Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Zmeselo
Senior Member+
Posts: 36763
Joined: 30 Jul 2010, 20:43

የኦሮሞ ምሁራንና የፓለቲካ ፓርቲ ተወካዮች ስምምነትና ውሳኔዎች

Post by Zmeselo » 02 Aug 2025, 03:27

የኦሮሞ ምሁራንና የፓለቲካ ፓርቲ ተወካዮች ስምምነትና ውሳኔዎች

ሲያትል ፣ ዋሽንግተን
ሐምሌ 31 ቀን 2025 (እ.ኤ.አ.)


የኦሮሞ ምሁራና የፓለቲካ ፓርቲ ተወካዮች እ.ኤ.አ. ሐምሌ 31 ቀን 2025 በሲያትል: ዋሽንግተን ግዛት በመገናኘት በኦሮሚያ፣ ኢትዮጵያና የአፍሪካ ቀንድ ጉዳዮች ላይ ሰፊ ውይይትና ትንተና ካደረግን በኋላ ከዚህ በታች በተዘረዘሩት ጉዳዮች ላይ ተስማምተን ውሳኔዎች ላይ ደርሰናል።

አንደኛ፡ አሁን በኢትዮጵያ ያለው አገዛዝ የኦሮሞን ህዝብ ከዚህ በፊት ታይቶ ለማይታወቅ ሰቆቃ እና ጭቆና እንዳጋለጠው ተገንዝበን ይህ አገዛዝ መወገድ እንዳለበት ተስማምተናል። ይህ ቡድን ፀረ ኦሮሞ ተግባራትንና ፖሊሲዎችን እየፈፀመ በዚህ ብሄር ውስጥ ለመደበቅ የሚያደርገውን ሙከራ አጥብቀን እናወግዛለን። በተመሳሳይ አንዳንድ ወገኖች ይህን ቡድን በተሳሳተ መንገድ "የኦሮሞ መንግሥት" ብለው መጥራታቸው ከነባራዊው እውነታ የራቀና ተቀባይነት የሌለው ነው።

ሁለተኛ፡ የአብይ አህመድ ጨቋኝ አገዛዝ በሁሉም የሀገሪቱ ብሄረሰቦች ላይ እያደረሰ ያለውን ጉዳት አጥብቀን እናወግዛለን።

ሶስተኛ፡ የኦሮሞ ፖለቲካ ድርጅቶች (ኦነግ-ኦነሠ: ኦፌኮ እና ኦነግ) አስፈላጊውን ለውጥ ለማምጣትና መጪውን ሽግግር ስኬታማ ለማድረግ በተደራጀ መንገድ የሚየደርጉትን እንቅስቃሴ በሁሉም ዘርፍ ለመደገፍ ተስማምተናል።

አራተኛ፡ የአብይ አህመድ መንግስት በሥልጣን ላይ ለመቆየት ከተጠቀመባቸው ስልቶች አንዱ በሕዝቦች መካከል ግጭቶችን መፍጠር ነው። በዚህም መሰረት በኦሮሞና በወንድማማች ሕዝቦች መካከል ጥርጣሬና ግጭት ለመፍጠር ያለመ መሆኑን በመረዳት ሁሉም የሀገሪቱ ሕዝቦችና ዜጎች ይህንን እኩይ አገዛዝ ለመለወጥ ከመቼውም ጊዜ በላይ ወቅታዊ ትብብር እንዲያደርጉ ጥሪያችንን እናቀርባለን።

አምስተኛ፡ የአብይን ብልፅግና መንግስት የሚያገለግሉ ወታደራዊና የፖለቲካ ሃይሎች የአገዛዙን ሥልጣን ከመጠበቅ የህዝብን ጥቅም ወደ ማስከበር እንዲሸጋገሩ ጥሪ እናደርጋለን።

ስድስተኛ፡ በኦሮሞ የፓለቲካ ኃይሎች መካከል የተጀመረው ውይይት እንዲቀጥልና ከሌሎች የአገሪቱ ሕዝቦችና ዜጎች ጋር ምክክር ለማድረግ ተስማምተናል።

ሰባተኛ፡ የአብይ አህመድ አገዛዝ እድሜውን ለማራዘም በህዝቦች መካከል ግጭት በመፍጠር መፈናቀልን ሲፈጥር የቆየና በመፍጠርም ላይ ያለ መሆኑን በመረዳት ህዝቡም ይህንን ስልት ተገንዝቦ በመካከሉ ያለውን አንድነትና ወንድማማችነት እንዲጠብቅ ጥሪያችንን እናቀርባለን።

ስምንተኛ፡ የአብይ አህመድ አገዛዝ ከላይ የተዘረዘሩትን ወንጀሎች የኦሮሞን ሕዝብ ጨምሮ በሁሉም የአገሪቱ ሕዝቦችና ዜጎች ላይ እየፈጸመ ያለ መሆኑን በመረዳት መጪው ለውጥና ሽግግር ስኬታማ እንዲሆኑ የኢትዮጵያ አጎራባች አገሮችና የዓለም አቀፍ ማኅበረሰብና ተቋማት አስፈላጊውን ጫና እንዲያደርጉ እንጠይቃለን።

በመጨረሻም የተጀመሩት ውይይቶችን የሚያካሂድና የተደረጉትን ውሳኔዎችን ለማሳካት አስተባባሪ ኮሚቴ ተቋቁሞ ሥራ እንዲጀምር ተደርጓል።

አንድነታችን በነፃነት ይፀናል፣
ድል በትግላችን ይመጣል!



Post Reply