ትላንትና ቃል ስፈልግ እነዚህን ቃላት ኣስታወስኩኝ።
የፈለኩት ቃል ወሬ ከምንለዉ ቃል ጋር የተገናኘ ነዉ።
ቃሉን ለብቻዬ ወዲህ ወድያ ኣድርጌ ሳጠናዉ በልጅነቴ የሰማሁትን አባባል ኣስታወሰኝ።
አባባሉ ዋን ወር ዋሪ ሃሰኡ እጆሌን ዋሬ ሃሶፍት የሚል ነዉ።
ቤተሰብ ማታ ያወራዉን ልጆች ጠዋት ያወራሉ ማለት ነዉ።
ዋሬ የሚለዉን ቃል ሳስታዉስ ወሬ የሚለዉ ቃል መሠረት ምንድነዉ ኣስባለኝ።
በተጨማሪም ሃሳ እና ሂስ የሚሉትን ቃላት ሳስታዉስ አባባሉ የበለጠ ደነቀኝ።
ቃላቶቹን ሁሉ ደግሞ በደንብ ሳስተዉል እንደዚህ ግልጽ የሆኑ የቀን ግዜ ኣመልካች ቃላት ሌሎች ቋንቋዎች ዉስጥ ለመኖራቸዉ መልስ ኣጣሁኝ።
የቃላቱ ትርጉሞች፥
ገነመ፥ ጠዋት፣ ፀሓይ መዉጫ አከባቢ
ዋሬ፥ ከጠዋት በኋላ፣ እኩለ ቀን ሳይደርስ በፊት ዉስጥ ያለ ግዜ ነዉ። በእኔ አስተሳሰብ ፀሓይ ወጥታ ሶስት ሰዓታት ሲሞላ አከባቢ ያለ ግዜ ነዉ።
ሳፋ፥ እኩለ ቀን ማለት ነዉ። በእንግሊዘኛ ኑን የሚባለዉ ነዉ።
ጨብሳ፥ ከእኩለ ቀን በኋላ፣ ማታ ሳይደርስ በፊት ዉስጥ ያለ ግዜ ነዉ። በእኔ አስተሳሰብ እኩለ ቀን ኣልፎ ሶስት ሰዓታት ሲሞላ አከባቢ ያለ ግዜ ነዉ።
ገልገለ፥ የፀሓይ መጥለቅያ ግዜ ቢሆንም ከዛ በኋላ ያለ አመሻሽም ይመስለኛል።
እነዚህን የቀን ግዜ ኣመልካች ቃላትን ማስታወስ እና ስለ የዐለም የመጀመርያዉ ሞኖቴይዝምን ማሰላሰል ሁለቱም ከፀሓይ ጋር የተገናኙ መሆኑን ልብ ኣልኩኝ።
እኔ የምለዉ እዴሳ እንደዚህ ማለት ነዉ። ለጥናት የሚሆን ኣዲስ ማስተዋል ላይ ብርሃን ቦግ ማድረግ ማለት ነዉ። ጥናቱን ግዜ እና ሙያዉን ላላቸዉ ተመራማሪዎች ማሳየት ማለት ነዉ።
ጉዳችሁ ፈላ ኣንሰማም ያላችሁ የኦርሙማ እና የቁቤ ፖለትከኞች። ኣንድ ፀሓይ ያለዉ፣ ፊደል የቀረጸዉ፣ ሃሳ ብሎ ሂሳብ ያስተማረዉ ማን ነዉ ተብላችሁ ልትጠየቁ ነዉ።
ጉዳችሁ ፈላ Gላ ማለት ማወቅ የመሰላችሁ ጥርቅሞች። እናንተም ይህንኑን ጥያቄ ተጠየቃችሁ። መልሳችሁ ምን ይሆን?