Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
almaze
Member+
Posts: 8356
Joined: 15 Dec 2013, 03:38

ባማርኛ መለፍለፍ አቁም!

Post by almaze » 02 Aug 2025, 01:31

:lol: :lol: :lol:

Please wait, video is loading...

Meleket
Member
Posts: 4773
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: ባማርኛ መለፍለፍ አቁም!

Post by Meleket » 02 Aug 2025, 04:13

ይህ ናትናኤል የሚባል ጥሬ ካድሬ ምንድን ነው የሚለው? ስታሊን በአማርኛ ለሰፊዉ የኢትዮጵያ ህዝብ ማስተላለፍ የሚፈልገውን ነገር በቀላል መንገድ ቢያስተላልፍ ምኑ ላይ ነው ሓጢኣቱ? የኤርትራ “ድምጽ ሓፋሽ” እንዲሁም የወያኔው ሬዲዮና ቲቪ፡ በኣማርኛ ዛሬ ሳይሆን በትግል ወቅትም ያስተላልፉ ነበር። በመሆኑም ስታሊን እያደረገ ያለው፡ የተለያዩ ኢትዮጵያዊያን የፖለቲካ ሃይሎችን ድምጽ ማሰማት፡ ማስተባበር፡ ሃሳቦች አፍልቆ ማካፈል፡ የትግራይን ኣቋም መግለጽ፡ ሊያስመሰግነው እንጂ፡ “ተዉ አማርኛ ኣታውራ” ሊያስብለው ኣይገባም።

የዚህ የናትናኤል የሚባል ልጅ ችግር፡ እሱ ማድረግ የማይችለውን ሌሎች ሲያደርጉና ይበልጥ እንደጸሃይ ደምቀው ሲታዩ፡ የሚያቅለሸልሸው መሆኑ ላይ ነው። ወደደም ጠላም ናትናኤል ልክ እንደ ስታሊን የትግራይ ልጅ ነው፡ በዜግነቱም ኢትዮጵያዊ፡ አማርኛም ከሃገራዊ ቋንቋዎቹ ኣንዱ። በመሆኑም አማርኛ ከትግርኛ ይልቅ በርካታ ሚሊዮኖች የሚግባቡበት ቋንቋ ስለሆነ፡ ስታሊን እያደረገ ያለው ነገር መበረታታት ይገባዋል። ሊገፋበትም ይገባዋል። ቢያንስ ቢያንስ ትግራይ ከጐረቤቶቿ ጋር በሙሉ ሰላም እንደምትሻ ለኢትዮጵያዉያን መንገር ይችላል በትግርኛ ሳይሆን በኣማርኛ ኢትዮጵያዊያን በሚሰሙት ቋንቋ። የትግርኛ ተናጋሪ ኣንቂ እጥረት ያለ ይመስል፡ ኣንድ ባማርኛም የህዝቡን ኣቋም መግለጽ የሚችል ዜጋ ቢገኝ እንዲህ የሚዘመትበት ለምንድን ነው? አግባብ አይደለም።

ይህ ናትናኤል የተባለ ወጠጤ፡ ከዚህ በፊት ሃይለ ደደቢት የተባለ የትግራይ የሚዲያ ሰዉን፡ ለምን እኔ እንደማስበው “ጽምዶ ጽምዶ” ብለህ ኣታናፋም፡ ለምን የራስህን ሃሳብና ኣቋም ታስተጋባለህ በማለት ሊዘረጥጠው ሲሞክር ታዝበን ነበር። ሃይለ “የማምንበት እንጂ ኣንተ የምታምንበትን ማስተጋባት ኣይጠበቅብኝም”፡ በማለት እቅጩን ነግሮት ነበር። ትግራይ እንኳንስ እንደ ስታሊንና ሃይለ ዓይነት የበሰሉ ልጆችን ወለድሽ፡ አንዱ ባማርኛ ኣንዱ በትግርኛ ህዝብን እያነቁ ሰላም ትኖሪ ዘንድ እየተጉልሽ ናቸው! አንድ ብርሃነ የተባለ “አክቲቪስት”ም ከዚህ ቀደም፡ አንዲት “መድህን” የተባለች በነጻነት ህዝቧን የምታነቃ ብርቅ የትግራይ ጋዜጠኛ ላይ ያነጣጠረ ዛቻ፡ ኤርትራ ውስጥ ከሚዘባርቀው አወል ጋር ኣብሮ ሲዘባርቅ ሰምተን ነበር። ትግራይ ሆይ፡ በሃይለና በስታሊን ልትኮሪ ሲገባሽ፡ በናትናኤልና ብርሃነ በተባሉት ትኩረት ፈላጊ ተራ ወጠጤዎች ልጆችሽ ግን ልታፍሪ ይገባሻል ብለናል እኛ ኤርትራዉያን የመሃልና የመስመር ዳኞች፡ በተለመደው ኤርትራዊ ጭዋነት ኩራትና ትህትና ጭምር።

almaze wrote:
02 Aug 2025, 01:31
:lol: :lol: :lol:

Please wait, video is loading...

Post Reply