The Addis Ababa Flooding Caused Due To A Flawed IrreCha Dam Around Maskel Square
Posted: 24 Jul 2025, 09:29
Yohaness Mekonnen
ምክር መስማት ማንን ይጎዳል?
ወንዝ ላይ አነስተኛ ዉኃ መከተርያም ሆነ ግድብ ሲሠራ ባለሙያዎች የወንዙን ተፋሰስ መጠን (Catchment area) በማጥናት እና ከሜትሪዮሎጂ መረጃ በማስላት ያልተጠበቀ ጎርፍ የሆነ ቀን ቢመጣ ማስተንፈሻ መንገዶችን አስቀድመው ያበጃሉ::
መስቀል አደባባይ አጠገብ እምብዛም ዉኃ በሌለው መሀል አዲስ አበባን አቋርጦ በሚሄደው ጅረት ላይ በቅርቡ አልፎ አልፎ አነስ አነስ ያሉ መከተሪያዎችን (ግድብ ላለማለት) ታስቦ ወራጁ ወንዝ ላይ በኮንክሪት ተሠርቷል:: ከእነኚህ አንደኛው ባለፉት 7 ዓመታት ኢሬቻ የሚከበርበት ቦታ እንደመሆኑ ተጨማሪ ዉኃ ለመከተር ታስቦ የተገነባው ነው::
በተያያዝው ቪዲዮ ላይ እንደምትመለከቱት ሙያዊ ባልሆነ መንገድ የተገነባው ይህ የኮንክሪት መከተሪያ የጎርፍ መጠን ሲጨምር ማስተንፈሻ አማራጭ ስላልታሰበለት የዛሬውን በመጠኑ ትንሽ ክፍ ያለ ዝናብ ማስተናገድ አቅቶት ከተፈጥሮአዊው ከመፋሰሻው ወጥቶ አካባቢውን አጥለቅልቆ ጉዳት አድርሷል::
በአካባቢው ያሉ ሕንጻዎች ምድር ቤታቸው ሙሉ በሙሉ ከጥቅም ውጪ ሲሆኑ በርካታ መኪኖችም በጎርፍ ተውጠው ከፊሎቹም እየተንሳፈፉ ሲሄዱ በአከባቢው የነበርን በኅዘን እያየን ነበር:: አንዳንድ ባለመኪኖችም ወገባቸው ድረስ በጎርፍ ተውጠው መኪናቸውን ለማዳን ጥረት ሲያደርጉ ይታዩ ነበር::
የኮሪደርም ሆነ የወንዝ ዳርርቻ ልማት ተብሎ የተጀመረውን ሥራ ከተማን የማሳመርም ሆነ የእግረኛ እና የብስክሌት መንገዶች የመገንባት ሃሳቡ መልካም እና የሚደገፍ ሆኖ ትግበራው ግን "ካድሬአዊ" ሳይሆን "ሙያዊ" ይሁን የሚል ሀሳብ ሲቀርብ "ጥድፊያ ላይ ስለሆንን ለምክር እና ለዲዛይን ጥናት ጊዜ የለንም" የሚሉ ባለሥልጣናት ቢያንስ ይህንን ከመሰለ ስህተታቸው እንዲማሩ እመኛለሁ::
ሥራን በሠከነ እና ሙያዊ በሆነ መንገድ አለመሥራት ውጤቱ ከዚህ ውጪ ሊሆን አይችልም:: ለታይታ እና ለምርቃት ብቻ በመጉዋጉዋት በችኮላ እና በግርግር ዕውቀት እና ልምድ የሚፈልግን ሥራ ጠቅልሎ በኮሚቴ እና በካቢኔ ውሳኔ አየገነቡ እና እያፈረሱ መሄድ የሀገርን ሀብት ለብክነት መዳረግ ነው::
ሰላም!