ዓይን-የሌላት ቅንድብ፡ [ሰሞንኛው ኤርትራዊ ስንኝ]
Posted: 09 Sep 2025, 10:24
ዓይን-የሌላት ቅንድብ፡ [ሰሞንኛው ኤርትራዊ ስንኝ]
መለስ ወዲ ኣለማሽ ኣባይን ባይገድብ፡
ኢትዮጵያ ነበረች ዓይን-ዬሌላት ቅንድብ።
ኢንጅነር ስመኘዉ የዓባዩ መሃንዲስ፡
የጎንደሩ ቅዱስ፡
መስቀል አደባባይ በመንፈስ ሚቀደስ።
ለኒህ ሁለት ፈርጦች የምድረ ኢጦብያ፡
ስላስመሰከሩ ያላቸውን ሙያ፡
ልዑል ክብር ኣላት ሃገረ ኤርትርያ!
በወዲ ዜናዊ "ተስሎ ተጠርቦ"፡
ሕወሓት ወያኔ "ቦተሊካ ጠግቦ"፡
ምድረ ኢትዮጵያዊን በጥበብ ሰብስቦ፡
በኢሕኣዴግ ዘመን አባይን ገድቦ፡
ግሩም ተግባር ሰርቷል "ለሃገሩ" አስቦ።
እኛ ኤርትራዉያን የመሃል እና የመስመር ዳኞች፡ በተለመደው ኤርትራዊ ጭዋነት ኩራትና ትህትና ጭምር፡ ለዓዲዃላዋ የእታችን ልጅና የሴራ ቦተሊካ ሰለባ ለሆነው ለጎንደሬው መሃንዲስ የቋጠርንላቸው ስንኝ መሆኑ ነው።
ግእዛዊው 2018 ዓ.ም. የሰላም የተመስገንና የጸጋ ዘመን ይሆን ዘንድ ተመኝተናል ለመላው የዓለም ህዝብ!
ተጣፈ "በዘመነ ጽምዶ" - በዘመነ ማርቆስ ዋዜማ