"ኢትዮጵያ የአረብ ሊግ አባል ብትሆን በመድረኩ የሚሸረብ ሴራን ለመቋቋም ይጠቅማታል" - አምባሳደር ዲና ሙፍቲ
Posted: 18 Aug 2025, 19:16
The desperation in the crumbling PP camp is becoming more ridiculous as the days go by! So after all "our historical enemies" narratives, the child king wants to join the Arab League! Just last week, his communications minister declared that their journey to Assab has reached the half-point! አረ ጌና፤ እንደ ድመት ኛው ኛው ልትሉ ነው።
https://www.facebook.com/share/p/1BTq5r8LwZ/
ኢትዮጵያ የአረብ ሊግ አባል ብትሆን መድረኩን ተጠቅመው ከኢትዮጵያ ብሄራዊ ጥቅምና ህልውና በተቃራኒ የሚሰሩ አካላትን ለመሞገትና ሴራዎችንም ለማክሸፍ ይጠቅማታል ሲሉ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውጭ ግንኙነትና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባል አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ገለጹ።
አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ኢትዮጵያ ከአፍሪካ ሀገራት ጋር ያላትን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት በሚመለከት ለጋዜጣ ፕላስ በሰጡት ማብራሪያ እንደገለጹት፤ ኢትዮጵያ የአረብ ሊግ አባል ብትሆን ያለንን መልከአምድራዊ፣ ታሪካዊ እና ባህላዊ እንዲሁም ኢኮኖሚያዊ ግንኙነት በማጠናከር ወደላቀ ደረጃ ለማሸጋገር ትልቅ ጠቀሜታ ይኖረዋል።
ግብጽ በተደጋጋሚ የታላቁ ህዳሴ ግድብን በተሳሳተ መንገድ ለአረብ ሊግ አባላት በማቅረብ የተሳሳተ ግንዛቤ እንዲያዝ ስታደርግ የቆየችውም ኢትዮጵያ አባል ሀገር ባለመሆኗ መሆኑን ጠቅሰው፣ አባል ብትሆን በወቅቱ ትክክለኛ መረጃ ለመስጠት እንደሚያስችላትም ጠቁመዋል።
ጎረቤት ሀገራት በሙሉ ሱዳን፣ ሱማሊና ጅቡቲ የአረብ ሊግ አባል መሆናቸውን እና ኤርትራም ታዛቢ መሆኗንም አምባሳደር ዲና ገልጸዋል።
የአረብ ሊግ አባል ሀገራት ከፍተኛ ሀብትም እንዳላቸው ገልጸው፤ ከነሱ ጋር ንግድን ለማጠናከር እና በአጠቃላይ በመድረኩ ስለኢትዮጵያ በጎ ድምጽ እንዲኖር ማድረግ እንደሚቻል አመላክተዋል።
በዓለምአቀፍ ግንኙነት ሁሉም ቦታ መገኘት ቢቻል ጥሩ ነው ያሉት አምባሳደሩ፤ እንኳን ቅርባችን ካለ የአረብ ሊግ ይቅርና ሩቅ ቦታ ካለ ተቋም ውስጥ መገኘት ብንችል ብሔራዊ ጥቅምን ማስከበር ነው ብለዋል።
ኢትዮጵያ የአባልነት ጥያቄዋ እንዲሰካ አባል ሀገራትን ማሳመን እና የብሪክስ አባል ለመሆን የተደረገውን ጥረት በዚህም መድገም እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
https://www.facebook.com/share/p/1BTq5r8LwZ/









