Page 1 of 1

ግምታዊ መለኮታዊ ጎህ በፍጥረት በር፥ ቁጥር 3 (ጥያቄ ቁጥር 2)

Posted: 12 Aug 2025, 10:59
by Naga Tuma
መለኮት ሁለት ዕዉቀት የምያንሳቸዉን ሰዎች ቢጸምድ ምን ለማስተማር ነዉ?

Re: ግምታዊ መለኮታዊ ጎህ በፍጥረት በር፥ ቁጥር 3 (ጥያቄ ቁጥር 2)

Posted: 09 Dec 2025, 19:16
by Naga Tuma
ሁለት ዕዉቀት የምያንሳቸዉን ሰዎች የጸመደዉ መለኮት ኣንዱን ጩቤ እጨብጣለሁ እንጂ ኣዲሱ ኪዳኑ እንደገና ኣይጻፍም ብያስብል እና ሌላዉን ኪዳነ ዘላለም ብሎ ብያስምል ምን ለማስተማር ነዉ?

የትራይባል ፓለቲከኞች ግምት ለዘላለም አድዋ አትቀየርም

Re: ግምታዊ መለኮታዊ ጎህ በፍጥረት በር፥ ቁጥር 3 (ጥያቄ ቁጥር 2)

Posted: 29 Jan 2026, 21:51
by Naga Tuma
ይህን ርዕስ ስጀምር መገባደጃዉ ሁለቱም ታቦት ጣዖት ነዉ ማለት ላይ ይስማማሉ ብዬ ፍጹም ኣልገመትኩም፣ ኣልጠበኩም።

ይህ ጽምዶ መለኮታዊነት ነበረዉ ከተባለ ይህ መገባደጃ ለምን እንደነበረ ግልጽ ያደርገዋል። ለእኔ እንደገባኝ ከሆነ።

Re: ግምታዊ መለኮታዊ ጎህ በፍጥረት በር፥ ቁጥር 3 (ጥያቄ ቁጥር 2)

Posted: 30 Jan 2026, 03:29
by Naga Tuma
ታቦት ጣዖት ነዉ ማለት ኢትዮጵያን በኣንዲት ሰይፍ ከመሠረቷ መቁረጥ ማለት ነዉ።

በአደዋ ማግስት ኢትዮጵያ መጤ ሆነዉ የፕሮቴስታንት ሃይማኖት ያስተማሩት ኢትዮጵያዊ ኣድጎ ታቦት ጣዖት ነዉ ቢል ብዙ ላይደንቅ ይችላል።

የታወቀ የአሜሪካ ዩኒቨርዚቲ የተማረ ኢትዮጵያዊ ታቦት እንደ ጣዖት ነዉ ብሎ ኣብሮ ጮቤ መርገጥ እጅግ ኣስደንጋጭ ነዉ። ኣይዴለም?

Re: ግምታዊ መለኮታዊ ጎህ በፍጥረት በር፥ ቁጥር 3 (ጥያቄ ቁጥር 2)

Posted: 11 Feb 2026, 20:59
by Naga Tuma

እስከዛሬ ድረስ ይህ በድብቅ የኖረ ቡድን በእየሱስ እንደማያምን ኣላዉቅም ነበር።

በአስርቱ ትዕዛዛት የምያምንን የማይቀበል መሆኑንም ኣላዉቅም።

በአስርቱ ትዕዛዛት ማመንን የሚቀበል ከሆነ ታቦት ጣዖት ነዉ የማይል ይሆናል ማለት ነዉ።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ሃይማኖት ታቦት ተሸካሚ እና ጠባቂ ከሆነ፣ ኣዉሮፓዊ ታቦት ጣዖት ነዉ የማይል ከሆነ፣ ታቦት ጣዖት ነዉ የሚል ኢትዮጵያዊ ምንድነዉ?

እንደሚሽነሪ ኢትዮጵያ የተላኩትን እነ በትለርን እና እነ ብሩስን ፍሪሜሶኖች የማያዉቁ እንደነበረ ይታወቃል?

የምያዉቁ የነበረ ከሆነ እነሱ በማያምኑበት በምሽነሪ የተማሩ ኢትዮጵያዊያን ለማመን ሲዳረጉ ተመልካቾች ነበሩ ማለት ይሆናል።

Re: ግምታዊ መለኮታዊ ጎህ በፍጥረት በር፥ ቁጥር 3 (ጥያቄ ቁጥር 2)

Posted: 13 Feb 2026, 15:29
by Naga Tuma
እንደ ኣንድ ግለሰብ ማሰላሰል የጀመርኩኝ እያደረ ኣሳማኝ እየሆነ ይመስለኛል።

ይህ ርዕስ ብቻዉን ላለፉት 18 ዓመታት ገደማ ያህል የኢትዮጵያ ፖለትካ ሂደትን ማንጸባረቅ የሚችል ይመስለኛል።

ለዚህ የታሪክ መስታወት የሶስት ግለሰቦችን ያለፉት 18 ዓመታት ገደማ ኣስተሳሰብን ማጥናት በቂ ነዉ ማለት ይቻላል።

እነዚህ ግለሰቦች ሆረስ፣ ሰሚራ ወይም ምስራቅ፣ እና ነጋ ቱማ ናቸዉ።

የሶስቱም ግለሰቦች ስለ ኣንድ ሃገራቸዉ አስተያየቶች ለየብቻ የነበሩ ናቸዉ።

እኔ ሁለቱንም ግለሰቦች የማስታዉሰዉ እዚህ መድረክ ላይ ምሁራንን ሳፈላልግ የነበረ ግዜ ነዉ። በአካል የማላዉቃቸዉ በሚጽፉት ብቻ ለቁምነገር መወያየት እንችላለን ብዬ ከቆጠርኩዋቸዉ ዉስጥ ነበሩ።

ሁለቱም በክብር ለማወያየት የሞከርኩኝን በቁምነገር የመወያየት ችሎታቸዉን ታዝቤ እና ኣዝኜ የተዉኳቸዉ ነበሩ።

እኔ ያኔ የነበረኝ ቁምነገር ከዛሬ የተለየ ኣይዴለም።

ስለ ስደት ታሪክ ኣጥንቼ በቁምነገር መወያየት ኣስፈላጊ ነዉ ማለት ያሳመነኝ ሰዉ ነበርኩ። ኣሁንም ያዉ ሰዉ ነኝ።

ሁለቱም ኣዲስ ኪዳን ዉስጥ የተጻፈን ትክክለኛነት መጠየቅ እንደ ሃጥዓት የሚቆጥሩ ብቻ ሳይሆኑ የጠየቀ ላይ የሚዘምቱ ነበሩ።

ከተሳሳትኩኝ ሁለቱም እኛም ጠይቀን ነበር ብለዉ ልያርሙኝ ይችላሉ።

ታዝቤኣቸዉ ትቻቸዉ ዓመታት ካለፉ በኋላ ሰሚራ ወይም ምስራቅ እዚሁ መድረክ ላይ ፕሮፌሰር ኣለኝ።

እኔ ፕሮፌሰር ኣይዴለሁም። መሆኑን በልጅነቴ የተገመተ እና የተመኘሁት ነበረ።

ሆረስ ደግሞ ከብዙ ዓመታት በኋላ እዚሁ መድረክ ላይ ፕሮፌት፣ ፀረ ክርስትያን፣ ኣንቲ ሴሜትክ ብሎኛል።

እኔ ፕሮፌት መሆን ቀርቶ ስለመለኮታዊ ነገር ሆነ ብዬ ያላጠናሁ ሰዉ ነኝ።

ከክርስትና በፊት የነበረዉ የስደት ታሪክ ተጠንቶ ይታረም ማለት ፀረ ክርስትያን እና ኣንቲ ሴሜትክ የምያደርግ መሆኑን ሆረስ ዬት ትምህርት ቤት እንደተማረ ኣላዉቅም።

በዚህ 18 ዓመታት ዉስጥ ሆረስ እና ምስራቅ ስለ ኢትዮጵያ ፖለትካ ሲከራከሩ የኖሩት ዱላ ቀረሽ ዐይነት የነበረ መሆኑን ምስራቅ እራሱ ምስክር ሆኗል።

የሁለቱን ክርክር ኣስተዉዬ ብዙ ምሁራን የሌላት ሃገር ጉዳይ ሁለታችሁ መከራከር ትታችሁ ኣብራችሁ ለሃገር እንድትለፉ እኔ የእናንተ ታነሽ እናንተን መምከር ኣለብኝ ወይ ብዬ በጥያቄ መክሬኣቸዋለሁ።

ይህ ሁሉ ዉስጥ ታልፎ ሁለቱም የፕሮቴስታንት ሃይማኖት ተቀበል ባይ ሰባኪዎች ሆኑ።

እኔ ከወጣትነት ግዜዬ ጀምሮ ይህን ሰበካ ሁለመናዬ ያልተቀበለዉ ብቻ ሳይሆን፣ ይህን መጤ ድርጅት እንደ ሃይማኖት የማልቆጥረዉ፣ በወጣትነቴ የቤተሰብ አባልን ለማስተዉ በርካታ ግዜዎችን በክርክር ያጠፋሁ ሰዉ ነኝ።

የፕሮቴስታንት ሃይማኖት ተቀበል ባይ ሰባኪዎች ከስብከታቸዉ ኣልፈዉ የኢትዮጵያ ታቦት ጣዖት ነዉ ኣሉ።

ኣወቅሽ ኣወቅሽ ቢሏት መጽሓፍ ኣጠበች እንደተባለዉ ኣወቅን ኣወቅን ብለዉ ጥንታዊት ኢትዮጵያ ዉስጥ ጥንታዊ መሠረት ያለዉ የኢትዮጵያ ታቦት ጣዖት ነዉ ኣሉ።

ኢትዮጵያ ዉስጥ ተወልዶ ኣድጎ የኖረ የኢትዮጵያ ሰዉ ቀርቶ የኢትዮጵያ ጦጣ የኢትዮጵያን ታቦት ክብር ታዉቃለች።

ይህ ሁሉ ማለት ላለፉት 18 ዓመታት ገደማ ሶስታችንም ለሃገራችን የምንናገር ነን የምንል በሃገር ጉዳይ ላይ መስማማት ኣልቻልንም ማለት ነዉ።

የምሁርነት ዕዉቀት እንደምያንሳቸዉ ከ18 ዓመታት ገደማ በፊት ታዝቤ እና ኣዝኜ ያለፍኩዋቸዉ ታቦት ጣዖት ነዉ ማለታቸዉ ትዝብቴን ከዚህ ሁሉ ዓመታት በኋላ ጉልህ ኣድርገዉታል።

በዚህ ግዜ ዉስጥ ሁለቱም ለሃገር ብለዉ የለፉትን ብቀንስባቸዉ ግፍ ይሆንብኛል።

ይሁን እንጂ በየዘመናቱ መሪዎችን እየወለደች እና እየገበረች የኖረች ሃገር በእራስዋ ልጆች ንዝህላልነት ስትንገዳገድ ሃጥዓት ነዉ ማለት ኣለመቻል እራሱ ሌላ ሃጥዓትን መፈጸም ነዉ።

የሃገር ጥንታዊ መሠረት የሆነን የሃገርን ጥንታዊ መሪ፣ ታላቁ ፈረዖ አክናተን፣ ቃላት ተሸካሚ እና ጠባቂ የኢትዮጵያ ታቦትን ጣዖት ማለት የበለጠ መሃይምነት፣ ባንዳነት፣ እና እብደት ዬለም።

ጥንታዊነቱ ተጠንቶ ታድሶ ይደግ ማለት ቁምነገር ነዉ። ሃገር ከጥንታዊ መሠረት በኣንዲት ሰይፍ ትገነዝ ማላት ምንድነዉ?

እኔ ላለፉት 33 ዓመታት ገደማ ቤተክርስትያን ሄጄ የማላዉቅ ያለ መለኮታዊ አሰራር ይህ ሁሉ ሊሆን የሚችል ኣይመስለኝም።

ስለዚህ ስለመለኮታዊ አሰራር ዕዉቀቱ ያላችሁ እዚህ ዉስጥ መለኮታዊ ምልክት ዬለም ማለት ትችላላችሁ?

ሌላ ኣዲስ ነገር ወደዚህ ርዕስ ካልመለሰኝ በእኔ አስተሳሰብ ይህም ግምት ከስህተትነቱ ዕዉነትነቱ ያየለ ሆኖ ተገባዷል።