, 00:27

Re: ሰዎች መለኮትን ፍሩ፥ ቁጥር 2

Post by Naga Tuma » 22 Sep 2025, 15:17

ለማመን ከምያዳግቱ ታሪካዊ ገጠመኞች፥ ቁጥር 3

ሁለት የወንድማማቾች ልጆች የኢትዮጵያ ማትሪክ ፈተናን ኣብረዉ ወስደዉ ኣንዱ ስያልፍ ሌላዋ ኣልተሳካላትም።

ያለፈዉ ተማሪ የሁለቱም ዉጤቶች የተጠበቁ መሆኑን ያምናል።

ያለፈዉ የመረጠዉ ኣዲስ ኮሌጅ ለመሄድ እየተዘጋጀ በእንቁጣጣሽ ቀን ፍጹም ያልጠበቀዉ ስሞታን ሰማ።

የአዲስ ዓመት ብቅልም ተጨምሮ ይሁን ከምር ይሁን ስሞታዉ ቢረዳኝ እኔም ኣልፍ ነበር ነዉ።

ያለፈዉ ተማሪ ቤተሰባዊ ፍቅር ያላቸዉ ሁለቱ ቤተሰቦች መካካል ያልጠበቀዉን ስሞታ ሲሰማ በጣም ከፍቶት ኣሁኑኑ መንገድ መጀመሬ ነዉ ይላል።

አመሻሽ ላይ ስለ ነበረ ከገጠር ወደ ከተማ መሄድን የሰጉት ቤተሰቦች ኣድረህ ሂድ ሲሉት ኣሻፈረኝ ብሎ ከቤት ይወጣል።

የቤተሰቡ መሪ የነበሩት የልተሳካላት አባት የቀበሌ ፖሊስ በሰፈሩ በኣጋጣሚ ኣይተዉ እከሌ፣ ፖሊስ ነህ እና ይህን ልጅ ያዝልኝ ይላሉ።

እኝህ የቤተሰብ ታላቅ መሪ የቤተሰቡ ነቢ አባት ነበሩ።

ያኮረፈዉ ልጅ የእሳቸዉን ቃላት ሲሰማ ምን ያህል እንዳስከፋቸዉ ገብቶት ወድያዉ ወደ ቤት ተመለሰ።

በሁኔታዉ የተደናገጡት ቤተሰቦች እና የሰፈር ሰዎች ተሰብስበዉ ምን እንደሆነ ማወቅ ፈለጉ።

ምራቅ ያልዋጡ ልጆች ጉዳይ ሆኖ ስብሰባዉ ብዙ ኣልቆየም።

ያለፈዉ ተማሪ ታላቅ ወንድም ስብሰባዉ ዉስጥ የተናገረዉን ያለፈዉ ተማሪ ሁሌም ያስታዉሳል።

ከን አከና ማቲ ኬሰት ሀፌ ለሚ ኬሰቱ ዸለቹን …

የተዘነጉ ቃላት ካሉ ስብሰባዉ ዉስጥ በርካታ ሰዎች ስለነበሩ ማረም ይችሉ ይሆናል።

ይህን ቃላት የተናገረዉ እንቁጣጣሽ የትዉልድ ቀኑ ነዉ።

ያለፈዉ ተማሪ የመጀመርያ ሰምስተር ዉጤቱ ከሁሉም የላቀ እና ካልተዘነጋ በኣዲሱ ኮሌጅ ኣዲስ ሬኮርድ ነበረ።

በሁለተኛዉ ሰምስተር የወሰደዉ የፊዚክስ ትምህርት ዉስጥ የመጀመርያ ፈተና ዉጤቱ በጣም የላቀ ሆነ። ከልተዘነጋ የእሱ ዉጤት ዘጠና አምስት ፐርሰንት ወይም እዛ አከባቢ ሲሆን ሁለተኛ ዉጤት ሰማንያ ሶስት ወይም እዛ አከባቢ ነበር። ፈተናዉ ሲመለስ ክፍል ዉስጥ ስላልነበረ ትክክለኞች ዉጤቶችን ክፍል ዉስጥ የነበሩት በደንብ ያስታዉሱ ይሆናል።

ምክንያቱም አስተማሪዉ የፈተናዉን ዉጤቶች ሲመልስ ይህን ዉጤት ያገኘ ተማሪን ማነጋገር እፈልጋለሁ ማለቱን ያልረሱ ይኖራሉ።

ማመን የምያዳግተዉ የዛን ቀን ማትሪክ ያልተሳካላት ትዳር መስርታ ትኖር ከነበረበት ቦታ ከባለቤቷ ጋር ሁለት ክፍለ ሃገራትን ኣቋርጠዉ ኣዲሱ ኮሌጅ የነበረበት ለጉብኝት ይሆን በሌላ ምክንያት መጥተዉ ይህን ተማሪ ማየት እንፈልጋለን ስላሉ ተማሪዉ ይህን ሰምቶ ከኮሌጁ ወጥቶ ከተማዉን ለማስጎብኘት ሄዶ ነበር።

ተማሪዉ ወደ ኮሌጁ ሲመለስ ኣስተማሪዉ ተናገረ የተባለዉን ሰምቶ ለምን ይሆን ብሎ በማግስቱ ቢሮዉ ሄደ።

ኣስተማሪዉ ልጁን ፊት ለፊት እያየ ይህን ፈተና ቀድሞ የሰጠህ ሰዉ ኣለ ወይ ብሎ ጠየቀዉ።

ተማሪዉም ፊት ለፊት ኣይቶት ኣይ ማለትም ኖ ኣለዉ። አስተማሪዉ ቀለስ ብሎ ክፍል ዉስጥ ዝምተኛ ነህ ብሎ ጥያቄዉን ኣበቃ።

ተማሪዉ የፈተናዉን ይዘት እና እንዴት በፍጥነት እንደሰራ ያስታዉሳል። የሚወደዉ ጽንሰ ሀሳቦች የበዙበት ፈተና ነበረ። የጽንሰ ሀሳቦችን ጥያቄዎች በፍጥነት እየመለሰ ጥያቄዎችን ሁሉ ለመመለስ ጣረ።

ያ የፊዝክስ ትምህርት አስተማሪ ህንድ ሃገር ዉስጥ የታወቀ ፕሮፌሰር ነበር ተብሎ ይገመታል። ስያስተምር ኣንድ ቀን ስለ ህንድ ሃገር ጄት ፕሮፐልሽን ላቦራቶሪ ዉስጥ ስለሚሰሩት ስያስተምር ለነበረዉ ኮርስ እንዲረዳ ቪድዮ ኣምጥቶ ስያሳይ እሱም ዉስጡ የነበረ መሆኑን ግምት ነበረ። እሱ ቪድዮዉን ስያሳይ ያ የምታዩት እኔ ነኝ ኣላለም።

ይህም ከተዘነጋ ያዩት ሌሎች ተማሪዎች ልያርሙት ይችላሉ።

ያ ተማሪ ከዛ ታላቅ ወንድሙ ጋር በእረኝነት ወይም ለአዝመራ የቤተሰብ መሬት ላይ ልጆች ሆነዉ ግዙፍ ደመናን ኣይቶ ከጀርባዉ ምን እንዳለ የጠየቀዉን ጥያቄ ያ የፊዝክስ አስተማሪ ስለ ዩኒቨርሳል ግራቪቴሽን ስያስተምር ነበር በደንብ የተመለሰለት። ልጅ ሆኖ የጠየቀዉን ጥያቄ ከጥያቄዉ በላይ ጥያቄዉን ለመመለስ የተደረገዉን ሙከራ ያስታዉሳል።

ይህ ሁሉ ማስታወሻ ያ ፈተና የተመለሰበት ቀን እና ብቸኛ ጉብኝት የተደረገበት ቀን መገጣጠም እንዴት ሊሆን ይችላል ለማለት ነዉ።

Naga Tuma
Member+
Posts: 6997
Joined: 24 Apr 2007, 00:27

Re: ሰዎች መለኮትን ፍሩ፥ ቁጥር 2

Post by Naga Tuma » 25 Nov 2025, 15:47

እስከ ኣሁን ማመን የምያስቸግሩ ሶስት ገጠመኞችን ጠቅሻለሁ።

ሶስቱንም ምንም ዐይነት ፊዝክስ ማብራራት እንደማይችል ይገባኛል።

እነዚህ ምንም ዐይነት ፊዝክስ ማብራራት የማይችል ተዓምራዊ ክስተቶችን ማሰላሰል ነዉ ስለ መለኮታዊ አሰራር የምያስጠይቀኝ።

በልጅነቴ ሰዉ ዋ ቤካ ወይም ነገር ኣዋቂ ብሎ ቃሉ ቤት ይሄዳል ማለት መስማት እና ገልመ ደንፋ ወይም የደንፋ ቤት የተባለን ከርቀት ከማየት ዉጪ መለኮታዊ ሀይል እንዳለዉ ኣልሰማሁም።

በደንፋ የምያምን ሰዉ ኣዉቃለሁ ማለትን ለመጀመርያ ግዜ የሰማሁኝ ኦክቶበር 31፣ 2025፣ ነዉ።

እስከኣሁን ጭላንጭል የመሰሉኝን የበለጠ እንዳሰላስል ኣድርጎኛል።

ምክንያቱም ስለ ኢትዮጵያ ወሳኝ ሚና ያላቸዉ ሁለት ሰዎች ኣንዱ በደንፋ የምያምን ቤተሰብ አባል፣ ሌላዉ በአከባቢዉ የኖረ ኢትዮጵያዊ መሆናቸዉ ነዉ።

ሁለቱ ወሳኝ ሚናዎች በኢትዮጵያ ታሪክ ዉስጥ መካድ የማይችሉ ጉልህ ናቸዉ።

እኔ ያልገባኝን መለኮታዊ አሰራር ዕዉነት ነዉ ብላችሁ ተቀበሉ ኣልልም።

እራሳችሁ በደንብ ኣስተዉላችሁ እራሳችሁን በመጠየቅ ለራሳችሁ ኣሳማኝ መልስ ኣግኙ ነዉ የእኔ ምክር።

Naga Tuma
Member+
Posts: 6997
Joined: 24 Apr 2007, 00:27

Re: ሰዎች መለኮትን ፍሩ፥ ቁጥር 2

Post by Naga Tuma » 28 Nov 2025, 16:19

ሁለት ገጠመኞች ያለመለኮታዊ አሰራር እንዴት ሊከሰቱ ቻሉ የተባሉ ስለ መለኮታዊ አሰራር የተለያየ አስተሳሰብ ያላቸዉ ሆነዉ ተከሰቱ።
“Fed_Up” wrote: እግዚአብሄትር ከኤርትራ ጋር መሆኑን ያውቃሉ?
Source: እግዚአብሄትር ከኤርትራ ጋር መሆኑን ያውቃሉ?
“Horus” wrote:ቤተ እውቀት የሌለው ሕዝብ ሺ ቤተ መቅደስ ቢኖረው ከንቱ ነው!
Source: ቤተ እውቀት የሌለው ሕዝብ ሺ ቤተ መቅደስ ቢኖረው ከንቱ ነው!

Naga Tuma
Member+
Posts: 6997
Joined: 24 Apr 2007, 00:27

Re: ሰዎች መለኮትን ፍሩ፥ ቁጥር 2

Post by Naga Tuma » 06 Jan 2026, 20:59

የሚከተለዉ ታሪካዊ ገጠመኝ ቢገርመኝም እኔ መለኮታዊ ምልክት ኣለዉ ማለት ኣልችልም።

የደርግ ዘመን የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት መንግስቱ ሀይለማርያም ቢሰማዉ ምን ማለት እንደሚችልም ኣላዉቅም።

ሁለተኛ ደረጃ ተማሪ እያለሁ ኣንድ ክረምት የልጅነት ነገር ሆኖ ከገጠር ከተማ የሚኖር ዝምድና ያለን ጓደኛዬን ልጠይቅ ብዬ ተነሳሁ።

ለቤተሰብ መጠየቅያ ትንሽ ስንቅም ጠይቄ ተሰንቆልኝ ሄድኩኝ። እንደዚህ ዐይነት አስተሳሰብ መጥቶልኝ ያደረኩኝ የዛን ቀን ብቻ ነዉ።

የጓደኛዬ ቤተሰብ ቤት ሳልደርስ በፊት መሃል ከተማ ደርሼ ከተማዉ ጭር ማለቱን ኣስተዉዬ ራመድ ራመድ እያልኩ ኣንድ ሰዉ ወደ እኔ መጣ።

አጠገቤ ደርሶ ዬት ነዉ የምትሄደዉ ብሎ ሲጠይቀኝ ገርሞኝ ፈርጠም ብዬ ጓደኛዬ ቤት ኣልኩት። ቀጥሎም በከተማዉ ዉስጥ የምታዉቀዉ ሰዉ ኣለ ወይ ብሎ ጠየቀኝ። የበለጠ ገርሞኝ የበለጠ ፈርጠም ብዬ ኣዎ ኣልኩት።

ከዛ በኋላ ምንም ሳይናገር ከአጠገቤ ሄደ።

እኔም እየገረመኝ መንገዴን ቀጠልኩኝ።

የጓደኛዬ ቤት ስደርስ ቤተሰቦቹ እንዴት ኣልፈህ እዚህ ደረስክ፣ ዛሬ በከተማዉ ዉስጥ አፈሳ ነበረ ብለዉ ጠየቁኝ።

ከዛ በኋላ የእንግዳ ሰዉ ከተማ መሃል ወደ እኔ መምጣት ምክንያቱን ገመትኩኝ።

የደርግ ዘመን የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት መንግስቱ ሀይለማርያም ይህን ታሪክ ቢሰማ እና ያ ከአፈሳ የተረፈ ተማሪ ተምሮ ዉጤት ያገኘ ነዉ ከተባለ እና እንኳንም ከአፈሳ ተርፎ ዉጤት ኣገኘ የሚል ከሆነ ስለ አፈሳ ምልክት ሊሆን ይችላል ማለት ይቻል ይሆን?

ለዚህ ጥያቄ እኔ ምንም መልስ ዬለኝም።

እኔ ኣብዛኛዉን የትምህርት ዕዉቀቴን ያገኘሁኝ በደርግ ዘመን ነበር። ኣንደኛ ደረጃ እና ኮሌጅ የተማርኩኝ በደርግ ዘመን የተሰሩ ትምህርት ቤቶች ዉስጥ ነዉ።

Naga Tuma
Member+
Posts: 6997
Joined: 24 Apr 2007, 00:27

Re: ሰዎች መለኮትን ፍሩ፥ ቁጥር 2

Post by Naga Tuma » Yesterday, 15:39

ይህን ርዕስ ስጀምር መሠረቱ ኢትዮጵያ የሆነ ሰዉ ታቦት ጣዖት ነዉ ይላል ብዬ ፍጹም ኣልጠበኩም።

ርዕሱን ያስጀመረኝን በጣም ፍንትዉ ያደረገዉ ይመስለኛል።

የታቦት ሃገር ኢትዮጵያን ለማፍረስ ኢሳያስ አፍወርቂ ታቦት ጣዖት ነዉ ከሚል መሠረቱ ኢትዮጵያ የሆነ ሰዉ ጋር የዋለ ከሆነ ታቦት ኢሳያስ አፍወርቂን ኣላሸነፈም?

ቃሉ እና አያነ አባ ዮሓንስ ለታን ኣላሸነፉም?

የወላይታ ሕዝብ ጦሳ፣ ስሙን ካልዘነጋሁኝ፣ ሀይለማርያም ደሳለኝን ኣላሸነፈም?

ምናልባት ደንፋ መረራ ጉድናን ኣላሸነፈም?

ምናልባት የምለዉ ጋና ግልጽ ያልሆነልኝ ስለሚመስለኝ ነዉ።

ኢትዮጵያ ዉስጥ ታቦትን፣ ቃሉ የተባለዉ ቃላት ተሸካሚ እና ጠባቂን፣ ነቢን፣ ደንፋን፣ ጦሳን የማያስማማ ዳያብሎስ ካልሆነ ምንድነዉ?

Naga Tuma
Member+
Posts: 6997
Joined: 24 Apr 2007, 00:27

Re: ሰዎች መለኮትን ፍሩ፥ ቁጥር 2

Post by Naga Tuma » Yesterday, 19:16

እኔ እጅግ በጣም የሚገርመኝ መለኮታዊ አሰራርን ለብቻ ትተን በሳይንሳዊ አስተሳሰብ ብቻ ብንሄድ ኢትዮጵያ ዉስጥ ታዳጊ ህፃናት ኢትዮጵያ ዉስጥ ስለኖሩ የእግዝኣብሔር አሰራር ምስክርነትን እየተማሩ ብያድጉ ሃጥዓት ኣለዉ?

የኢትዮጵያ ሕዝብ ከሰሜን እስከ ደቡብ፣ ከምስራቅ እስከ ምዕራብ ጥንታዊ የሆነ ሃይማኖታዊ አስተሳሰብ ባህሉ ዉስጥ ኣለ።

ስለዚህ ከቦረና ቃሉ እስከ ሐረርጌ ቃልቻ፣ ከወላይታ ጦሳ እስከ ሰሜን እግዝኣብሔር መለኮታዊ ምስክርነት ያላቸዉ ቢጠኑ በቂ የእግዝኣብሔርን አሰራር የማያስተምሩ ኣይዴሉም?

ይህ በጣም ቀላል የሆነ አስተሳሰብ ነዉ።

የክርስትና ሃይማኖት ተከታዮች እና ኣራማጆች ስለ ካዉንስል ኦፍ ኒስያ ብቻ በጣም ቀላል ጥያቄ በመጠየቅ ቀላል ህዳሴ ማድረግ ይችላሉ።

የካዉንስል ኦፍ ኒስያ ዉሳኔ በድምጽ ብልጫ ስለነበረ እና በካዉንስሉ ላይ የተገኙት ዐለም ኣቀፋዊ ስላልነበረ በዐለም ኣቀፍ ደረጃ ድምጽ ብልጫ ያልነበረዉ ነዉ።

ስለዚህ ምናልባት እየሱስ የእግዝኣብሔር መንፈስ ያደረበት ነብይ የነበረን የጥንት ሰዎች የእግዝኣብሔር ልጅ መስሏቸዉ ይችላል።

እግዝኣብሔር የሚልከዉን ማን ያዉቃል?

ስለማናዉቅ ምናልባት ነብይ ነበረ ብለን ክስተትን ብናጠና የጥንት ግዜ ስህተትን ማረም ይሆናል ማለት ኣይችሉም?

ይህ አስተሳሰብ በጣም ቀላል የሆነ ሳይንሳዊ እንጂ መለኮታዊ ኣይዴለም።

የመለኮታዊ ነገር እራሱን የቻለ ነዉ።

Post Reply