Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
DefendTheTruth
Senior Member
Posts: 12878
Joined: 08 Mar 2014, 16:32

በጌን የበላ ሌባ፣ ራሱ ይንጫጫል ና እናንተ ዝም በሉ ብቻ፣ አለ አንደ መላ አዋቂ ።

Post by DefendTheTruth » 03 Aug 2025, 03:47

በግ ተሰረቀ ና በአፋን ኦሮሞ አዉጫጪኚ የምባል የሕዝብ ስብሰባ ተጠረ፤ ሌባዉን ለማጋለጥ። በዚህን ጊዜ የበጉ በለቤት በተጠረዉ የሕዝብ ስብሰባ ላይ ብድግ ብሎ፣ በጌን የበላ ራሱ ይንጫጫል ና እናንተ ዝም በሉ ብሎ ለተሰብሰቢዉ ይናገራል። ይህን የሰማ ሌባ ደግሞ ብድግ ይል ና ታዲያ እኔ መች ተንጫጫሁ ብሎ በጥያቄ የበጉን በላቤት አፋጣጠሁ ይባላል። ታዲያ የተሰበሰብዉም ሕዝብ፣ እናመሰግናለን፣ ራስህን ስላጋለጥክ ና ሌላ ድካም ስላቃለልክልን ብሎ ሌባዉን ጋማዉን ይዞ ወደ ሕግ አቀረቡት ና ስብሰባዉ ተቋጫ፣ ይባላል።

ይህን እኩዪ የሆነ ልጅ መስማት ና ማንበብ ሰልችቶኛል፣ ፅሑፍ ግን ያጋጥሙኛል፣ ሰዎች ወዲያ ወዲህ ስለምቀባበሉት መሰለኝ።

በቀደም እንደምከተለዉ ብሎ ፅፎ ነበር፣ ተደነቁኝ፣ ይህ ጋጠወጥ እንዴት የኢትዮጵያን ሕዝብ እንደ ሕዝብ ብንቅ ነዉ ይህን የመሰለ ተልካሻ መልዕክት እንተርኔት ላይ የምለጥፈዉ፣ የህ ጉዳይ የአብይ ጉዳይ አይደልም፣ የኢትዮጵያ ሕዝብ ጉዳይ እንጂ። የራስን ዕድል በራስ የመወሰን ና የሉዓላዊነት መግለጫ ነዉ። መሪያቸዉን ከፈለጉ ማዉጣት ና ማዉረድ ሳይችሉ፣ ሉዓላዊ ነን ማለት አይቻልም። ይህ ክፍት አፍ ልጅ ሌላ አካል በቶሎ ደርሶ መሪያቸዉን ስፈልግ ልያወጣላቸዉ ና ስፍለግ ደግሞ ልያወርድላቸዉ ነዉ ብሎን በጉጉት እንድንጠብቀዉ በአደባባይ ለፈፈልን፣ ያላንዳች እፍረት። አፈርኩኝ በሱ ቦታ።

ታዲያ አለቆቹ (ላኪዎቹ) ያልከዉ ነገር ከሕዝቡ ጋር ነዉ የያጋጫን ብሎት ነዉ መሰለኝ በንጋታዉ ተመለሰ ና መስታባቢያ የምመስል ምናጫጭር ለጥፎ ሄደ። ድኩማን የሆንክ እኪዪ! እፍረት አልፈጠረብህም። የአሜሪካ መንግስት መሪ ለኢሳያስ አፈወርቂ ደብዳቤ በመፃፉ ነዉ፣ እንደዚያ የፈንደቅኩት ና ኢትዮጵያ ዉስት የመንግስት ለዉጥ በጣም ከጠበቅነዉ በላይ በፍጥነት አየመጣ ነዉ ብዬ የለጠፍኩት ለማለት ዳዳዉ።
ቅሌታም!
Change is coming, and its coming fast. We must speed up preparation to successufully manage the transition. Its literally a race against time.
on 02.08.2025 (GC).

literally a race against time? "l*ick my ar$h in public now, you have no other choice!
Please wait, video is loading...
ሌላ መደበቂያ ስላጣ እንዲህም ብዬ ነበር ለማለት ደግሞ ይህኘዉን ሞናጫጭሩን በአፋን ኦሮሞ ብቻ ሞነጫጭሮት ሄደ።
ዉርደታም!
Please wait, video is loading...

DefendTheTruth
Senior Member
Posts: 12878
Joined: 08 Mar 2014, 16:32

Re: በጌን የበላ ሌባ፣ ራሱ ይንጫጫል ና እናንተ ዝም በሉ ብቻ፣ አለ አንደ መላ አዋቂ ።

Post by DefendTheTruth » 03 Aug 2025, 15:14

አንድ ሰዉ እንዴት ብያስብ ና ምን ብያስብ ነዉ፣ እንዲህ አይነት ምልከታ በአንድ አገር ሕዝብ ላይ የምነዘዉ? አብይ አህመድን አይደለም የናቀዉ መላዉ የኢትዮጵያ ሕዝብን ና ሉዓላዊነታቸዉን እንጂ። ለዉጥ በፍጥነት እየመጣ ስለሆነ፣ እኛም በፍጥነት ለሽግግር እንዘጋጅ ብሎን አረፈ። ለዉጡን የምያመጣዉ ማን ነዉ የምለዉን ጥያቄ ሆን ብሎ አልመለሰም። የልመለሰበት ምክንያት ደግሞ እሱ ወይም ሌላ አካል ከአገር ዉስጥ ተነስቶ ለዉጥ ልያመጣ እንዳማይችል እንኳን እሱ መላዉ አለም ያዉቃል። ለዚህ ነዉ የልደፈረዉ። አቅሙን እንደሌላዉ ያዉቃል። ድሮ ገና ይህን ሐቅ ተገንዝቦ ነዉ፣ ተንደርድሮ እንደገባ ሁሉ ተንደርድሮ ደግሞ ሸሸ፣ ለሁለተኛ ጊዜ። ለሁለት ጊዜ ከኢትዮጵያ የኮበለለ ካዲ ምን ጊዜም ኢትዮጵያ ላይ ስልጣን መያዝ አይችልም። የሱ ጉዳይ አልቆዋል። እያጭበረበረ ከመንጋዉ ስሙኒዉን እየለቀመ መኖር ለተወሰን ጊዜ ይችል ይሆናል።

በዚህ ሞነጫጭሩ ልንገርን የፈለገዉ የዉጪ አካል የኢትዮጵያን መንግስት ልያወርድልኝ ነዉ ና፤ ለዚያዉም በፍጥነት፣ ቶሎ ብላቸዉ እኔን ለመሪነት አዘጋጁኝ የምል ሳንካላ የሆነ መልዕክት ለለመደዉ መንጋዉ ማስተላለፍ ፈልጎ ነዉ። በዚህ መልዕክቱ አብይን ወይም ደግሞ ዛሬ ላይ ያለዉን መንግስት ሳይሆን በኢትዮጵያ ሕዝብ ና ሉዓላዊነታቸዉ ላይ ተመፀድቆ ሔደ። የኢትዮጵያ ሕዝብ ሳይሆን የሆነ የዉጪ አካል፣ የፈለገ ቀን የአግሪቷን መንግስት እንደፈለገ ና እንደተመቸዉ እንስቶ ሌላ ተላላኪ መንግስት መስቀመጥ ይችላል። ጃንጆ ደግሞ ያኔ ጥሩ አጋጣሚ የምገኝለት ና እንደለመደዉ መንጋዉን አሰልፎ ወደ ስልጣን ጠጋ የምል ይመስለዋል። በምወረዉራቸዉ ተልካሻ አባባሎች፣ የሱ የስልጣን ሕልም ይበልጥ እየራቀዉ ይሄዳል። ይህን ግለሰብ ጃንጆ ያልኩት የለምክንያት አይደለም። ዳሩ ግን ብዙ ጃንጆዎች በዛሬዋ ኢትዮጵያ ዉስጥ ፈለቶዋል፣ እንደ አሸን። ሁሉም የዞረባቸዉ ብቻ ሳይሆኑ፣ አጭበርባሪ ሌቦች ናቸዉ።

Post Reply