የባለቅኔ ክቡር መንግስቱ ለማ ምሽት ነው! ዛሬ አዳረ!!!
Posted: 25 Jul 2025, 21:49
የስነጽሁፍ ፍቅር ያሲያዙኝ ተቀዳሚው ልሳነ ማሩ መንግስቱ! ግጥምና ቲያትሮቻችውን ስንት ግዜ ደጋግመን እንዳነበብን ፈጣሪ ነው የሚያውቀው !!! ይህን እዚህ የምትሰሙት ባሻ አሸብር ባሜሪካ በጥቁር አሜሪካኖች የነጻነት ትግል ላይ የተቀኙት ቅኔ ሲሆን ልደት አዳራሽ ውስጥ በያመቱ የግጥም መድብል ወቅት ሲያብቡት ነው!
እስረኛ ግጥሞቼ በሚለው መድብላቸው ውስጥ ይህን ብለው ነበር ...
"ወይ ካላካበቱ ወይም ካላምታቱ
ማን ለማ ይሰጣል ከዚያ ከሱረቱ"
ንጉስ ኃይለ ስላሴና መኳንቶቻቸው ለስልጣኔ እንዲመች ብሄራዊ ቋንቋችን እንግሊዝኛ ይሁን አይሁን ብለው ሲሟገቱ ገና ሁለተኛ ደረጃ ተማሪ ሆኖ የብሄራዊ ቋንቋና የአገር ክብር ት ስ ስ ር በማስረዳት ኃይለ ስላሴን ያሳመነው ያልተዘመረለት ታላቅ ሰው መንግስቱ ለማ !!!!!!!!!!!!!
የኛ ትውልድ እድለኛ የተባረከ ትውልድ !!!! ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር !