Page 1 of 1

በጦርነቱ ወቅት አካሏ የጎደለ ውድ ትግራወይቲ እህታችን ለ almaze እና ለ Deqi Arawit ያስተላለፈችው ልብ የሚነካ መልዕክት

Posted: 26 Aug 2025, 17:07
by Digital Weyane
:roll: :roll: :roll: :roll:
Please wait, video is loading...
ትርጉም

ልብ የሚነካ የወጣትዋ ተማፅኖ!

እባካችሁ ከእኛ ተማሩ!

ሰላም ወንድሞቼ እንዴት አላችሁ ደህና ናችሁ? አሁን ላስተላልፈው የፈለኩት መልእክት እኛ ታጋዮች ጉዳታችን ሁሉ ነገር እያወጣን ፖስት የምናደርገው መልእክት ለማስተላለፍ ነው። ከእኛ ተማሩ ጦርነት በእኛ ይብቃ የትግራይ እናት እስከመቼ ነው እያነባች የምትኖረው? በእኛ አይበቃም? እኛ መማርያ አንሆንም? ማሰከምያ አጣን፣አካላችን ጎደለ፣መብላት አንችል ጭንቅላታቸው ተመተው የአእምሮ በሽተና የሆኑ አሉ። ብዙዎች አካላቸው ጎድሎ ሰው ሊያያቸው የሚከብድ ጓዶች አሉ።

ከእኛ ለምን አትማሩም ድጋሜ እንደኛ ልትሆኑ? መስዋዕትነት ይበቃል እኛ ሞከርን አይደል? ከእንግዲህ የሚያስፈልገው በየሃይማኖታችን ፆምና ፀሎት ብቻ ነው።

ተጋሩ ወንድሞቼ ወጣት እስከመቼ ነው እያለቀ የሚኖረው? ይሄ ወጣት መሄጃ ነው ያጣው በሊብያ ቢሄድ ይታሰራል፣ ይሞታል እዚህ ሆኖ እንዳይሰራ፣ መስራት አይችልም እንዴት ብሎ ይስራ? ይህንን የጦርነት ወሬ እየሰማ በዚህ የሚጠቀሙ አሉ አንዳንድ ሰነፎች ነጋዴዎች ይጠቀማሉ፣ ባለስልጣናት ይጠቀማሉ።

ስለዚህ ለእነሱ ተብሎ የእኛ ህይወት መገበር አለበት ማለት ነው? እስኪ በረሃ ያላችሁ ታጋዮች ምን ታስባላችሁ? እስኪ አቋማችሁን ግለፁ? አሁንም ልትዋጉ ነው እየተሰለፋችሁ ያላችሁ? እኔ በእውነት አሁን የሚዋጋ ታጋይ ካለ እኔ ታጋይ አልለውም ለምን ብሎ ነው የሚዋጋው? እስኪ ለማን ነው? ደማችን ለመገብረው ነው? የምንዋጋው? ሁሉ ጊዜ ወደ ጦርነት ያስገባን አካል ለጊዜው ነው ጥሩ ነገር ሊሰብከን የሚችለው ይሄ ልናገኝ ይሄ ልናገኝ ነው ሊለን ይችላል ነገርግን ልክ እንደዛሬ የጓዶቻችን ደም እንደተካድነው በከንቱ እንዲፈስ ምንም ትርጉም እንዳይኖረው እያደረጉ እንዳሉት አሁንም ለሚፈጠረው ጦርነት እንደዚህ ነው የሚያደርጉት።

ምንም አዲስ ነገር አይፈጠርም እኛ ከማንም ጋር በሰላማዊ መንገድ ነው ችግራችን መፈታት ያለበት። እስኪ ሁላችንም ፀሎት እናድርግ ፀሎቱ ግን ከልባችን ይሁን ልባችንን ጥለን በእግዚአብሔር ፊት እንውደቅ እንምበርከክ፣ከልባችን ከፀለይን አንድ ቀን ትበቃለች፣እግዚአብሔር እንዲሰማን አሁን ፆም አለ ተግባር ግን የለም፣ቤተክርስትያን እግዚኦ እንላለን ከእዛ ስንወጣ ርሕራሔ የለም። እባካችሁ ከእኛ ተማሩ እኛ ፖስት የምናደርገው አንድ ከእኛ እንድትማሩ ነው የእኛ ጥንካሬ ብቻ እንድታዩ አይደለም ሁላችንም ሰላም ብቻ እንስበክ ብቻ ሁኔታው ከባድ ነው"።

Re: በጦርነቱ ወቅት አካሏ የጎደለ ውድ ትግራወይቲ እህታችን ለ almaze እና ለ Deqi Arawit ያስተላለፈችው ድንቅ መልእክት

Posted: 26 Aug 2025, 18:34
by Digital Weyane
የሚሰማ ጆሮ ያለው የብልፅግና ካድሬ ይስማ! :roll: :roll:

Re: በጦርነቱ ወቅት አካሏ የጎደለ ውድ ትግራወይቲ እህታችን ለ almaze እና ለ Deqi Arawit ያስተላለፈችው ድንቅ መልእክት

Posted: 26 Aug 2025, 22:41
by Digital Weyane
:roll: :roll: :roll: :roll:

Re: በጦርነቱ ወቅት አካሏ የጎደለ ውድ ትግራወይቲ እህታችን ለ almaze እና ለ Deqi Arawit ያስተላለፈችው ልብ የሚነካ መልዕክት

Posted: 27 Aug 2025, 01:26
by Abdisa
The poor girl got betrayed by the very people who forced her into the battlefield, and who have since sided with Abiy to finish her off. :x :x

Re: በጦርነቱ ወቅት አካሏ የጎደለ ውድ ትግራወይቲ እህታችን ለ almaze እና ለ Deqi Arawit ያስተላለፈችው ልብ የሚነካ መልዕክት

Posted: 27 Aug 2025, 12:09
by Fiyameta
:shock: :shock: :shock: :shock: :shock: :shock: :shock: :shock: