Page 1 of 1

ኢትዮጵያ ዛሬ

Posted: 29 Aug 2025, 10:03
by Thomas H
ወይ አቀማመጥ! ወይ ፕሮቶኮል !አሁን ይሄ ሰውዬ ትራምፕ ጋር ቢቀርብ እንደዚህ ይቀመጣል ? አገር በ7ኛ ክፍል ደንቆሮ ስትመራ ሁሉም ይንቃታል !

የኢትዮ ቴሌኮም እና የሳውዲ ቴሌኮም ስምምነትን ተከትሎ ቴሌብር በሳውዲ አረቢያ አገልግሎት ሊሰጥ ነው

#Ethiopia | ኢትዮ ቴሌኮም እና የሳውዲ ቴሌኮም ኩባንያ የኢትዮጵያ ትልቁ የዲጂታል ክፍያ ሥርዓት የሆነውን ቴሌብር ወደ ሳውዲ ገበያ ለማስገባት ትብብራቸውን ለማጠናከር ተስማምተዋል፡፡

በሳውዲ ቴሌኮም ኩባንያ የሴልስ ከርየር እና ሆልሴል ምክትል ፕሬዝዳንት ዚያድ ሃማድ ኤ. አልሃሶን እና የከርየር ሴልስ ዳይሬክተር ባንደር ኤ. አልኮዳይር የተመራ ልዑክ ከኢትዮ ቴሌኮም ማኔጅመንት ጋር ውይይት አድርጓል፡፡

የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈፃሚ ፍሬሕይወት ታምሩ “ለጋራ ተጠቃሚነት ብዙ ልንተባበርባቸው እና አዳዲስ የዕድገት አማራጮችን ልንፈልግላቸው የምንችላቸው ዘርፎች ያሉ ሲሆን፤ እነዚህም የሀገሮቻችንን ዲጂታል ሽግግር የሚያሳድጉ እና ይበልጥ ሁሉን አቀፍ የሆነ የዲጂታል ኢኮኖሚ ልማትን የሚያፋጥኑ ዕድሎች ናቸው” ብለዋል።