Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Naga Tuma
Member+
Posts: 6789
Joined: 24 Apr 2007, 00:27

ሬሲስት ማለት እና የኢትዮጵያ መሠረታዊ ጎሳዎችን ማወቅ

Post by Naga Tuma » 21 Aug 2025, 00:48

ሬሲስት ማለት የተለመደ ቢሆንም በኢትዮጵያ ቋንቋዎች ትክክለኛ የሆነ ትርጉሙን የምያዉቅ የቋንቋ ልሂቅ ኣለ?

በቅርቡ ኣዲስ ጎሰኛ የሚል አባባል ከጻፍኩኝ ወዲህ ሬሲስት ለማለት ጎሰኛ ማለት ትክክለኛ ትርጉም መሆኑ ኣላሳመነኝም።

ከኣሁን በፊት ኤትኒክ ማለትን ወደ ኢትዮጵያ ቋንቋዎች ብንተረጉም ምን ቃላት ትክክለኛ ትርጉም እንደሚሆኑ ጠይቄ ኣሁንም መልስ ኣላገኘሁም።

ሬሲስት ሆነ ኤትኒክ ትክክለኛ ትርጉሞቻቸዉን ሳናገኝ በፊት ግምታዊ ቃላትን መጠቀም ሌላ ጥራዝ ነጠቅነት ይሆናል።

ኢትዮጵያ ዉስጥ የሰዉ ሆነ የሰብል ጎሳ ሲባል በጣም ግልጽ ነዉ። እኔ እስከማዉቀዉ ድረስ ጎሳ ማለት የተለመደ ቢሆንም ጎሰኛ ማለት የተለመደ ኣይዴለም።

ስለዚህ የሬሲስትም ሆነ የኤትኒክ ትክክለኛ ትርጉሞችን መፈለግ ለቋንቋ ልሂቃን መተዉ ይቻላል።

የሰዉ ጎሳ ሲባል ግን ግልጽ የሆኑ ምሳሌዎችን መጥቀስ ይቻላል።

በደቡብ ኢትዮጵያ የቦረና ጎሳ እና የገብረ ጎሳ ማለት የማያሻማ ነዉ።

በምስራቅ ኢትዮጵያ የአፋር ጎሳ እና የኢሳ ጎሳ ማለት የማያሻማ ነዉ።

በምዕራብ ኢትዮጵያ የጉሙዝ ጎሳ እና የአኙዋ ጎሳ ማለት የማያሻማ ነዉ።

የሰሜን ኢትዮጵያ ክፍል ጎሳዎች ለእኔ ግልጽ ባይሆኑም አገዉ ጎሳ ማለት የማያሻማ ይመስለኛል።

የሃይማኖት ትምህርቶች ጠንክረዉ የሰነበቱበት አከባቢዎች ክርስትያን የሆኑ እና ያልሆኑ መካከል፣ ሙስሊም የሆኑ እና ያልሆኑ መካከል፣ እና ክርስትያን የሆኑ እና ሙስሊም የሆኑ መካከል ልዩነቶች ነበሩ።

ሌላ መሠረታዊ ልዩነት የነበረዉ ገብረ ባሉ እና በተባሉ መካከል ነበር።

በኣንድ ሃገር ሉዓላዊነት ስር የሁሉም ዜጎች እና ጎሳዎች እኩልነት ይስፈን ማለት ይህ መሠረታዊ የሆነ የተፈጥሮ ልዩነት ኣልነበረም ማለት ኣይዴለም። ኣልነበረም ማለት ለምሳሌ ሀይለእየሱስ እና ገንረእየሱስ ወይም ክፍለማርያም እና ገብረማርያም የሚሉ ስሞች ኣልነበሩም ብሎ እራስን ማታለል ወይም ንዝህላልነት ይሆናል።

ለዚህ መሠረታዊ የተፈጥሮ ልዩነት ምሳሌ መሆን የሚችለዉ የቦረና እና የአኙዋ ጎሳዎች መገናኛ፣ የሁለት ክርስትና ሃይማኖቶች መገናኛ፣ የምሽነሪ ትምህርት እና የኢትዮጵያ ትምህርት መገናኛ፣ እና የባህል እና ክርስትና መገናኛ የሆነዉን የምዕራብ ኢትዮጵያ ክፍልን መጥቀስ ይቻላል።

በኣንድ ሃገር ዉስጥ የሃገር ሉዓላዊነት እና የጎሳዎች እኩልነት ለድርድር የማይቀርቡ ሆኖ ሁሉም በሰላም ሠርተዉ ይደጉ ማለት ስለ ታሪክ ሳይሆን ስለ ወደፊት ተባብሮ መኖር እና ሰርቶ ማደግ ነዉ።

ይህ ማለት ጎሳዎች ሁሉ ታሪካዊ የሆነ የንቃተህሊና ልዩነት ኣልነበራቸዉም ማለት ነዉ?

ቦረና ድረስ ሄዶ ስለ ቦረና ጎሳ ኣጥንቻለዉ ያለዉ ዶክተር ገመቹ መገርሳ ስለ ቦረና ጎሳ እና አጠገቡ ስላሉት፣ ምናልባት እሱንም ያበቀሉትን የአኙዋ ጎሳ፣ ንቃተህሊናዎችን ኣጥንቶ ኣመዛዝኖ ያዉቃል? ኣጥንቶኣቸዉ ያመዛዘናቸዉ ከሆነ ተመሳሳይ ናቸዉ ይላል ወይስ ልዩነት ኣላቸዉ ይላል?

ኣጥንቶ ሳያመዛዝን አፍ የሚከፍት ከሆነ እንደዚህ ዐይነት አፍ መክፈትን ከየት ኣመጣዉ?

የኣንዱን ጎሳ ንቃተህሊና ኣጥንቶ የሌላዉን ጎሳ ንቃተህሊና ገሸሽ ማድረግ ማንን ይጠቅማል?

የእነዚህ ሁሉ ጥናቶች ኣስፈላጊነት የሁሉንም ጎሳዎች ንቃተህሊናን የምያበለጽግ ይሆናል። ገሸሽ የሚደረጉትን ጨምሮ ማለት ነዉ። ይህን ኣለማድረግ ከማንም በላይ እራስን ማታለል ነዉ።