Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Naga Tuma
Member+
Posts: 6753
Joined: 24 Apr 2007, 00:27

ጋላ ገዳይ ስለተባለዉ ቡድን ወይም ድርጅት ዮሓንስ ለታ የምያዉቀዉ ኣለ?

Post by Naga Tuma » 16 Aug 2025, 00:08

የደርግ መንግስት ከወደቀ በኋላ ጋላ ገዳይ የተባለ ቡድን ወይም ድርጅት ተቋቋመ የሚባል ወሬ ይወራ ነበር።

በኢትዮጵያ የምሽነሪዎች ትምህርት ላይ የተመሠረተ ትምህርት ተምሯል ብዬ የምገምተዉ ዮሓንስ ለታ የሽግግር መንግስት ዉስጥ ሚና የነበረዉ መሆኑ በዜና ይሰማ ነበር።

ኦሮሞን እወክላለሁ ብሎ ጋላ ገዳይ ስለተባለዉ ቡድን ወይም ድርጅት ምንነት ሳይጠይቅ የቀረ ኣይመስለኝም።

ጠይቆ ከሆነ ስለ ቡድኑ ወይም ድርጅት የምያዉቀዉ ወይም የደረሰበት ኣለ?

ተወዳጅ ከሆኑት የአብተዉ ከበደ ፉፋ ዘፈኖች ዉስጥ ኣንዱ ሹሩቤን ህን ቃርቴ የሚል ዉስጥ “ሃ ታኡ ካ ዸለ እሳፎ” የሚል ስንኝ ኣለ።

በዚህ ስንኝ ምን ማለቱ ነበር?

ከብዙ ዐመታት በኋላ ሉበ አብተዉ ከበደ ፉፋ ሆኖ ብቅ ብሎ ሲዘምር “ጨጨብሴ” ይላል። ምን ማለቱ ነዉ?

“ዱረቱ መቃ ኑ እረ ቱለኒ” በሚለዉ ዘፈኑም ተወዳጅ የነበረዉ አብተዉ ከበደ ፉፋ በገዳ ስርዓት ኣርባ ዐመታትን የምያስፈልግ ሂደት ዉስጥ ሳያልፍ ምንድነዉ በአቋራጭ ሉበ ያስባለዉ? እግዝኣብሔር ስያናግረዉ ኖረ ማለት ነዉ?

Naga Tuma
Member+
Posts: 6753
Joined: 24 Apr 2007, 00:27

Re: ጋላ ገዳይ ስለተባለዉ ቡድን ወይም ድርጅት ዮሓንስ ለታ የምያዉቀዉ ኣለ?

Post by Naga Tuma » 04 Sep 2025, 00:59

ገተተ በትለር ሀራሙ ወለጋ ዮሓንስ ለታ፥

ህወሓት ኢትዮጵያ ዉስጥ ስልጣን ላይ ከወጣ በኋላ ኣንተ ለኦሮሞ ሕዝብ መብት የህወሓት ተቃዋሚ ነኝ ብለህ በአደባባይ ስትንቀሳቀስ የነበረ ዘመን ህወሓትን በመቃወም እንታገላለን ብለዉ ብዙዎች ተነስተዉ ነበር።

ተነስተዉ ከነበሩት ዉስጥ ብዙዎች ህይወታቸዉ ኣልፏል። ከቤት ወጥተዉ ድምጻቸዉ ፈጽሞ ስላልተሰማ ህይወታቸዉ ኣልፎ መሆን ኣለበት ተብለዉ የተደመደሙ ኣንድ ሁለት የሚባሉ ኣይዴሉም።

ከነዚህ ዉስጥ በቀለ አበበ ኣንዱ ነዉ።

ሌሎች ዘመዶቻቸዉ ኣፈላልገዉ ተናግሮላቸዉ ድምዳሜ ላይ ደርሰዉ ከሆነ ኣላዉቅም።

በቀለ አበበ በአካል የማዉቀዉ የቅርብ ዘመዴ ነዉ። ሞቶ ከሆነ አሟሟቱን እና የት እና እንዴት እንደተቀበረ ዛሬ ድረስ ኣላዉቅም።

ሞት ያለ ነዉ። ዺር ጋፈ ዸለቴ ዱቴ ማለት ጀግና የሞተ ዕለት ተወለደ ማለት ነዉ።

የኦሮሞ ሕዝብ መብት ተከራካሪ ነኝ ስትል ስለኖርክ ሞቶ ከሆነ እንዴት እንደሞተ እና የት እንደተቀበረ የምታዉቀዉ ኣለህ?

የፖለትካ ሳይንስ ፕሮፌሰር መረራ ጉድና ስለ በቀለ አበበ አሟሟት እና የት እንደተቀበረ የምያዉቀዉ ይኖር ይሆን?

ሰዉ ኣስገድሎት ከሆነ አባትን ኣስገድሎ፣ ልጆቹን እየሱስ በሉ ብሎ፣ በዚህ እኩይ ተግባሩ እ አ አ በ1995 ወይም በ2005 ወይም በ2015 ሳይሆን በ2025 ጀግና ነኝ ብሎ የሚመጻደቅ በሰዉ ልጅ ታሪክ ዉስጥ የሚታወቅ ሰዉ ካለ ታዉቃለህ? የት ሃገር የተወለደ ይሆን?

የወለጋ ክፍለ ሃገር የመጀመርያዉ አስተዳዳሪ ነበረ የተባለዉ እና ወንድ ልጁን በለጋ ዕድሜዉ ያጣዉ ፊታዉራሪ እብሳ ጉታ ወለጋ ዉስጥ አባትን ኣስገድሎ ልጆቹን እየሱስ በሉ የሚል እኩይ ተግባር ፈጽማችሁ ጀግና ነኝ በሉ ብሎ ኣስተምሯል?

Post Reply