Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 39842
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

የአዳረ (አርብ) ባንድ ጉንጉን ነው!!! ተፈታቱ!

Post by Horus » 18 Jul 2025, 23:18

በክስታኔኛ ቋንቋ አርብ አዳረ ይባላል ። ቅዳሜ ቅዳም ሰንበት (ቀዳሚ ሰንበት) ይባላል። አርብ ግዕዝ ሲሆን የፀኃይ መጥለቅ ማለት ነው ። ኧርብ ከሚለው ቃል ነው ምዕራብ የፀኃይ መጥለቂያ ቦታ የሚለው የመጣው። የአርብም ሆነ የምዕራብ ስረው ቃል ግን ወረብ (ዙረት ፣ መዞር) የሚለው ስረ ቃል ነው ። ዛሬ ላይ ወረብ ወይም የዙረት ሽብሸባ የምንለው ማለት ነው ።

የክስታኔኛ አዳረ ተነሳሳይ የፀኃይ መጥለቅና የምሽት ግዜ ዞሮ መምጣት የሚገልጽ ቃል ነው ። ዛሬ ላይ አደረ ፣ አዳሪ ፣ እንደ ምንለው ማለት ነው። አርብም ሆነ አዳረ ከጸሃይ መጥለቅ እና ከሳምንቱ የግዜ ኡደት ወይም ወረብ ጋር የተያያዘበት ምክኛት በኦሪት ክርስትና ዛሬ እሁድ ወይም አንደኛ ቀን የምንለው ቅዳሜን ነበር። እስከ አባቶቻችን ዘመን ቅዳሜ ልክ እንደ እሁድ የሚከበር ሰንበት ነበር። ስለዚህም ነው ክስታኔ ቅዳሜን ቅዳም (ቀዳሚ) ሰንበት የሚለው ።

ስለዚህ አርብ (አዳረ) የሳምንቱ መዝጊያ እና ያዲሱ ሳምንት ዋዜማ ማለት ነው/ነበር። እሁድን ክስታኔኛ ኡር ሰንበት ይለዋል ። ትርጉሙ እንደ ወረደ ዋናው ወይም የሓዲስ ኪዳን ሰንበት (ሳባዝ) ማለት ሲሆን ጥንታዊ ትርጉም የብርሃን መውጫ ቀን ማለት ነው ። ኡር ብርሃን ማለት ነው ፤ በግዕዝም በእብራይስጥም። ሰንበት (ስባዝ) የሚለው ቃል በግዕዝ ጽባህ ፣ ጽባዕ ወይም ወጣ ፣ ውጣ የምንለው ቃል ነው። ጽባህ ወንሴብሆ እጅግ ታላቅና ትልቅ ቃል ነው ።

የኬር አዳረ!