ይህ ጥያቄ ስለ ሁለቱ ቃላት ትርጉም ማጥናት እና የኢትዮጵያ ጥንት ግዜ ክብረ ነገስት መሠረቶችን መመርመር ነዉ።
የቃላቱን መሠረቶች ማጤን ጉድ ነዉ የምያስብል ይመስለኛል። ሌላ የተሻለ አስተሳሰብ ከተገኘ ማወቁ ደስ ይለኛል።
ስለ ኢትዮጵያ እና ምስራቅ ኣፍርካ ታሪክ ማንበብ ስጀምር ሰለ ንግስት ሳባ ታሪክ ኣንድ ነገር ገርሞኝ ሀሳቤን ጽፌ ነበር።
እስከ ቅርብ ግዜ ድረስ ከንጉስ ሰለሞን ጋር ተገናኝታ ቀዳማዊ ምንልክን ወልዳለች የሚለዉን ታሪክ ተጠራጥሬ ኣላዉቅም ነበር።
በቅርብ ግዜ በአጋጣሚ ኣይቼ ያነበብኩኝ ንግስት ሳባ እና ንጉስ ሰለሞን የኖሩት ግዜዎች የተራራቁ ስለሆነ በግዜ ምክንያት ብቻ ትረካዉ ዕዉነት ሊሆን ኣይችልም ይላል።
የእኔ ጥያቄ ትረካዉን እንደ ዕዉነት ተቀብዬ ንግስት ነበረች ማለት ንግስት የሆነችላቸዉ ሕዝብ ነበረ ከማለት ይጀምራል። ትረካዉ የሕዝቡ መሆኑ ቀርቶ ከንጉስ ሰለሞን ስለወለደችዉ ቀዳማዊ ምንልክ ሆነ ማለት ነዉ።
ይህ ሁሉ ትረካ ለክብረ ነገስት መሆኑ ነዉ?
የንግስት ሳባ እና የንጉስ ሰለሞን መገናኘት ትረካ ሀሰት ከሆነ ዕዉነቱን መፈለግ ያስፈልጋል ማለት ነዉ።
ይህን ዕዉነት መፈለግ ምርምር ፈቶታል ብዬ ኣስባለሁ።
ንጉስ የሚለዉ ቃል መሠረቱ ነጋ የሚል ነዉ ብዬ ማሰላሰል ከጀመርኩኝ ሰንብቻለሁ።
ትላንትና ክብር የሚለዉን ቃል ለብቻዬ እያሰላሰልኩኝ ሁለት ቃላትን ኣስታወስኩኝ፥ ከን በራ። በረ ማለት በእንግሊዘኛ ኤራ የምንለዉ ነዉ።
ኣሁን አጭር ጥያቄዉ ከበረ የሚለዉ ቃል ዉስጥ በረ ወይም ኤራ ሊኖር ይችላል ወይ ነዉ።
በረ አክናተን ከተባለ፣ በረ ቱታንከአሙን ከተባለ የአክናተን፣ የቱታንከአሙን ዘመን ወይም ጀበን ማለት ይሆናል።
ሰዎችን ጉድ ነዉ ማስባል ያለበት ለምንድነዉ የክብረ ነገስት ትረካዉ መሠረቱ የምስራቅ ኣፍርካ ፈረኦኖች እነ አክናተን እና ቱታንከአሙን መሆኑ ቀርቶ ምናልባትም መወለዱ ያልተረጋገጠ ቀዳማዊ ምንልክ የሆነዉ ነዉ።
ይህንንም ፕሮፌሰር ዶናልድ ኤን ለቪን ግልጥ ኣድርጎ ኣስቀምጧል።
የጥንት ኢትዮጵያ ነገስታት በእግዝኣብሔር ፈቃድ የተባረከ እና የተረገመ ጎሳዎች የሚል ወሬ ሲሰሙ የቀድሞ ማንነታቸዉን መተዉ ስላልፈለጉ እና በእግዝ ኣብሔር ፈቃድ የተረገሙ መባልም ስላልፈለጉ ለሁለት ሺህ ዓመታት ገደማ የማንነት ትግል ዉስጥ ገቡ ይላል።
ይሰማል ፕሮፌሰር ሆረስ?
ይህ ማለት ልክ እንደ ስደት ታሪክ የክብረ ነገስት መሠረት ታሪክም ከኣፍርካኖቹ ፈረኦኖች ተናግቶ መወለዱ ወደ ኣልተረጋገጠዉ ቀዳማዊ ምንልክ እንዲሆን ተደረገ ማለት ነዉ።
ይህን ስህተት የምያርመዉ የተሳሳተዉን የተባረከ እና የተረገመ ወሬዉን ማረም ነዉ ብዬ ኣስባለሁ።
ይህን የተሳሳተ ወሬን ማረም ንግስት ሳባ የነገሰችላቸዉ ሕዝብ ማን ነበሩ ወደሚለዉ ጥያቄ ይመልሰናል።
ንግስት ሳባ ትናገር የነበረዉ ቋንቋ ምን ይባል ነበር? ትግርኛ፣ ጉራግኛ፣ አማርኛ፣ ኦሮምኛ ተብለዉ ይታወቁ ነበር? ወይስ ግዕዝ ተብሎ ይታወቅ ነበር፣ ወይስ በጥቅሉ ሰብኛ ልንለዉ እንችላለን?
ዶክተር ኦሮሞ ለዚህ በጣም ጥልቅ ጥያቄ ቀርቶ ኦሮሞ የምለዉን ቃል መሠረት ያለ ስህተት ማብራራት ይችላል?
እነዚህ ጥያቄዎች ለሁለተኛዉ ሬይነሳንስ ለምለዉ መሠረትን የሚጥሉ ናቸዉ።
የእኔ ሀሳብ ሆነ አስተሳሰብ ትክክል ነዉ ብዬ ኣልከራከርም። የበለጠ ትክክለኛ የሆኑ ከተገኙ በደስታ ለመማር ዝግጁ ነኝ።
መሠረቱ የፍጥረት በሯ ኢትዮጵያ የሆነዉ ሁለተኛዉ ሬይነሳንስ ብሎም የኢትዮጵያ ህዳሴ ሆነ እዴሳ ለብዙ ጥናቶች መንገድ የሚከፍት እንጂ ስራዉ የተደመደመ ኣይዴለም።
የማጥናት ዕዉቀቱ እና ችሎታዉን ያላችሁ ጉድ ነዉ ሰዎች ብላችሁ በመነሳት ማጥናት ትችላላችሁ?