Page 1 of 1

ሸዋ በሶዱ ህዳ ዘመን እና በዚህ ዘመን

Posted: 01 Sep 2025, 17:57
by Naga Tuma
ቅጽል ስሙ ሶዱ ህዳ የተባለ ሰዉ በኢትዮጵያ ዉስጥ ለመጀመርያ ግዜ ዕጽን መትካል የጀመረ ሰዉ ነበር የሚል አፈታሪክ ሰምቻለሁ። አፈታሪኩ ትክክል ይሁን ኣይሁን ኣላረጋገጥኩም።

አፈታሪኩ የሚለዉ በዚህ ዘመን ሶዶ ጅዳ የተባለዉ ትክክለኛ ቅጽል ስሙ ሶዱ ህዳ ነበር ይላል። ቅጽል ስሙንም ያገኘዉ ስር ኣላማጅ ስለነበረ ነዉ ይላል። ህደ ማለት ስር ማለት ነዉ።

ዕጾችን እና የዱር እንስሳዎችን ኢትዮጵያ ዉስጥ ጨምሮ ማላመድ ወይም ዶመስትኬት ማድረግ የተጀመረዉ አስር ሺህዎች ዓመታት ገደማ በፊት መሆኑን ታሪክ ጸሓፊዎች ኣስቀምጠዋል።

ስለዚህ የሶዱ ህዳ አፈታሪክ ዕዉነት ከሆነ ያ ታሪካዊዉ ሰዉ ሸዋ ዉስጥ የኖረዉ አስር ሺህዎች ዓመታት ገደማ ሊሆን ይችላል?

ይህ ማለት የክርስትና ሃይማኖት ሳይፈጠር ስምንት ሺህዎች ዓመታት በፊት ማለት ነዉ።

ከሁለት አስርተ ዓመታት በፊት በአንጋፋዉ የአሜሪካ ሳይንስ መጽሔት ዉስጥ የታተመ የዲ ኤን ኤ ጥናት ሰዎች ከአዲስ አበባ ዙርያ ወደ ሌላ አለማት ፈለሱ ይላል።

ሌላ ጥልቅ የሳይንስ ጥናት መሆን የሚችል በጣም ቀላል ጥያቄ ቡዴነ መስራት የት እና መቼ ተጀመረ ነዉ። ለጥናቱ ቡዴነ የሚለዉ ቃል የተመረጠበት ምክንያት በእንግሊዘኛ ፉድ ለሚለዉ ቃል መሠረት መሆኑ ፍንጮች ስላሉ ነዉ።

ቡዴነ መስራት መጀመር ዕጽ ከማላመድ መጀመር በኋላ ብቻ ነዉ መምጣት የሚችለዉ። ቀመዲ ወይም ዊት ሳይመረት ወይም ሳይሰበሰብ በፊት ዳቦ መጋገር ሊኖር ኣይችልም።

እነዚህን ጥያቄዎች የማነሳዉ ሁሉም ኢትዮጵያዊያን ሸዋን ጨምሮ ኢትዮጵያ ዉስጥ ሰዎች ዕጾችን እና የዱር እንስሳዎች እያላመዱ ይኖሩ የነበረዉ ዘመን ምን ያህል ጥንታዊ እንደነበረ እራሳቸዉን ጠይቀዉ ያእራሳቸዉን መልስ እንድያገኙ ነዉ።

የዚህ የዘመን ወይም የጀበነ ጥንታዊነትን ማወቅ ከዛ በኋላ የሰዉ ልጅ ንቃተ ህሊና ምን ያህል ዳብሮ እንደነበረ መገመት እና ማጥናት ይቻላል።

ቃላትን መርጦ የመናገር እና ፊደላትን ከመፍጠር ኣልፎ ፊደላትን መርጦ መጻፍ ማለት በቀላሉ የተደረሰበት ንቃተህሊና ኣይመስለኝም። ሠ እና ሰ ተመሳሳይ ድምስ ቢኖራቸዉም የተለያየ አጠቃቀም ነበራቸዉ። ቅኔ ኣንድ ቃልን ለሰም እና ለወርቅ ይጠቀማል። መቅማቅሰ ብዙ ሳይተነትን በቂ መልዕክትን ይገልጻል።

ቤተሰብ የጉድፈቻ ልጅን የጉድፈቻ ልጅ ነህ ሳይለዉ እንደ ኣንድ ቤተሰብ አባል ኣሳድጎ ያኖራል።

በሶዱ ህዳ ዘመን ነመ ማለት እንጂ ገብረ የማለት እና የመባል ክፍፍል መኖሩን መገመት ሌላ ጥናት የምያስገዉ ርዕስ ነዉ።

ምናልባትም ሶዱ ህዳ ዕጽን ያላመደበት ዘመን ድቃላ የሚባል ቃል ሆነ አስተሳሰብ ነመ እያሉ በኖሩት ማህበረሰብ መካከል መኖሩን መገመት ያስቸግራል። በቅሎ ከፈረስ እና ከኣህያ ስለምትወለድ ድቃላ ትባላለች።

ገብረ ካሉት እና ከተባሉት የሚወለድ ሰዉ ድቃላ ይባል የነበረ መሆኑን ኣላዉቅም። የነበረ ከሆነ ፀያፍ ቃል መሆኑን ማወቅ ብዙ ትምህርት የምያስፈልግ ኣይመስለኝም።

ይህን ያህል ንቃተ ህሊና የነበረዉ ማህበረሰብ ዉስጥ ነዉ በዚህ ዘመን ፀያፍ የሆኑ የጋጠወጦች ቃላት ለሰላማዊ ሕዝብ በጋጠወጦች የሚረጩት።

ለጥፋት ወቀሳን ከሰላማዊ የዳበረ ንቃተህሊና አገላለጽ ለይቶ ማወቅም ብዙ ትምህርት የምያስፈልጉ ኣይዴለም።

እ አ አ በ1991 የኢትዮጵያ እና የኤርትራን መንግስታዊ መዋቅሮችን የተቆጣጠሩት የኤርትራዉ ኢሳያስ አፍወርቂ እና የኢትዮጵያዉ መለስ ዜናዊ እና የኦነጉ ዮሓንስ ለታ በኢትዮጵያ ላይ የማመጽ ትግሎቻቸዉን የጀመሩበት ዕድሜዎቻቸዉ በማንኛዉም መመዘኛ ምራቅ የዋጡ እና የተመራመሩ ነበሩ ማለት ኣይቻልም።

በወጣትነት ዕድሜዎቻቸዉ ዐላማ ብለዉ መነሳታቸዉ ኣይደንቀኝም።

በዚህ ዘመን እጅግ የሚገርመኝ ኣሁን በህይወት ያሉት ሆነ ታማኝ ደጋፊዎቻቸዉ ምራቅ ሳይዉጡ እና ብዙ ሳይመራመሩ የጀመሩት ትግሎቻቸዉ እንከን ዬለሽ ዐይነት ኣድርገዉ መከራከራቸዉ ነዉ።

የህዝቡን ንቃተህሊና ወደኋላ ጎትተዋል የምያስብሉ በርካታ ነገሮችን ማስተዋል ሲችሉ እንከን ዬለሽ ዐይነት ክርክሮቻቸዉን ታሪክ የምያወሳዉ እንዴት ይሆን?

አስር ሺህ ዓመታት በፊት ዕጽ ማላመድ የጀመረች ሃገር ናት የሚል የታሪክ መላምት ዕዉነት ከሆነ ከዚህ ሁሉ ዘመናት በኋላ ለመጽናት ትንገዳገዳለችን ታሪክ የምያብራራዉ እንዴት ነዉ?

ወይ መመራመር ነዉ። ወይም በተመራመሩት መመከር ነዉ።

Re: ሸዋ በሶዱ ህዳ ዘመን እና በዚህ ዘመን

Posted: 01 Sep 2025, 20:19
by Horus
ዲዲቲ/ናጋቱማ፣
ሶዶ ጅዳ ነኝ ብለህ ስለ ምታምን የዘር ሃረግክን ለማግኘት መልፋትህ ክፋት የለውም ። ነገር ግን የዲ ኤን ኤ ሳይንስ አፈ ታሪኮችን ሁሉ እየሻረ ባለበት ዘመን አዲስ አፈ ተረት ለማሰራጨት መሞክርህ ሞኝ ያሰኝሃል። ማን እንደ ሆንክ ለማወቅ ዲ ኤን ኤክን አሰራ አለቀ።

በተረፈ ሰደን ኦሮሞች (የጋብቻ ወይም የአማች ኦሮሞ ማለት ነው) ለምን ራሳቸው ሶዶ ጅዳ ብለው ትርጉም የለሽ ስም እንደ ሰጡ እነግርማ ብሩን ጠይቃቸው ።

ወደ ቋንቋው ስንመጣ አሁንም የተለመደ የደንቆሮ ስህተት እየሰራህ ነው። ህዳ ህጻ (ህጻን) ጽንስ ፣ ልጅ ፣ ዘር ፣ እጽ ፣ ማለት ሲሆን ኦሮሞች ከግዕዝ የተዋሱት ቃል ነው ። ደጋግሜ እንደ ነገርኩህ መዋስ በሁሉም ካልቸር ያለ ነገር ስለሆነ የሚያሳፍር አይደለም ። ነገር ግን ጽንስ ፣ ጂን፣ ቅርስ ፣ የአንድ ነገር መጀመሪያ ስር ወይም ዘር በፍጹም ከሰው ስም ጋር አታያይዘው ። ቃሉ በሴም ቋንቋም ሆነ በላቲን አንድ ስለ ሆነ!!!! ጂኒሲስ ማለት ጥንስስ ማለት!!! የዉሸት ትርክት ለመፈብረክ ስትል ራስክ ማጋለጥ የለብህም!

ቡዴነ (ቡዴና ፣ ሙዴና) የሚባሉት ቃላትም ኦሮሞች በቀጥታ ከሴም ቋንቋ ተናጋሪዎች የተዋሱት ነው ። ኢድ ምግብ ማለት ነው ። ዛሬ ሙስሊሞች ኢድ አል ፍጥር እንደሚሉት ማለት ነው ። በግዕዝ ማዕድ ይባላል። የምግብ ማብሰያ ቦታ ማዕድ ቤት (ማድቤት) ይባላል። ያ ነው ቡዴና ሙዴና የምትሉት ።

ዳቦ የሚለው ቃል በፍጹም በኦሮሞኛ ውስጥ የለም ። ዳቦ ፣ ዱፋ፣ ፒታ፣ ቸፓታ ፣ ጣቤታ ፣ ጣይታ ከሱመሪያ ዘመን ጀምሮ የመጣ ጥሬ ቃሉ እንደ ኦቨን የሚቆፈረው ምድጃ ማለት ነው። ድፎ የምንለው ጥንት ዱፋ የሚባለው ምድጃ ወይም ኦቨን ማለት ነው።

ስለዚህ አፈ ታሪክ ለመፈብረክ ከመሞከርህ በፊት የሕዝቦችን ታሪክና የቋንቋና ባህር አወራረስ ላይ ትንሽ ጥናት አድርግ ።

ለምሳሌ ኧርባታ የሚባለው ኦሮሞች እራት ለማለት የሚጠቀሙትን ቃል ውሰድ። ኧርባት እንዳለ ክስታኔኛ ነው ፣ እራት ማለት ነው ። ቃሉ ከየት መጣ በል? ኧርብ ማለት የጸሃይ መጥለቅ ማለት ነው ፤ እሱም ምዕራብ ይባላል። በአረብኛ የጸሃይ መግባት ግሩብ ሂሩብ (ገርብ) ይባላል። ሌላው ቀርቶ ኢሮፕ የሚለው የምዕራባዊያን ስም ይህ ኧርብ ከተባለው ቃል የወረደ ነው ። ዛሬ በኢትዮጵያ አርብ የምንለው ቀን የጸሃይ መጥለቂያ ማለታች ነው። ለዚህ ነው ቅዳሜን ቀዳሚ ሰንበት የጸሃይ መውጫ ቀን ይባል የነበረው። ምራብ የጸሃይ መጥለቂያ ቦታ ማለት ነው ። ኧርባት ጸሃይ ከገባ በኋላ የሚበላ ምግብ ማለት ነው ። ይህን ውብ ቃል ኦሮሞች መዋሳችው ድንቅ ነው ። ግ ን የቃሉን ምነንት መለወጥ አትችልም ።

ለምሳሌ ፈረንጆች አለምንም ችግር አንድ ቃል ከፈረንሳይ የተዋስነው ፣ ከጀረመን የተዋስነው ይላሉ ! የሚያሳፍር ነገር አይደለም ! ኦሮሞኛ የኢትዮጵያ ቋንቋ ነው! ግዕዝም እንዲሁ! ዉሸት ግን ይብቃን

ነጋቲ