ዶክተር ኢትዮጵያ፣ ዶክተር ቦረና፣ ዶክተር ኦሮሞ፥ ስህተት ያልሆኑት የትኞቹ አባባሎች ናቸዉ?
Posted: 06 Aug 2025, 21:59
ካልዘነጋሁ ኢትዮጵያ እያለሁኝ ነበር የአሜሪካዉ ዶክተር ኒዉተን ግንግሪች ተናገረ ተብሎ ታይም መጽሔት ዉስጥ የታተመዉን ያነበብኩኝ።
ቃል በቃል ባላስታዉሰዉም በመጽሔቱ ዉስጥ የታተመዉ መልዕክቱ የሚከተለዉ ነዉ።
“One who can’t read the degree one holds is not going to lead anyone.” (Paraphrased.)
በደንብ ላጤነዉ ለዐለም ኣቀፍ ኣንባብያን የታተመዉ መልዕክት ቅስም ሰባሪ ነዉ።
በእኔ አስተያየት የትኛዉም ኢትዮጵያዊ ዶክተር ዉስጡ ያለችን ኦኔ ተባለ ወኔ ለኳሽ መልዕክት ነዉ።
እዚህ ዶክተር ያልኩኝ የፒ ኤች ዲ ድግሪ ያለዉ ኢትዮጵያዊን በሙሉ ነዉ።
ሁላቸዉም በእጁ የያዘዉን ድግሪ ማንበብ የማይችል የሚል ዘለፋ ምን ማለት ነዉ ብሎ መጠየቅ እና ለማወቅ መጣር ኣለበት።
የቤልጀም ፖልሲ በኮንጎ ታሪክ ጥናት ፒ ኤች ዲ ድግሪ ያለዉ ኒዉተን ግንግሪች የያዘዉን ድህሪ ማንበብ የማይችል ያለዉ ምን ማለቱ እንደሆነ የምያዉቀዉ እሱ ነዉ።
ያነበቡት ምን ማለቱ እንደሆነ መገመት ይችላሉ።
ኣንድ የታወቀ የምሁራን ብልህነት ማንም ሰዉ ለስህተት መብት ዬለዉም የሚል ነዉ።
ይህ ብልህነት ሰዉ ኣይሳሳትም ሳይሆን ሰዉ ስህተቱን ማረም እንደኣለበት ይመክራል። ወጣት ሳይሆን ጎልማሳ የሆነ ሰዉ እንደሌለ ሁሉ ሳይሳሳት ዕድሜ ልኩን የኖረ ሰዉ ያለ ኣይመስለኝም።
የእኔ ጥረት ሳይንሳዊ አስተሳሰብ እና እንዲህ ያለ ምሁራዊ ብልህነት ኢትዮጵያ ዉስጥ ስር እንዲሰዱ የተቻለዉን አስተዋፅ ኦ ማድረግ ነዉ።
ከርቀት ሆኜ ሳነብ እና ሳሰላስል ኢትዮጵያ ለሳይንሳዊ አስተሳሰብ እና ምሁራዊ ብልህነት ስር መስደድ ኣቅጣጫ እያሳየች ያለች ይመስለኛል።
ለዚህ ደግሞ የዉስጣዊ ፖለትካ ፉክክር ወደ ታሪክ መዝገብ እያዘገመ ሃገራዊ እና ብሔራዊ ዉይይቶች እየበረከቱ የሚመጡ ይመስለኛል።
ቃልቻ ቃሉን ቅኝ ስለገዛ ቃሉ ከቃልቻ ነፃነት ማግኘት ኣለበት ዐይነት ክርክሮች፣ የዘመኑ ወዶ ገብ የአሜሪካ ድርጅት በግ አፍ ኣለኝ ብላ ከሃገር ዉጪ አፍ መክፈት የታሪክ መዝገብ የማይረሳቸዉ ናቸዉ።
የኢትዮጵያ ዶክተሮች በሙሉም የታሪክ መዝገብ ዉስጥ ተገቢ ስፍራዎች እንዲኖራቸዉ ተነስተዉ የኒዉተን ግንግሪች ዘለፋን በጥልቁ ማጤን ይጠነቅባቸዋል ብዬ ኣስባለሁ።
ለምሳሌ ማንም ሰዉ ለስህተት መብት ዬለዉም ከሚለዉ ምሁራዊ ብልህነት ተነስተን በርዕሱ ዉስጥ ከጠቀስኩኝ አባባሎች ዉስጥ ስህተት ያልሆኑት የትኞቹ ናቸዉ ብለን መጠየቅ እንችላለን።
ኢትዮጵያ ማለት የታወቀች ሃገር ስለሆነች ዶክተር ኢትዮጵያ ወይም ኢትዮጵያዊ ዶክተር ማለት ስህተት ያለዉ ኣይመስለኝም።
ቦረናም ቢሆን ጎሳ ሆነ ስፍራ ለረጅም ግዜ የታወቀ ስለሆነ ዶክተር ቦረና ወይም የቦረና ዶክተር ማለትም ስህተት ያለዉ ኣይመስለኝም።
ዶክተር ኦሮሞ ሲባል ስህተት እንዳለዉ እና እንደሌለዉ በቀላሉ ማወቅ የሚቻለዉ ቦረና ከኦሮሞ ተወለደ ወይስ ኦሮሞ ከቦረና ተወለደ የሚለዉን ጥያቄ በትክክል በመመለስ ነዉ።
ማንኛዉም ፒ ኤች ዲ ድግሪ ኣለኝ የሚል ኢትዮጵያዊ ይህን ጥያቄ በትክክል ሳይመልስ ዶክተር ኦሮሞ ካለ ኒዉተን ግንግሪች የያዘዉን ድግሪ ማንበብ የማይችል ለተባለዉ በቂ ምሳሌ ኣይዴለም?
ኦሮሞ ማለት እና ኦሮምኛ ተናጋሪ ማለት ልዩነታቸዉ ግልጽ ያልሆነለት ሰዉ ጥያቄዉን በቀላሉ ለመመለስ እንደሚከብደዉ እገምታለሁ። ማስተዋሉ ጥልቅ ጥናት እንደምያስፈልገዉ እገነዘባለሁ።
ኦሮምኛ ተብሎ የታወቀዉ ቋንቋ ጥንታዊ እና ቃላቱ ሌሎች ቋንቋዎች ዉስጥ የሚገኝ ነዉ። ለምሳሌ ከአማርኛ እና ትግርኛ ቋንቋዎች ኣልፎ እንግሊዘኛ ዉስጥ ይገኛሉ። ቢሆንም እንግሊዘኛ ተናጋሪዉ ኦሮሞ ነበርኩ ብሎ ነበር የሚል ሰምቼ ኣላዉቅም።
ሴቄ፣ ፈይሴ፣ ዌድሴ ባይ ኦሮሞ ነኝ ካለ ሳቀ፣ ፈወሰ፣ ወደሰ የሚለም ለምንድነዉ ኦሮሞ ነኝ ያላለዉ?
ሀረርጌ ዉስጥ እ ኣ አ እስከ 1991 ድረስ ሙስሊሞች ተብለን እንታወቅ ነበር እንጂ ኦሮሞዎች ተብለን ኣንታወቅም ነበር ያሉ ሰዎችን ሰምቻለሁ።
ከዛ በኋላም ኣንድ ዩኒቨርዚቲ የገባ የአርሲ ተማሪ ከየትኛዉ ሕዝብ እንደመጣ ሲጠየቅ ኦሮሞ ማለትን ባለማወቁ እና ጎሳዉን በመናገር መመለሱ የማያዉቅ ነዉ ተብሎ ሲሳቅበት ታዝቤኣለሁ።
የሶሻል ሳይንስ ተማሪ ባልሆንም በልጅነቴ ኦሮምኛ ተናጋሪዎች ኦሮሞ ሳይሆን በሌሎች ጎሳዎች ስም ሲጠሩ እንደኖሩ ኣስታዉሳለሁ።
ኦሮሞ ማለት እና ኦሮምኛ ተናጋሪ ማለት ልዩነት እንዳላቸዉ ማሰላሰል እና ቀድሞ የተስተዋሉትን ማስታወስ ስለ ኢትዮጵያ ሕዝብ ጎሳዎች የኢትዮጵያ ኣርሶ ኣደሮች ዕዉቀት ከብዙ የኢትዮጵያ ዶክተሮች የሚበልጥ መሆኑን ኣለማድነቅ ኣይቻልም።
ከኦነግ በፊት የተመሠረተዉ መጫ እና ቱለማ ይህን ጠንቅቆ ብያዉቅ ነዉ ስሙን ይዞ የሰነበተዉ?
ኦሮሞ የተወለደዉ ከቦረና ነዉ ከተባለ የቦረና ጎሳ ነኝ ማለት የሚችል እንጂ ከዚህ ኦሮሞ የተባለ ጎሳ ነኝ ማለት የሚችል ዶክተር ኦሮሞ ለምስክርነት ማግኘት ይቻላል?
እነዚህ ጥያቄዎች ለሃገራዊ እና ብሔራዊ ዉይይት እና መግባባት ጠቃሚ ናቸዉ ብዬ ኣስባለሁ። ኣይዴሉም የሚትሉ ዶክተሮች ካላችሁ እስቲ ፍልስፍናችሁን ሰምተን ኣጥንተን እንወቀዉ።