Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Naga Tuma
Member+
Posts: 6244
Joined: 24 Apr 2007, 00:27

የመሃይምነት ማረጋገጫ መሃይምነት እራሱን ማደባየት ነዉ

Post by Naga Tuma » 22 Jul 2025, 14:29

ይህን ቃል በቀላሉ የምጠቀም ሰዉ ኣልነበርኩም።

እዚህ ፎረም ላይ መሳተፍ የጀመርኩኝ ከ18 ዓመታት በፊት ነበር።

በርካታ ነገሮችን ኣንብቤ፣ ኣጥንቼ፣ ለረጅም ግዜ ኣሰላስዬ ስለ ኣስተዋልኩኝ ለመወያየት የኢትዮጵያ ምሁራንን ስፈልግ ኖርኩኝ።

እዚህ ፎረም ላይ ተሳታፊዎች ዉስጥ በአካል ባንተዋወቅም ምሁራዊ ዝንባሌ ኣላቸዉ ብዬ ካሰብኩዋቸዉ ጋር ለመወያየት ሞከርኩኝ።

በብዛት ኣንድ በሽታ ኣላቸዉ። የተሻለ ስለምናዉቅ ሀሳብህን ቆም ብለን ለማስተዋል ግዜያችንን ኣናጠፋም የሚል ዐይነት ተመሳሳይ ጉራ ነዉ።

እየታዘብኩ፣ እየታገስኩ ያስተዋልኩትን ማጋራት ቀጠልኩኝ። ማስተዋሉ በቀላሉ እንደማይመጣ በደንብ ኣዉቃለሁ።

የሰዉ ልጅ ትምህርት ከጀመረበት ቀን ጀምሮ የሚማረዉ ኣንድ መሠረታዊ የሆነ ነገር ነዉ። ዕዉነትን ከሀሰት ወይም ትክክልን ከስህተት መለየት ነዉ። ለዚህ መሣርያዉ ዕዉቀት ነዉ። ለዚህ ነዉ ሰዉ ለማወቅ የሚጥረዉ ወይም መጣር ያለበት።

ስለዚህ ለምሁር መሳሳት ኣሳፋሪ ነዉ። የታወቀ ስህተትን ኣለማረም ለምሁር ነዉር ነዉ።

ይህቺን ያህል ያላስተዋለን ለብዙ ዓመታት መታዘብ፣ መታገስ፣ መዝለፍን ያስከትላል።

በርጩመ ኡልፍና አባቱ ኡፍ ጀለ ባተ የተባለዉ ያለምክንያት ኣልነበረም። የክብር በርጩማን ባለቤቱ ነዉ ስር ስሩ የሚሸከመዉ እንደማለት ነዉ።

እዚህ ፎረም ላይ መሳተፍ ሳልጀምር በፊት በኢትዮጵያዊያን ሆነ ኤርትራዊያን ምሁራን ዉይይት ኣስፈላጊ ነዉ ያልኩኝ ይህን ያህል ዓመታት ሰንብተዉ ስህተት እንደነበሩ በእራሳቸዉ መሰከሩ።

ሁለት ማስረጃዎች ለታሪክ ይቀመጡ።

Naga Tuma
Member+
Posts: 6244
Joined: 24 Apr 2007, 00:27

Re: የመሃይምነት ማረጋገጫ መሃይምነት እራሱን ማደባየት ነዉ

Post by Naga Tuma » 22 Jul 2025, 14:48

ማስረጃ ቁጥር 1፥

The Western powers or Vatican are not Christian’s by definition

ይህን የፃፈዉ ethiopianunity ነዉ።

ይህን ከፃፈ በኋላም የበለጠ አዋቂ ነኝ ማለት ይዳዳዋል።

Abere
Senior Member
Posts: 13971
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

Re: የመሃይምነት ማረጋገጫ መሃይምነት እራሱን ማደባየት ነዉ

Post by Abere » 22 Jul 2025, 15:02

Naga Tuma,

ከይቅርታ ጋራ ለመጀመሪያ ጊዜ እንከን የለሽ የተሳካ ቀጥተኛ አጻጻፍ ዛሬ አነበብሁኝ። ሌሎች ምን እንደታዘቡ አላውቅም። ታዲያ እንድህ ቀጥተኛ አገላለጽ እያለ ብዙ ጊዜ በዞረ ሁኔታ ነበር አገላለጽህ - ውስጠ ወይራ ይሁን ሌላ አቡሻክር ብቻ በዚያ መልኩ ነበር ሀሳብህን አገላለጽህ።

በመቀጠል በዚህ ፎረም ላይ ካድሬዎች፤ ጆሮ ጠቢዎች፤ ባንዳዎች፤ የፓለቲካ መልቲዎች (ቁማርተኞች)፤ አገር ሻጮች (ባንዳዎች)፤ ስነ-አደሮች (ዓሳማዎች - ሆድ ንጉሡ) በየዋሃን፤ በአገር ወዳዶች መካከል የሚርመሰመሱበት እንጅ አካዳሚክ ውይይት የሚደረገብት እኮ አይደለም። ምሳሌ ልስጥህ - በእውነት ብርሃኑ ነጋ እና አል ማርያም የአካዳሚክ የምርምር የሳይንሳዊ ተጠየቅ ሰዎች ቢሆኑ መያዣ መጨበጫ ካለው የዘር አጥፊ ፓለቲካ እና ወንበዴ ጋር ይሆኑ ነበር? አይሆኑም ነበር። ስለዚህ በመጀመሪያ እራስህን ጠይቅ እስኪ አንተ እራስህ ኢ-ሳይንሳዊ እና ኢ-ሰ ብ አዊ ከሆነ የድንጋይ ዘመን ጎሳ አስተሳሰብ ነጻ ነህ ወይ? በተልዕኮ የተሰማሩ አዞዎች የተሰማሩበት ፎረም እንጅ አካዳሚክ ውይይት በማድረግ ውጤታማ የጋራ ህልም ወይም መንገድ መያዝ ላይ ያተኮረ አይደለም።

የተረተረት ልብ-ወለድ የታሪክ መድብል በካድሬዎች ይጻፋል እንጅ ህዝብ ከህዝብ ለማጋጨት - በጎ ሀሳብ አይንሸራሸርም። ዛሬ ጥሩ አስተያየት እና ምክር አዘል ሀሳብ ሰጠ ያልከው ሰው ነገ በኦሮሙማ -ብልጽግና ተገዝቶ ጭልጥ ብሎ ጥፋት ውቅያኖስ ይሰምጣል። ታዲያ ወፈ ሰማያት ሻዕብያ ከዚህ የሚርመሰመሰው በጎ ሀሳብ ሊዘራ አይደለም እኮ በተቻለ መጠን ሻዕብያ የሚፈልጋት አይነት ደካማ ኢትዮጵያ ማየት ነው። ነጩን ጥቁር ነው ብለው ሸምጥጠው የሚያጭበረበሩ።

In any case, based on your today's writing I visualize two Naga Tuma, but still one Nega Tuma. :mrgreen:


Naga Tuma
Member+
Posts: 6244
Joined: 24 Apr 2007, 00:27

Re: የመሃይምነት ማረጋገጫ መሃይምነት እራሱን ማደባየት ነዉ

Post by Naga Tuma » 22 Jul 2025, 15:12

ማስረጃ ቁጥር 2፥

ፈርኦኖቹ ፒራሚድ ያቆማሉ! ፊኛሜንታል አሁንም ፎቶሾፕ እየነፋ ነው!!!!

ይህን የፃፈዉ Horus ነዉ። በእኔ ግምት ቦረና ዉስጥ ባህሌን ብለዉ ጸንተዉ የሰነበቱትን ኢትዮጵያዊዎችን ዕድሜ ልኩን Gላ ሲል ኖሮ ነዉ።

የሬይነሳንስ ሰዉ ፈረኦኖች እና ቦረና ዉስጥ ባህሌን ብለዉ ጸንተዉ የኖሩት ኢትዮጵያዊዎች ከክርስትና ዉጪ የኖሩ መሆናቸዉን በቅጽበት ያስተዉላል።

የሬይነሳንስ ሰዉ ከሳይንትስት በላይ ኣዋቂ የሆነ ሰዉ ነዉ።

Naga Tuma
Member+
Posts: 6244
Joined: 24 Apr 2007, 00:27

Re: የመሃይምነት ማረጋገጫ መሃይምነት እራሱን ማደባየት ነዉ

Post by Naga Tuma » 22 Jul 2025, 15:19

Abere:

የምጽፋቸዉ እንደ ዳ ቪንቺ ኮድ ከሆኑብህ የበለጠ ግልጽ ማድረግ ይጠበቅብኛል።

ዳ ቪንቺ ኮድን ኣንብቦ ማወቅ እኔ ከኣንተ የበለጠ ግዴታ ኣለብኝ?

Post Reply