ፈለቀ ማሩ፡ የእንሾሽላው ንጉስ!
Posted: 31 Aug 2025, 22:35
አርቲስት ፈለቀ ማሩ የዛሬ 12 ዓመት ይህን ጥንታዊ የሰርግ ባህል ከተረሳበት አንስቶ በዚህ መልክ ካቀረበው ወዲህ በሰርግ ባህል ላይ አብዮት ነው የቀሰቀሰው! እንሾሽላ ጥንት ሴት ልጅ ሰርጓ እንደ እሁድ ሆኖ አርብ ማታ ቤተሰቦቿ እንሶስላ እየታሰረላት መላ ቤተ ዘመዶቹዋ እጅግ በማይረሳ በዓል የሚያሰናብቷት እለት ነው! ፈለቀ ይህን ዝክረ እንሾሽላ ካወጣ በኋላ ባህሉ እንደ ሰደድ እሳት መነሳቱ ብቻ ሳይሆን ቸግ (ፍጥምጥም) የሚባለውን ባህልንም በዚያ ልክ መለሰው። ቸግ ከጉራጌ ባህልነት አልፎ አሁን ሽምግልና የሚባለው ባህል ከፍጥምጥምነት አልፎ እራሱ ሰርግን እየተካው ነው። አሁን ሽምብልና የሚባለው የጋብቻ ድግስ የተነሳው ከቸግ ባህል ነው ። ቸግ ሽማግሎች የወንድ አባቶች ወደ ሴት ልጅ ቤት የሚላኩበት ባህል ነበር! አሁን ግ ን እራሱ ሰርግ ሆኖዋል!