DefendTheTruth wrote: ↑02 Jul 2025, 16:15
ድሮ እንደዚህ ስባል እሰማ ነበር፣ እኔንም እንደዚህ ብሎ የምተርቡኝ "ጓደኞች" ነበሩኝ፣ ትርጉሙን ግን በደምብ ተረድቻለሁ ለማለት አልደፍርም። ይህን ጋዜጠኛ አየሁኝ ና አባባሉ ትዝ አለኝ። ስለምናገረዉ ጉዳይ በደምብ የተረዳ አይመስለኝም።
ይህን ቃለ መጠይቅ ኣዳመጥኩኝ።
በኣንድ በኩል ከእርስ በእርስ መዋጋት ንትርክ ተላቆ ስለ ዕዉቀት ማዉጋት፣ መወያየት ኣቅጣጫ ማየት፣ ማሳየት በጎ ነዉ።
ያለፉትን የሃገር መንግስታትን ስራዎች ከዜሮ በታች ወይም ኔጋቲቭ ኣድርጎ ማዉራት የተለመደ ነበር ማለት ይቻላል።
ፕሮፌሰር ብርሃኑ የኣፄ ሀይለስላሴ ዘመን፣ የደርግ ዘመን፣ እና የኢህኣዲግ ዘመን ትምህርትን ለማስፋፋት ጥረቶች እንደነበሩ መናገሩ ኢትዮጵያ ዉስጥ መንግስት ጠንካራም ሆነ ደካማ ትምህርትን ለማስፋፋት ቀጣይነት የነበራቸዉ ጥረቶች መኖራቸዉን ያመለክታል።
እንደዚህ ዐይነት ቀጣይነት ደካማዉን እና ጠንካራዉን ፈትሾ ለማጠናከር ይረዳል።
በሌላ በኩል የዉይይቱ ይዘት ለእኔ ኣስደንጋጭ ነዉ። ለዚህም ነዉ ያለኝን ሀሳብ ማካፈል የፈለኩኝ።
መልሼ መላልሼ ኣስቤ የጋዜጠኛዉን ርዕሶች መነሻዎች እና መድረሻዎች ምንድናቸዉ ኣስባለኝ።
ከዚህ በፊት የታዘብኩትን ሁለት ቁምነገር የሆኑ ዉይይቶችን ኣስታወሰኝ።
ኣንዱ ቁምነገር እዚሁ ፎረም ላይ ተነስቶ የዉይይቱ ይዘት እስከ መጨረሻዉ የተማሩት ኢትዮጵያዊያን በኣፍታ ኣንድ አፍ መናገር ኣለመቻላቸዉ ነበር። ርዕሱም ፒ ኤች ዲ ምን ማለት ነዉ የሚል ነበር። ይህን መግለጽ ክርክር ሲሆን ኣስቡት።
ሁለተኛዉ ቁምነገር በቅርቡ ፒ ኤች ዲ ያገኘ ማንኛዉም ኢትዮጵያዊ በህይወት ዘመኑ ብያንስ ኣንድ የሳይንስ ጥናት ሰርቶ ብያሳትም በጎ ነዉ ብዬ እዚሁ ፈረም ላይ የጻፍኩኝ ነዉ።
ሀሳቤን የበለጠ ለማስረዳት እያሰላሰልኩ እያለሁ ነዉ ይህን ዉይይት ያየሁኝ።
እዚህ ዉይይት ዉስጥ ሁለቱም በኣንድ ኣፍታ በኣንድ አፍ የሰዉ ልጅ የዕዉቀት ዉቅያኖስ ኣንድ ነዉ እንደማለት መከራከር ሆነ። የዕዉቀት ዉቅያኖስ ያልኩኝ በእንግልዘኛ ቦዲ ኦፍ ኖዉሌጅ የሚባለዉን ነዉ።
ፒ ኤች ዲ የማግኘት ዕዉቅና መነሻዉ ወይም መጀመርያዉ ወይም ኦሪጅኑ የኣንድ ሰዉ ኣዕምሮ ሆኖ፣ መሆኑ በፍሮፌሰሮች እና ሳይንቲስቶች ተመስክሮለት፣ በሳይንስ መጽሔት ዉስጥ ታትሞ እንደ ትንሽ ጠብታ ወደ ዕዉቀት ዉቅያኖስ የሚወረወር ኣዲስ ዕዉቀትን የማበርከት ችሎታ ነዉ ማለት ይቻላል። ምስክርነቱ ኣንዴ ኣዲስ ዕዉቀትን ማበርከት የቻለ በቀሪዉ የህይወት ዘመኑ ኣዳዲስ ዕዉቀትን እያበረከተ ሊኖር ይችላል ማለት ነዉ።
የዕዉቀት ዉቅያኖስ የአሜሪካ ወይም የቻይና ወይም የህንድ ወይም የኢትዮጵያ ወይም የሌላ ሃገር ሳይሆን የሰዉ ልጅ ነዉ።
እኔ በቅርቡ እዚህ ፎረም ላይ የጻፍኩኝ ጥሪ የሰዉ ልጅ የዕዉቀት ዉቅያኖስ ዉስጥ የኢትዮጵያዊያን ሳይንትስቶች ጠብታዎች እንዲበዙ ምርምር የመስራት ችሎታቸዉ የተመሰከላቸዉ ወይም ፒ ኤች ዲ ያገኙ በህይወት ዘመናቸዉ ብያንስ ኣንድ ጠብታ ይጨምሩ የሚል ነዉ።
ይህ እየተጠናከረ ሲሄድ፣ የኢትዮጵያዊያን ኣስተዋጽኦዎች እየጎሉ ሲሄድ፣ ሃገር ጠንካራ ምርምር እያካሄደች ነዉ ይባላል።
በቅርቡ በኣንድ የምርምር ረድፍ ቻይና ለመጀመርያ ግዜ ከኣሜሪካ ቀደመች የሚል ዜና ነበረ።
ይህ ማለት ዕዉቀቱ የቻይና ነዉ ማለት ሳይሆን በቻይና ዩኒቨርዚቲዎች ዉስጥ የሚስሩ ተመራማሪዎች እንግልዝ ሃገር ዉስጥ በሚታተም ኔቸር የተባለ በጣም ታዋቂ የሳይንስ መጽሔት ዉስጥ ያበረከቱት ኣዳዲስ ሀሳቦች በአሜርካ ዩኒቨርዚቲዎች የሚሰሩ ተመራማሪዎች ካበረከቱት በለጠ ማለት ነዉ።
በቅርቡ ለብቻዬ ሳሰላስል እዚህ ፎረም ዉስጥ ኣልፎ ኣልፎ የሚጻፉት ኣዳዲስ ሀሳቦች የአሜሪካዉ ሃርቫርድ ዩኒቨርዚቲ ያልደረሰባቸዉ ዕዉቀት ነዉ ብዬ በዚህ ረገድ የኤልያስ ክፍሌ ዩኒቨርዚቲ ከሃርቫርድ ዩኒቨርዚቲ ይበልጣል ኣልኩኝ። ለራሴ።
የዕዉቀቱ ጥልቀት ምን ያህል ለብዙዎች መገለጡን ባላዉቅም ሃርቫርድ ዩኒቨርዚቲ ስለ መጀመርያዉ ሬይነሳንስ በደንብ የምያዉቅ ቢሆንም ስለ ሁለተኛዉ ሬይነሳንስ የኤልያስ ክፍሌ ዩኒቨርዚቲ ያህል ኣያዉቅም ብዬ መከራከር እችላለሁ። ለምሳሌ ያህል ስለ ኩት፣ ኩረት፣ ከት የተጻፈዉን መጥቀስ ይቻላል።
ይህ ኣዲስ ማስተዋል ከታተመ ቀን ጀምሮ የሰዉ ልጅ የዕዉቀት ዉቅያኖስ ዉስጥ ጠብ ብሏል።
የሰዉ ልጅ የዕዉቀት ዉቅያኖስ ዉስጥ ዕዉቀትን መፈለግ በጣም ፈታኝ ስራ ነዉ። ፒ ኤች ዲን ለማግኘት የሚሰራ ሰዉ ኣንዱ ትልቁ ፈተናዉ የምርምር ችሎታ ዕዉቅና ለማግኘት መጀመርያ ኣዲስ ሀሳብን ያመነጨዉ የተመራማሪዉ ኣዕምሮ መሆኑን ማረጋገጥ ነዉ። ለዚህ ፈተና ሊትሬቸር ሪቪዉን ማለፍ ኣለበት።
ጉግል ሳይፈጠር በፊት ርፈረንስ የተባሉትን የምርምር ኣመልካቾችን ማጥናት ትልቅ ስራ ነበረ።
ጉግል የዕዉቀት ዉቅያኖስን ለመቃኘት የምያስችል ኣዲስ ቴክኖሎጂ ነዉ።
ካልተሳሳትኩ ጉግል ዉስጥ የታተመ ዕዉቀት ሲፈለግ ይህ የአሜሪካ ዕዉቀት ነዉ፣ ይህ የቻይና ነዉ፣ ይህ የኢትዮጵያ ነዉ ብሎ ደርድሮ ኣይመልስም።
ኣዲስ ዕዉቀት የመነጨዉ አሜሪካ ዉስጥ ሆነ ኢትዮጵያ ዉስጥ ከታተመ ቀን ጀምሮ የሰዉ ልጅ ዕዉቀት ነዉ። የታተመ ከሆነ ኣልታወቀም ማለት የታተመዉ ዕዉቀት ዉቅያኖሱ ዉስጥ ዬለም ማለት ኣይዴለም።
ስለዚህ በእኔ አስተሳሰብ መሠረታዊ ጥያቄ መሆን ያለበት የሰዉ ልጅ የዕዉቀት ዉቅያኖስ ዉስጥ ምን ያህል ጠብታዎችን ጨምረናል ነዉ።
ለዚህ ደግሞ ሜዳዉም ይሀዉ፣ ፈረሱም ይሀዉ እንደሚባለዉ ነዉ። በአለም ዙርያ ያሉ ተመራማሪዎች ኣዲስ ዕዉቀትን እንግሊዝ ሃገር የሚታተመዉ ታዋቂ የሳይንስ መጽሔት ዉስጥ ማሳተም ከቻሉ ኢትዮጵያዊያን ተመራማሪዎችም ማሳተም ይችለሉ። ይህ የሳይንስ መጽሔት ኣድሎ ያለዉ ከሆነ ተቀባይነትን ማግኘት የሚችልን የሳይንስ መጽሔት የኢትዮጵያ የሳይንስ ድርጅት መጀመር ይችላል። ይህ ሜዳዉ ነዉ።
ፈረሱ ደግሞ የኢትዮጵያ ዩኒቨርዚቲዎች በሙሉ ሊሆኑ ይችላሉ።
እኔ የማዉቃቸዉ የተከበሩ ኣስተማሪዎች ልጆችዋን በፍቅር እንደምታሳድግ የተከበረች እናት ናቸዉ። የተከበረች እናት ቤት ያፈራዉን ለፍታ ለልጆችዋ ኣቅርባ በበሉልኝ የምትል ናት። የሚጠግቡ ኣይመስላትም። በደንብ ቢበሉላት በደንብ የምያድጉላት መሆኑን ነዉ የምታዉቀዉ።
የተከበረ አስተማሪም የምያስተምራቸዉን ዕድሜ ጠገብ ያልሆኑ ተማሪዎቹን ከዕዉቀት ዉቅያኖስ እየጨለፈ ምነዉ የበለጠ ባወቁልኝ ባይ ነዉ።
እኔ እንደሚገባኝ ከሆነ የትምህርት ምንስቴር ለዚህ ሁሉ ሂደት ፕሮቶኮልን ማስተካከል ነዉ።
ጋዜጠኛዉ ይህቺን መጣጥፍ ኣንብቦ ከአፉ የወጡትን አረፍተ ነገሮች ሁሉ እንደገና ኣዳምጧቸዉ፣ በደንብ ኣጥንቷቸዉ፣ ሌላ ቃል መጠይቅ ማድረግ ይችላል?
እንደ እኔ ዐይነት ኣዳማጮች ያልገባንን እንዲገቡን ለማድረግ ያህል።