Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum

Abere
Senior Member
Posts: 13971
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

Re: “አማራ አማራ አትበሉ፤ አሰብ አሰብ በሉ” ለሚሉት ቱስ ቱስ ካድሬዎች!

Post by Abere » 12 Jul 2025, 21:10


ይህ የተናገረው ቅድመ-ተረኞች ሳይመጡ። ከሿሿ ኢትዮጵያ ሱሴዎች በፊት ይመስለኛል። እኔ በዚህ ሰውዬ አገላለጽ አልስማማም። የተሳሳተ አረዳድ ነው ያለው ባይነኝ። የተሰረቀ አይመለስም የማለት ያህል ነው። ሌባው እስከታወቀ ድረስ በማንኛውም አግባብ ማስመለስ ይቻላል። አሰብ የኢትዮጵያ ተፈጥሮአዊ እና ህጋዊ አካል ነው። ይህ ደግሞ በበርካታ ተቃዋሚ ፓርቲዎች፤ ምሁራን፤ የታሪክ ምሁራን የተነሳ እና ነፍስ ዘርቶ ያለ ጥያቄ ነው። በእርግጥ ጉዳዩ በሰላም ቢፈታ ጥሩ ነበር። በጦርነት መቋጨቱ አይቀሬ ነው - ባይነኝ። ነገር ግን እኔ በፍጹም በሻዕብያ እና በኦነግ-ብልጽግና መካከል ጦርነት ይኖራ በአሰብ ጉዳይ ብየ አላምንም። ኦነግ አብይ እና ሻዕብያ ተጣሉ ማለት ፈረስ እና ጥሬ ተጣሉ እንደማለት ነው - ፀረ-ኢትዮጵያ ናቸው። ነገር ግን ኢትዮጵያዊ መሪ እና ህዝብ አንድ ሲሆን የተዳፈነው የአሰብ ቦንብ ይፈነዳል።

ከዚህ ውጭ ሰውየው የሰጠው ትንታኔ ድርቅ ያለ ነው - ጉዳዩን 360 ዲግሪ አላየውም -ግግም ያለ አገላለጽነው።


Axumezana
Senior Member
Posts: 17548
Joined: 27 Jan 2020, 23:15

Re: “አማራ አማራ አትበሉ፤ አሰብ አሰብ በሉ” ለሚሉት ቱስ ቱስ ካድሬዎች!

Post by Axumezana » 13 Jul 2025, 03:42

ህግን እናክብር ከተባለ ሟቹ ወንድማችን ትክክል ነው። ህግ ግን በጉልበተኛ ቁጥጥር ስር እንዲሆን የታወቀ ነው!

Selam/
Senior Member
Posts: 15624
Joined: 04 Aug 2018, 13:15

Re: “አማራ አማራ አትበሉ፤ አሰብ አሰብ በሉ” ለሚሉት ቱስ ቱስ ካድሬዎች!

Post by Selam/ » 13 Jul 2025, 07:24

እጨጌ ዓይጠ መጎጡ

ህግ የፈጣሪ ነው “የሞራል justice governs” ስትል ከርመህ፣ ወደ ተመሳቀለው የምድር አሰራር ተመልሰህ እንደ ትራዘማከስ “ህግ በጉልበተኞች ስር ነች” ብለህ አረፍከው። ያ አፈር የበላው ኮምሬድህ ኢትዮ አሽ the winner takes it all ይል ነበር፣ ታዲያ ተሸናፊነቱ ወደእርሱ በኩል ሲያዘነብል፣ ደም ፍላቱ አናቱ ላይ ወጥቶበት ከመረጃ ኮብልሎ ሄዶ ውቅሮ ላይ በአፍጢሙ ተደፋ። The winner took him away too.

ሲዖሉ ይቅለለውና፣ ካላሽንኮቭ በአህያ ጭነን፣ ዛላንመበሳንና ባድሜን ተሻግረን ሻዕቢያን ድባቅ መተናታል ያለው ጉርጡ አለቃህ ደግሞ ሰራዊቱን አፈግፍግ ብሎ ሲያበቃ፣ ወደቡን አንፈልገውም የግመል መጠጫ ሆኖ ማየት ነው የምንመኘው ብሎ ህግን ዓየር ላይ መበተኑስ እንዴት ይረሳል? እናንተ ወያኔዎች ስለ ህግ ያላችሁ አተረጓጎም ልክ እንደ ጨረቃ የአቀማመጥ ሁኔታ ስለሚለዋወጥ፣ ምላሳችሁን የሚያመረቅዘውን ቁስላችሁን ለመላሻ ብቻ ብትጠቀሙበት ይሻላል። ወለንጪቲን!

አፍሪካ ሁልጊዜ የምትናወጠው፣ ህግ በጉልበተኞች ስለምትደፈቅ ነው። ታዲያ ይኸንን አሰራር ብቻ አሜን ብሎ ተቀብሎ ዕንቅልፉን የሚለጥጠው ካድሬና ልሂቅ ከርሳም እንሰሳ ነው።

“The Arc of the Moral Universe is Long, But it Bends Toward Justice.” MLK



Abere
Senior Member
Posts: 13971
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

Re: “አማራ አማራ አትበሉ፤ አሰብ አሰብ በሉ” ለሚሉት ቱስ ቱስ ካድሬዎች!

Post by Abere » 13 Jul 2025, 11:23

በህግ-ዐልባ ወያኔ ዘመን ስለ ተሰረቀ የኢትዮጵያ ግዛት ስለሆነው አሰብ ነው የምናወራው። ኢትዮጵያ መንግስትም ህገ-መንግስትም አልነበራትም። ምናልባት አንተ ወያኔ መንግስት ነው ብለህ የምታምን ከሆነ የደደቢትወይም የህልመኛዋ ዐባይ-ትግራይ ሪፓብሊክ ሊሆን ይችላል። :lol:
Axumezana wrote:
13 Jul 2025, 03:42
ህግን እናክብር ከተባለ ሟቹ ወንድማችን ትክክል ነው። ህግ ግን በጉልበተኛ ቁጥጥር ስር እንዲሆን የታወቀ ነው!

Post Reply