ቃሉዎች እና ቃልቻዎች የምያዉቁት ዕዉነት ኣላቸዉ?
Posted: 19 Aug 2025, 15:05
ብዙ ሰዎች ኣንድ ጽንሰ ሀሳብ ከመሠረቱ ሳይገባቸዉ ብዙ ለመተንተን ይጥራሉ።
ወጣት ሆኜ የሰማሁኝ ኣንድ ክርክር የአማራ ቃልቻ እና የኦሮሞ ቃሉ የተለያየ አስተሳሰብ ኣላቸዉ የሚል ነበር። ቃሉ ሀይማኖተኛ፣ ቃልቻ መተተኛ ዐይነት ተደርገዉ ይተነተኑ ነበር።
የሰዉን አስተሳሰብ ማነስን ፍንትዉ ኣድርጎ ያሳያል።
ይህ ክርክር ጠንክሮ የቅኝ ግዛት ጥያቄ ኣለ ሲባል ቃልቻ ቃሉን ቅኝ ገዛ እንደማለት ነዉ የሚል ምሳሌ ያመጣል።
ስለ ኢትዮጵያ ጥንት ታሪክ ሳነብ ፍጹም ከማልረሳዎች ዉስጥ ኣንዱ የሰሜኑ ክፍል የጥንት ኢትዮጵያኖች በእግዝኣብሔር ፈቃድ የተባረኩ እና የተረገሙ ጎሳዎች የሚል ሀይማኖታዊ ወሬ ሲሰሙ ግራ ተጋቡ ይላል።
በኣንድ በኩል በእግዝኣብሔር ፈቃድ የተረገሙ ጎሳ ከተባሉት ጎራ መመደብ ኣልፈለጉም ይላል።
በሌላ በኩል ወሬዉን ሳይሰሙ በፊት የነበራቸዉን ማንነት እና መሠረት መርሳት ኣልፈለጉም ይላል።
በዚህ ምክንያት ለሁለት ሺህ ዐመታት ገደማ ያዘገመ የማንነት ትግል ዉስጥ ገኑ ይላል።
ሃይማኖተኞች ስለ ነበሩ በእግዝኣብሔር ፈቃድ የተባረኩ እና የተረገሙ የተባለን ወሬ ተቀበሉ እንጂ ኣልጠየቁም።
በዚህ ዘመን ቢሆን እግዝኣብሔር ያፈጠራቸዉን ጎሳዎች ሁሉ በእኩልነት የሚመዝን እንጂ ኣንዱን ጎሳ በርኮ ሌላዉን የሚረግም ኣይደለም ማለት ይችሉ ነበር።
አበረ፥
ሰሞኑን ስለ ኢትዮጲስ እዚህ መድረክ ላይ የጻፍከዉ ይህን ታሪክ በቀጥታ ይመለከታል።
ታሪኩ የሚለዉ በእግዝኣብሔር ፈቃድ የተባረኩ እና የተረገሙ ጎሳዎች የሚባል ወሬን ሳይሰሙ በፊት ኢትዮጲስ የቀድሞ ማንነቱ እና መሠረቱ በዚህ ዘመን ኩሽ የሚባል ጎሳ ነበር ይላል።
በእግዝኣብሔር ፈቃድ ከተረገመ ጎሳ ነዉ ላለመባል በዚህ ዘመን ሴም ከሚባለዉ ጎሳ ሴሜታይዝድ በመሆን የቀድሞ ማንነታቸዉን ካዱ ይላል።
ይህ ሁሉ በጥልቀት ከታወቀ በኋላ የዛን ዘመን የተከሰተን ይህን ሁሉ ዘመናትን ሰንብቶ ኣለማረም ምን ይባላል?
ብዙ ሰዎች የኢትዮጵያ ህዳሴ ሲሉ ይሰማሉ። ለእኔ የኢትዮጵያ ህዳሴ ማለት የኢትዮጲስ ህዳሴ ማለትም ነዉ። ከህዳሴ በላይ እዴሳ የበለጠ የሚገልጸዉ ይመስለኛል።
የእዴሳ ኣንዱ ክንዉን በዛ ዘመን የተከሰተ ስህተት ላይ ብርሃን ቦግ ማድረግ ነዉ። የተከሰተዉ ስህተት ላይ ብርሃን ቦግ ማድረግ እርማቱን መጀመር ነዉ።
ይህ ብርሃን እዴሳ እና ህዳሴን፣ ቃሉ እና ቃልቻን፣ ገዳ እና ገዳምን፣ ዉዳሴ እና ዌድሴን፣ ፈይሳ እና ፈወሰን፣ ወዘተ ጎን ለጎን ኣድርጎ ያሳያል።
በዛን ዘመን አማራ እና ኦሮሞ የተባሉ የጎሳ ስሞች እንደነበሩ ኣላዉቅም።
የጥንቱ ታሪክ ላይ ብርሃን ቦግ ስናደርግ ለብዙ ሳይንሳዊ ጥናቶች በር መክፈት ማለት ነዉ።
የዚህ ዐይነት ጥናት አዉሮፓ ዉስጥ የመጀመርያዉን ሬይነሳንስ ኣስከተለ። የጥናታቸዉ መሠረት የጎደስ አቴና ዘመን የነበረዉ የጥንት ግሪክ ስልጣኔ፣ ኣዉሮፓዊ የነበረ የተባለ ነበር።
እኔ የዚህ ዘመን ሁለተኛዉ ሬይነሳንስ የምለዉ የጥናቱ መሠረት ከስደት በፊት የነበረዉ የፈረኦ አክናተን ዘመን የነበረዉ የጥንት ግዜ ኣፍርካዊ ስልጣኔ ነዉ።
ለዚህ ጥናት ቃሉዎች እና ቃልቻዎች ብልጭታዎች ናቸዉ።
ቃሉ ሆነ ቃልቻ ኣንድም ሰዉ ኣጋጥሞኝ ኣነጋግሬ ባላዉቅም ዕዉቀታቸዉ በብዛት ግምታዊ ይመስለኛል። ለመመለስ ኣስቸጋሪ የሚሆነዉ ጥያቄ ያላቸዉ ዕዉቀት ሁሉም ግምታዊ ነዉ ወይ የሚለዉ ነዉ።
ቃሉ ባይሆንም ኣንድ ወቅት የተገናኘን የቦረና ወግ ኣዋቂ እና ጠባቂ ነዉ የተባለ ሰዉ ከተናገራቸዉ ዉስጥ ኣንዱ ገና እንደሰማሁኝ ያሳመነኝ የሚከተለዉ ነዉ።
ነምን ህን ሶባ፣ ኡርጂን ህን ሶቡ። ሰዉ ይዋሻል፣ ኮከብ ኣይዋሽም ማለት ነዉ።
በእኔ አስተሳሰብ ይህ አባባል ብቻ ለሁለተኛዉ ሬይነሳንስ ኣንድ የመሠረት ድንጋይን ይጥላል።
በተለያዩ ቋንቋዎች ሆነ እንጂ ኣንተ የምትለዉ የጥንት ግዜ ኢትዮጲስ ሆነ ቦረና የሚለዉ የጥንት ግዜ የቦረና ወግ የኣንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታዎች ናቸዉ ብዬ ኣስባለሁ። ቃሉ እና ቃልቻም እንደዛዉ ነዉ።
የቦረና ወግ ብለዉ ዋቀ የሚሉት ምናልባትም ሳይንሳዊ ጥናት ያላደረጉ ምሁራን ኣሁን ባይኖራቸዉም የሁለተኛዉ ሬይነሳንስ ፍሪሜሶኖች መሆን ይችሉ ይሆናል።
ይህ ጥናት ስለ ጥንት ታሪካችን ብሔራዊ ግንዛቤን የምያበለጽግ ይመስለኛል።
በዚህ ዘመን ያሉ ቃሉዎች እና ቃልቻዎች ካሉ ወይም ቃሎቻቸዉ የሚታወሱ ካሉ ልሂቃኖች ብያጠኑዋቸዉ ግምቶችን እና ክስተቶችን ማበጠር የሚችሉ ይመስለኛል።
ለምሳሌ ስምንተኛዉ ሺህ ምን ላይ የተመሠረተ ነበር? እጆችዋን ትዘረጋለች የተባለዉ ትንቢት ምን ላይ የተመሠረተ ነበር? ተፈጸመ ማለት ኣሳማኝ ከሆነ ከመለኮታዊ አሰራር ጥልቀት በላይ የሆነ ምን የምያሳምን ሊገኝ ይችላል?