Page 1 of 1

ሞላ ማሩ!

Posted: 02 Aug 2025, 17:14
by Horus
ጊቢሶ ገበያ ማለት ከአማውቴ በላይ በአዲስ አበባ መንገድ ያለ ትልቅ የቅዳሜ ገበያ ነው! ብዙ ብዙ ግዜ ከናቴ ጋር ሂጄበታለሁ ! ( የሶዶ ጉራጌዎችና የበቾ ኦሮሞች መገበያያ የነበረ)።
ኦጀ ማለት ከብት መጠበቂያ (መገጃ) ደቦ ማለት ነው። እኔ ኦጀ ጥብቂያለሉ ፤ ማለትም ጠዋት ሁሉም ከብቱን አውጥቶ የኦጀ ተራ ለደረሰበት ልጅ ያስረክባል ።ያ ልጅ ከብቶቹን ሲጠብቅ ውሎ ማታ ለየቤቱ ያስረክባል ። በማግስቱ ሌላ ልጅ ተመሳሳይ ያረጋል ... ይህ ኦጀ ነው ፤ ሴቶች እንሰት የሚፍቁበት ደቦ ዉሳቻ ይባላል ። ወንዶች እንሰት የቆፍሩበት ደቦ ድድቅ ይባላል ። እርሻ የሚታረስበት ወይም እህል የሚታጨድበት ደቦ ይባላል። ሰርግ ካለ የጌሾ መውቀጫ ደቦ ውዘተ ወዘተ አለ ። ይህ የጉራጌ ሴራ ነው!!!