Re: I wish every success and good health to PM Abiy in the next few months
We Eritreans don't have friends or enemies, only permanent interests.

Re: I wish every success and good health to PM Abiy in the next few months
አበረ:
አብይ ችግር የለበትም አላልኩም... ግን በአሁኑ ተጨባጭ ሁኔታ: ወያኔና ሻዕብያ ተባብረው እንደገና ከ34 ዓመታት በሗላ ለሁለተኛ ጊዜ አገራችንን ሊያወድሙ እየዛቱ ባለበት ወቅት አብይን ከመደገፍ ውጭ አማራጭ የለም:: በተለይም አማራ ነኝ የሚል ሁሉ የወያኔወችን የ 'ብቀላ' ዛቻ በቀላሉ ማየት የለበትም:: አንድ ሰው ሁኔታወች ሲቀየሩ አካሄዱን ካላስተካከለ ዋጋ ቢስ ነው:: አላማና ግብ በየጊዜው updated መሆን አለባቸው ... እንደተጨባጩ ሁኔታ... ደግሞም አብይ በኢትዮጵያ ካየናቸው መሪወች ስናነፃፀረው በጣም የተሻለ ነው: ይህን ያክልም መጥፎ መሪ አይደለም::

Abere wrote: ↑05 Jul 2025, 19:02ይመር፥
በአንተ ቤት ወሎየዋ አይሻ ሰይድ ሰው አይደለችም። ለአንተ ሰው ማለት ኦሮሙማ ብቻ ነው። አማራ ሰው አይደለም - ለአንተ። በአብይ አህመድ በወሎ፤በጎጃም፤ በሸዋ፤ በጎንደር፤ በወለጋ፤ አሩሲ ወዘተ ደማቸው የፈሰሰ በግፍ የተጨፈጨፉት፤ በቢላዎ የታረዱት፤ ተዘቅዝቀው የተሰቀሉት፤ የተፈናቀሉት ህጻናት፤ እናቶች፤ አዛውንት ሰው አይደሉም።
አዎ፤ ለሰው ልጆች ሁሉ በጎ መመኘት፤ ስለ ሰላም እና ብጎ ነገር ለግለሰብ ይሁን ለአገር ወደ እግዚአብሄር መለመን የትክክለኛ ሰው ምግባር ነው። እኔ ለማንም ሰው መጥፎ አልመኝም። ጥያቄየ ግን ቢያንስ ዝም ማለት ሲገባህ እንደት በአማራ ህዝብ ብትሳለቅ ነው አብይ አህመድ መልካም እንደ ሰራ ሁሉ " ሺ አመት ንገሥ" ብለህ ወደ እግዚአብሄር የምትማጸነው? እግዚአብሄር የደግ ሰው እና የክፉ ሰው መንገድ የማያውቅ መስሎህ ነው? እግዚአብሄር እኮ የልበ አምላክ ዳዊት እና የሄሮድስን ማንነት እና ዕጣ ፈንታ የሚያውቅ አምላክ ነው። ቢያንስ ቢያንስ ወደ ብጎ ህሌና እንድመልሰው፤ እጁ በደም እንዳለላ የቀላች በመሆኑ ወደ ንስሃ እንደ መለስ፤ ለመንበረ ስልጣን ብቁ አለመሆኑን እንድረዳ መጸለይ ሲገባህ - ለኢትዮጵያ የግፍ እና የመከራ ዘመን ትመኛለህ።
ሄሮዶስ ለስልጣን እጅግ ስግብግብ ስለነበረ፤ ህጻኑ እየሱስ ክርስቶስ ንግስናዬን ይነጥቀኛል በማለት፤ ክርስቶስን ያገኘ ምስሎት በአቦ ሰጥ በርካታ ሺ ተባዕት ህጻናት አረደ። ይህ እኩይ ስራ እግዚአብሄር አስቀየመው እና ገና ክርስቶስ የ2 አመት ህጻን እያለ፤ ሄሮዶስ በቁሙ ሰውነቱ በትል ተበልቶ ብጥስጥሱ ወጥቶ ወደ ማያቀረው አለም ሄደ። ታዲያ በዚያን ጊዜ ልክ እንደ አንተ ይመር አይነቶች በርካታ ውታፍ-ነቃዮች ነበሩ። በመምከር እና በመገሰጽ ወይም ወደ በጎ ህሌናው እንድመለስ በመጸለይ ፋንታ ለእኩይ ስራ ይገፋፉት ነበር።
አዎ! የአይሻ ሰይድ እና የዕልፍ አዕላፋት አማራ ህጻንት ነፍስ ከመቃብር እየጮኸ ወደ ህያው እግዚአብሄር ይጣራል።