ኬር እና ፈያ የሚባሉት ጉራጌኛ ቃላት!
Posted: 13 Jul 2025, 01:49
ኬር ወይም ኬይር ሰላም ፣ ደህና ፣ መልካም ማለት ነው በክስታኔ ጉራጌኛ ። በሰባት ቤት ዎገሬት (ዎከሬት) ይባላል። ኬረት ፣ ኬርታ ፣ ኬርነት የሚሉና ሌሎችም እርባታዎች አሉት ። ይህ ቃል በአረብኛና በሕንድ እንዳለ ኬርይ ወይም ሄይር ይባላል ፤ መልካምነት ፣ ደህንነት ማለት ነው። ኬርታ ፣ ኬርነት በተለይ በክስታኔዎች ዘንድ መንፈሳዊነት የሚደርስ ትርጉም አለው ፤ እዝኬር ። እዝጌር (እግዚአብሄር) እስከ ማለት ድረስ ።
ሌላው ብዙ ሰው የምያውቀው ፈያ ፣ ፈያነት የሚባለው የክስታኔ ቃል ነው ። ይህ ቃል ጤና ማለት ሲሆን የአካል ጤነንት ብቻ ሳሆን ማንኛውም ጤነኛ የሆነ ነገርና ጥሩ የሆነ ነገርም ማመልከቻ ሆኖ ያገለግላል። ዋና ትርጉሙ ግን ያካልና ያይምሮ ጤንነት ነው ። አፌይት ፣ ቁም አፌይት ጤነንት ፣ ያካል ጤንነት ማለት ነው ። ይህ ቃል እንዳለ አረብኛ ውስጥ ያለ ነው ። እሱም አል አፊያ ይባላል!
ስለዚህ ክስታኔዎች ፈያ ነሽ? ሲሉ ከሰማችሁ ጤና ነሽ? ማለታቸው እንደ ሆነ እንድታውቁት ብዬ ነው። ኦሮሞች ተውሰውት ፋያ ፣ ፋዩማ ስለሚሉ ቃሉ ኦሮሞኛ እንዳይመስላችሁ ለማለት ነው።
ለምሳሌ ያክል ይህን ውይይት ስሙ
Al khayr