የእኔም ግድብ ነው ፡ እንኳን ደስ አላችሁ! “Ethiopians, both at home and in the diaspora, funded the dam's construction”
Posted: 07 Sep 2025, 09:26
ከኋላ የመጣ ዓይን አወጣ ይባላል።
የኢትዮጵያ እናቶች ሳይቀሩ መቀነታቸውን ፈትተው የገነቡትን ግድብ፣ ለዘመናት አኩርፎ የምን ግድብ ነው፣ የምን ቦንድ ነው ሲል የኖረው የዛሬ አለቅላቂ ካድሬ ዕሪሪሪሪሪሪ ማለቱ ይገርመኛል። ሜቴክ የሚባል ጅብ የህዝቡን ንብረት ምጥምጥ አድርጎ ሲበዘብዝና ፕሮጀክቱን በማዘግየትና ዋጋውን ከበጀቱ በላይ በመቆለል የዓለም መዛበቻ ሲያደርገን፣ ከውስጥ ሆነው አብረው ያሽቃብጡ የነበሩት ካድሬዎች ዛሬ ግድቡ በእነሱ ትከሻ እንደተገነባ ዓይነት አድርገው ዕሪሪሪሪሪሪ ሲሉም ይደንቀኛል።
በእኔ አስተያየት ግድቡ በማለቁ ደስተኛ ነኝ፣ እንደ ቶስቷሳ ካድሬ ግን በጭፍኑ አላንቋልጥም፣ ብዙ ጥያቄዎች ስላሉኝ፥
>>ወደ ሁለት ቢሊዮን ዶላር የሚቆጠር ገንዘብ ከፕሮጀክቱ ላይ የዘረፉትና ያባከኑት ሌባዎች ለምን በህግ አልተጠየቁም? ክንፈ ዳኘው እንኳን ለ 5 ዓመት ብቻ ሸቤ ተደርጎ እንደ ስብሃት እያፏጨ በነፃ ተለቋል። በብዕራቸው ብቻ የሰላ አስተያየት የሚሰጡት እነ መስከረም አበራ፣ ታዲዮስ ታንቱ፣ ኤርሚያስ መኩሪያ፣ አብዱልሰመድ ሞሐመድ፣ ከድር ሞሐመድ እስማኤል፣ ዮናስ አማረ ወዘተ ግን እስከ አሁን እስር ቤት እየማቀቁ ነው። ስለዚህ እንደ ከብት ካድሬ ዓይኔን ጨፍኜ ዕልልልልልል አልልም።
>> ግድቡ የተገነባው በኢትዮጵያውያኖች ገንዘብ ነው፣ ስለዚህ ዋናው ምስጋናና ደስታ ለእነሱ እንጂ ንቅዘቱ ውስጥ አብረው ሲጨማለቁ ለነበሩት ፖለቲከኞችና አሽቃባጮች አይደለም።
>> የህዳሴ ግድብ እግረኛ መሃንዲስ ለበረውና በግፍ ለተገየለው ስመኘው በቀለ እንኳን ደስ ያለህ እላለሁ። ገዳይህ ለዛሬ ተደብቆ ቢቀርም፣ ህዳሴን ለስምህ መጠሪያ ትተህልን ሄደሃል።
>> በዚያ በረሃ ሲፈጉና ሲኳትኑ ለነበሩት የግንባታ ሰራተኞች፣ እንዲሁም በስራ ላይ በአደጋ ህይወታቸውን ላጡት በብዙ ሺህ የሚቆጠሩት ወገኖቼና ዘመዶቻቸው ዕሪሪሪሪሪሪታ ሳላበዛ ምስጋና አቀርባለሁ።
>> ንፉግ አይደለሁምና፣ ፕሮጀክቱን ላስጀመረውና የግብፅን ተንኮል በመመከት በራሳቸው ሜዲያ ላይ ሳይቀር በብልሃት ሲሞግታቸው ለነበረው ክፉው መለስ ዜናዊ ክሬዲት እሰጠዋለሁ።
>> በተመሳሳይ እኔን ጨምሮ በደጋፊዎቹ ሰልፍ ታጅቦ በተባበሩት መንግስታት ፊት ቀርቦ በረቀቀ ሙያዊ መከራከሪያ ግብፅን ለረታው ዶር ስለሺ ደምሴ ምስጋና ይገባዋል።
>> ዕርጉሙና አራጋቢው መሽረፍት፣ አራት ኪሎ ጎዳና ላይ መጎተቱ ባይቀርም፣ ፕሮጀግቱን ስላስጨረሰ አመሰግነዋለሁ። ዋናው ፈተና ግን፣ መቀነቷን ፈትታ መዋጮ የሰጠችው እናት ከዚህ ግድብ ምን ትጠቀማለች የሚለው ጥያቄ ነው። ገሚሱ ተርባይኖች መስራት ጀሞረዋል ከተባለ ሶስት ዓመት ቢያልፍም፣ ኮሪዶሩ በድቅድቅ ሌሊት ፏ ብሎ በርቶ ነዋሪዎች ግን መብራት በፈረቃ ነው የሚያገኙት። ትክክል ነው፣ ግድቡ ያቆረው ውሃ ለልማት ይጠቅማል፣ አሳ በአሳ ቆስጣ በቆስጣ ያደርገናል ግን ይኸ መናጢው ወገኔን እንዴት ከረሃብ ያላቅቀዋል?
>> በመጨረሻም ትዕንቢታቸው ሁልጊዜም ለሚይዝላቸው ግርማዊ ቀዳማዊ ኃይለ ስላሴ እንኳን ደስ አለዎት እላለሁ!
>> አሁን ስራው ያለቀ መስሎህ ዕሪሪሪሪ ለምትለው የፕሮፓጋንዳ ጡሩምባ ካድሬ ደግሞ አንድ ምክር አለኝ። የውሃ ቧንቧ በየጊዜው በሚሰበርበትና ጥገና ለማግኘት ነዋሪው በሚጉላላበት ድሃ አገር፤ እንዲሁም በዕውቀት ድርቀት ምክንያት መንገድና አደባባይ በጎርፍ በሚጥለቀልቅበት አሰራር፣ ግድብን መጠበቅ፣ መንከባከብና ማደስ የመጨረሻ ፈታኝ ጉዳይ ነውና ስራው ተጠናቋል ብለህ አታንኮራፋ።
https://www.bbc.com/news/articles/cz71zndj001o.amp