Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Naga Tuma
Member+
Posts: 6242
Joined: 24 Apr 2007, 00:27

የኤርትራ ምሁራን ለምንድነዉ ከእናት ሃገራችን የምንጣላዉ ማለት እንዴት ነዉ ያልቻሉት?

Post by Naga Tuma » 20 Jul 2025, 19:59

ይህን ጥያቄ የምጠይቅ እ ኣ አ በ1988 ዓ ም የመጀመርያ ዓመት የኮሌጅ ተማሪ ሆኜ የኢትዮጵያ ታሪክ ትምህርት ዉስጥ ስለ አደዋ እና ኤርትራ ታሪክ የተማርኩኝ ዕለት እዉነታቸዉን ነዉ የሚታገሉት ያልኩኝ ነኝ።

በወቅቱ የነበረዉ የኢትዮጵያ መንግስት ከወደቀ በኋላ የኤርትራ ምሁራን የኢትዮጵያን ሪቪዉ መጽሔት ላይ የምያሳትሙትን ጽሑፎች በጥሞና ነበር የማነበዉ።

ካልዘነጋሁ በተለይ ተኬ ፍስሃጽዮን የተባለ የኤርትራ ምሁር የሚጽፈዉን በጉጉት ኣነበዉ ነበር።

የኢትዮጵያ ታሪክ ትምህርት ዉስጥ የትግላቸዉ መንስኤ እጅግ ኣሳዛኝ መሆኑ በኣንድ ኣፍታ ቢገባኝም የምያዛልቅ መፍትሔዉ ከእናት ሃገራቸዉ ከኢትዮጵያ ነፃነት ነዉ ማለት ለእኔ ኣሳማኝ ሆኖ ኣያዉቅም።

ብዙ ኤርትራዊያንን ባላዉቅም በኣንድ ወቅት የተማርኩበት ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ዳይሬክተር ወይም ሬጂስትራር የዛን ግዜ ኤርትራ ክፍለ ሃገር ሰዉ ነበር ሲባል ሰምቻለሁ። መሆኑን ብቻ ሳይሆን ለሌላ የትግራይ ክፍለ ሃገር ሰዉ ይህ ባች ጠንካራ ባች ነዉ ማለቱን ሰምቼ ነበር። የሁለተኛ ደረጃ የተለያዩ ባቾችን ተከታትሎ የምያነፃጽር መሆኑ ያልጠበኩት ሆኖ ያከበርኩት ሰዉ ነዉ።

የኤርትራ ክፍለ ሃገር ሆነ የትግራይ ክፍለ ሃገር ሰዉ እንደ ማንኛዉም ኢትዮጵያዊ እያየሁኝ ነበር ትምህርቴን የምከታተለዉ።

እኔ የማዉቀዉ እነሱም እራሳቸዉን እንደ ማንኛዉ ኢትዮጵያዊ የምያዩ እና የምያዉቁ እንደሆነ ነበር የሚገባኝ።

የፍጥረት በር የተባለችዉ ኢትዮጵያ ለእነሱም እናት ሃገር መሆንዋን ሁላቸዉም፣ በተለይ ምሁራኖቻቸዉ፣ በጥልቀት ያስተዋሉ ይመስለኝ ነበር።

እናት ሃገር ስል ከፍጥረት ግዜ ጀምሮ ስያፈሩ እና ስያበሉ የኖሩ አፈሩ፣ ዉሃዉ፣ አየሩ ናቸዉ።

ኢትዮጵያ ተብላ የተሰየመች ሃገር ኣንድ የፖለትካ ማህበረሰብ የሚኖርባት የዚህ ምድር አካል ናት።

እንደ እኔ አስተሳሰብ ኢትዮጵያ ተብላ ከተሰየመች ሃገር በላይ መሠረታዊ የሆነ የፖለትካ ማህበረሰብ ያለ ኣይመስለኝም። ማስረጃዉ ከዚህ የምድር አካል በላይ የሰዉ ዘር ለረጅም ግዜ የኖረበት የምድር አካል መኖሩን ኣላዉቅም።

ይህ ስህተት ካልሆነ በዚህ የምድር አካል የሚኖር ሕዝብ እስከዚህ ዘመን ድረስ የተረጋጋ የፖለትካ ማህበረሰብ መፍጠር ኣለመቻሉ እጅግ ኣሳዛኝ ነዉ።

አሜሪካ ስያሜዋ ለጣልያናዊ ቀያሽ ወይም ፈለግ ወጊ በጀርመናዊ ቀያሽ ተሰጥቷት፣ እንግሊዘኛን ከእንግሊዞች ወስዳ፣ ሳይንስን ከኣዉሮፓ ኣግዛ፣ ግማሽ ኣህጉርን አሜሪካ ይኖሩ ከነበሩ ወስዳ፣ ጉልበት ከኣፍርካ ሰብስባ፣ የዲሞክራሲ ስርዓትን ከጥንት ግሪኮች ኣጥንታ፣ ሁለት መቶ ሃምሳ ዓመታት ባልሞላ ግዜ ዉስጥ የዚህ ምድር ዋነኛ ሃያል አካል ለመባል በቃች።

ከሁሉም የምድር አካል የመጡ ሕዝብ ኣንድ ላይ የኣንድ የፖለትካ ማህበረሰብ ነን ብለዉ ይኖራሉ።

መሠረቱ ኢትዮጵያ የሆነ የዚህ የፖለትካ ማህበረሰብ ጦር ወታደር ሆኖ ያገለግላል።

መሠረቱ ኤርትራ የሆነ የዚህ የፖለትካ ማህበረሰ አካል ለሆኑ መራጮች የሕግ ኣዉጪ አካል ተወካይ ሆኖ የመረጡትን ያገለግላል።

ይህን ማስተዋል ብቻ የኤርትራ ምሁራን እጅግ ኣሳዛኝ ታሪክ እንዳለ ሆኖ እንዴት ነዉ ለምንድነዉ ከእናት ሃገራችን የምንጣላዉ ማለት ያልቻሉት?

የእኔ የዚህ ዘመን ዋናዉ ጥያቄ በዚህ በፍጥረት በር አዲስ የታሪክ ምዕራፍ መከፈቱን ስለምገነዘብ እኔ ተማሪ ሆኜ በመጀመርያ ተርታ ይሰለፉ የነበሩ የኤርትራ ምሁራን በዚህ አዲስ ምዕራፍ ዉስጥ የእነሱ ጉልህ ሚና ማነስ አዲሱን ምዕራፍ ያሳንሳል ለማለት ነዉ።

ይህን አዲስ ምዕራፍ በርካቶች ህዳሴ ቢሉትም በእኔ አስተሳሰብ እዴሳ የበለጠ ይገልጸዋል ብዬ ኣስባለሁ። ለእንላይትንመንት የሚቀርብ ትርጉም ኣለዉ። ሌላ የተሻለ ቃል ሊኖር ይችላል። ከተገኘ ለእኔ እሰዬ ነዉ።

ለዚህ እዴሳ ወይም እንላይትንመንት ኣንድ በጣም ቀላል ምሳሌ ንጉሴ የሚል ቃል ነዉ። እኔ የቋንቋ ባለሙያ ባልሆንም ነገሠ እና ነጋ እሳ ተመሳሳይ ይመስሉኛል።

እዴሳ እነዚህ ቃላት ላይ ብርሃኑን ቦግ ካረገ ሌሎች ስለ ቃላቱ ማጥናት ይችላሉ።

ድንበር ዬለሽ የኢትዮጵያም ሆነ የኤርትራ ምሁራን ሚና እዴሳን ያራምዳል፣ ጥናቶቹን ያቀላጥፋል።

የእኔ የዚህ ዘመን ጥሪ ይሄ ነዉ።

በእኔ ግምት ይህ ጥሪ የአዉሮፓ ከአምስት መቶ ዓመታት በፊት አነሳስ የበለጠ ጥልቅ የሆነ አነሳስ ለፍጥረት በር ኣበርካች የሚሆን ነዉ።

ይህን ጥሪ የበለጠ ኣንገብጋቢ የምያደርገዉ መሠረቱ ኤርትራ የሆነዉ የአሜሪካ የሕግ ኣዉጪ አካል አባል የሆነዉ ጆ ንጉሴን ኣሳታፊ ያደረገዉ የዲሞክራሲ ስርዓት የጥንት ግሪኮች ከጥንት ግብጥ የተዋሱት መሆኑን የምያሳይ ጥናት መገኘቱ ነዉ።

በእኔ ግምት ትግርኛ ተናጋሪ የሆነ በእንግሊዘኛ እየተናገረ የመረጡትን ሕዝብ የምያገለግል ነዉ።

ይህ ማለት ኢትዮጵያም የተረጋጋች አንድ የፖለትካ ማህበረሰብ ብትሆን ሁለት ቋንቋዎችን መናገር የሚችሉ የሕዝብ ኣገልጋዮችን ማፍራት ትችል ነበር ማለት ነዉ። የእኔ ቋንቋ ብቻ እንጂ ማለት እንቅፋት ይፈጥራል። ሌላ ቋንቋን መማር እና መናገር መቻል የራስን ቋንቋም ለማስተማር ድልድይ ይከፍታል።

ስለዚህ ለምሳሌ ያህል ጆ ንጉሴ ሁለት ቋንቋዎችን መናገር የሚችል የአሜሪካ የፖለትካ ማህበረሰብ የሕግ ኣዉጪ አካል አባል ሆኖ የመረጠዉን ሕዝብ ለማገልገል ፈቃደኛ ከሆነ እንዴት ሆኖ ነዉ የኤርትራ ምሁራን ለምንድነዉ ከእናት ሃገራችን የፖለትካ ማህብረሰብ የምንጣላዉ ማለት ያልቻሉት?

Fiyameta
Senior Member
Posts: 18123
Joined: 02 Aug 2018, 22:59

Re: የኤርትራ ምሁራን ለምንድነዉ ከእናት ሃገራችን የምንጣላዉ ማለት እንዴት ነዉ ያልቻሉት?

Post by Fiyameta » 20 Jul 2025, 21:16





For the record: We Eritreans never fought against the aid-fed minions next door to win our independence.
We fought against not one, but two world super powers.





Naga Tuma
Member+
Posts: 6242
Joined: 24 Apr 2007, 00:27

Re: የኤርትራ ምሁራን ለምንድነዉ ከእናት ሃገራችን የምንጣላዉ ማለት እንዴት ነዉ ያልቻሉት?

Post by Naga Tuma » 20 Jul 2025, 22:59

I have added this question before and let me ask you the same question again.

If you are not an Eritrean, what is your purpose in aggravating the wound?

For your information, my comments are for learned Eritreans, if there are some out there, about moving forward.

Fiyameta
Senior Member
Posts: 18123
Joined: 02 Aug 2018, 22:59

Re: የኤርትራ ምሁራን ለምንድነዉ ከእናት ሃገራችን የምንጣላዉ ማለት እንዴት ነዉ ያልቻሉት?

Post by Fiyameta » 20 Jul 2025, 23:12

What is your IQ? :|
I asked you because I don't want to give you any information that is beyond your level of understanding.


Naga Tuma
Member+
Posts: 6242
Joined: 24 Apr 2007, 00:27

Re: የኤርትራ ምሁራን ለምንድነዉ ከእናት ሃገራችን የምንጣላዉ ማለት እንዴት ነዉ ያልቻሉት?

Post by Naga Tuma » 21 Jul 2025, 12:12

Fiyameta wrote:
20 Jul 2025, 23:12
What is your IQ? :|
I asked you because I don't want to give you any information that is beyond your level of understanding.

I am an Ethiopian who has proven wrong every person from your map that I have ever met and redefined IQ that was formulated for illiterates like you.

Post Reply