Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
DefendTheTruth
Senior Member
Posts: 12459
Joined: 08 Mar 2014, 16:32

"ጥራዝ ነጠቅ" ማለት ምን ማለት ነዉ?

Post by DefendTheTruth » 02 Jul 2025, 16:15

ድሮ እንደዚህ ስባል እሰማ ነበር፣ እኔንም እንደዚህ ብሎ የምተርቡኝ "ጓደኞች" ነበሩኝ፣ ትርጉሙን ግን በደምብ ተረድቻለሁ ለማለት አልደፍርም። ይህን ጋዜጠኛ አየሁኝ ና አባባሉ ትዝ አለኝ። ስለምናገረዉ ጉዳይ በደምብ የተረዳ አይመስለኝም።


Abere
Senior Member
Posts: 13922
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

Re: "ጥራዝ ነጠቅ" ማለት ምን ማለት ነዉ?

Post by Abere » 02 Jul 2025, 16:28

ለጥራዝ ነጠቅ ዋና ምሳሌ እራሱ ብርሃኑ ነጋ ነው። የ1960ዎቹ ትውልድ የሆነው ብርሃኑ ነጋ ገና ትንሽ ፊደል ጠንቅሎ እንደ ካቲካል ጭንቅላቱ ሲወጣ የኮሙኒዝም ተከታይ በመሆን ኢትዮጵያን ወደ ደም-ዐባላ ስርዐት ያስገባ ነው። ትንሽ እውቀት አደገኛ ናት። ለነገሩ ብርሃኑ ነጋ እና ወንዝ ውስጥ ያለ ደንጋይ አንድ ናቸው - አይገባቸውም። ትምህርቱ አልተዋኸደውም - ዛሬ የናዚ ኦሮሙማ ግብረ-ሃይል በመሆን በትውልድ ላይ የዘር ማጥፋት እየፈጸመ ያለ ሰው ነው። ብርሃኑን ስለ አንድ አካዳሚክ ንድፈ-ሀሳብ ከምትጠይቀው የዛሬ ስድስት ወር ምሳውን ምን እንደ በላ ብትጠይቀው ያስታውሳል - ወይም መስተንግዶውን ያብራርሃል። ሆድ ዕቃ እንጅ ጭንቅላት የለውም።

sesame
Member+
Posts: 7384
Joined: 28 Feb 2013, 17:55

Re: "ጥራዝ ነጠቅ" ማለት ምን ማለት ነዉ?

Post by sesame » 02 Jul 2025, 18:06

The best example of ጥራዝ ነጠቅ is Abiy Ahmed, who pontificates about matters way above his head using little facts garnered from Wikipedia. Alternatively, he might, therefore, be called ዊኪፒድያ ነጠቅ:: :lol: :lol: :lol: :lol:

Selam/
Senior Member
Posts: 15512
Joined: 04 Aug 2018, 13:15

Re: "ጥራዝ ነጠቅ" ማለት ምን ማለት ነዉ?

Post by Selam/ » 02 Jul 2025, 21:18

የጥራዝ ነጠቅነትን ትርጉም ለማወቅ በእናቶችና በህፃናቶች ደም የተጨማለቀውን ሜንጫህን አናግረው!










Affable
Member
Posts: 457
Joined: 15 Jul 2023, 13:21

Re: "ጥራዝ ነጠቅ" ማለት ምን ማለት ነዉ?

Post by Affable » 02 Jul 2025, 21:22

ከዘጠና ፐርሰንት በላይ የ ER ደንበኞች የጥራዝ ነጠቅ ቃል በቃል ትርጉም ናቸው። Eden የጭቃ ጅራፎአን ከመምዘዟ በፊት አንድ ነገር ግልፅ ማረግ እፈልጋለሁ። ከዛ ቡድን ውስጥ አልመድባትም። እሷ የ ትራይባል ፓለቲከኞች ሰለባ ነች። ጡጦ እና የትራይባል አሉባልታ በአንድ ወቅት ነው የጋቷት። አይፈረድባትም።

Horus
Senior Member+
Posts: 36872
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: "ጥራዝ ነጠቅ" ማለት ምን ማለት ነዉ?

Post by Horus » 02 Jul 2025, 21:50

ይሄ መሃይም ጠያቂ ነው! ሳይንስ ምን ማለት እንደ ሆነ እንኳን አያውቅም! ሳይንሳዊ እውቀት ምን እንደ ሆነ አያውቅም። ይህ ደደብ ባህላዊ መድሃኒትና የኬሚስትሪ ሳይንስ እንዴት እንደ ሚያያዙ ብቻ ሳይሆን ሳይንሳዊ ምርምር እንዴት እንደ ሚደረግ ጉግል ማድረግ ማድረግ ያልቻለ ጠያቂ ነው። እውቀት የሚያድገው እንዴት ነው ብሎ እንኳን መጠየቅ የማይችል ደደብ ነው!


Naga Tuma
Member+
Posts: 6201
Joined: 24 Apr 2007, 00:27

Re: "ጥራዝ ነጠቅ" ማለት ምን ማለት ነዉ?

Post by Naga Tuma » 02 Jul 2025, 23:12

ጥራዝ ነጠቅ ማለትማ የፖለትካ ጥርሴን የነቀልኩበት ስለሆነ ጥያቄዉን ለመመለስ ልሞክር።

ጥራዝ ማለት የተጠረዘ ወይም የታተመ ማለት ነዉ። ነጠቅ ማለት የታተመዉን ኣይቶ ብቻ እዉነት ይሁን ስህተት ሳያሰላስል እና ሳያረጋግጥ እዉነት ነዉ ብሎ መቀበል ነዉ።

ለምሳሌ ኮሎኒ ተብሎ ከታተመ፣ የሰባት ቀናት ተዓምር ተብሎ ከታተመ፣ የተባረከ እና የተረገመ ተብሎ ከታተመ የተጠረዘ ነዉ እና ተቀብያለሁ ማለት ነዉ።

ጥራዝ ነጠቅ ያልሆነ ኮሎኒ ማለትን ስያነብ ቃልቻ ቃሉን ኮሎኒ ያደርጋል? ፈወሰ ፈይሳን ኮሎኒ ያደርጋል? እኩል የተፈጠሩት እንዴት ነዉ የተባረከ እና የተረገመ የሚባለዉ ብሎ ከመቀበል በፊት፣ ጥራዙን ነጠቅ ሳያደርግ በፊት፣ ኣስቦ፣ ኣሰላስሎ ይጠይቃል።

ጥያቄዉ መልስ ካላገኘ ማብራርያ ልጨምርበት እችላለሁ።

DefendTheTruth
Senior Member
Posts: 12459
Joined: 08 Mar 2014, 16:32

Re: "ጥራዝ ነጠቅ" ማለት ምን ማለት ነዉ?

Post by DefendTheTruth » 03 Jul 2025, 13:33

Abere wrote:
02 Jul 2025, 16:28
ለጥራዝ ነጠቅ ዋና ምሳሌ እራሱ ብርሃኑ ነጋ ነው። የ1960ዎቹ ትውልድ የሆነው ብርሃኑ ነጋ ገና ትንሽ ፊደል ጠንቅሎ እንደ ካቲካል ጭንቅላቱ ሲወጣ የኮሙኒዝም ተከታይ በመሆን ኢትዮጵያን ወደ ደም-ዐባላ ስርዐት ያስገባ ነው። ትንሽ እውቀት አደገኛ ናት። ለነገሩ ብርሃኑ ነጋ እና ወንዝ ውስጥ ያለ ደንጋይ አንድ ናቸው - አይገባቸውም። ትምህርቱ አልተዋኸደውም - ዛሬ የናዚ ኦሮሙማ ግብረ-ሃይል በመሆን በትውልድ ላይ የዘር ማጥፋት እየፈጸመ ያለ ሰው ነው። ብርሃኑን ስለ አንድ አካዳሚክ ንድፈ-ሀሳብ ከምትጠይቀው የዛሬ ስድስት ወር ምሳውን ምን እንደ በላ ብትጠይቀው ያስታውሳል - ወይም መስተንግዶውን ያብራርሃል። ሆድ ዕቃ እንጅ ጭንቅላት የለውም።
Abere,

እንኳን ሌላ ሰዉ ራስህን ማሳመን አትችልም በምትሞጫጭራቸዉ ትርክምርኪ ሞነጫጭሮችህ። ፕርፌሰር ብርሃኑ ነጋን አንድ ወቅት ላይ ተቀዉሜዉ ነበር፣ ያም በአሜሪካ ዩኒቨርሲቲ ማስተማሩን ትቶ ወደ ኢርትሪያ በረሃ የኢትዮጵያን መንግስት በጠመንጃ አፈ-ሙዝ ለመስወገድ በምል ህሳቤ። ያኔ የኔ ምልከታ የነበረዉ በትምህርት ወይም በእዉቀት እንጂ በጠመንጃ መንግስትን መገልበጥ ዘላቂ መብቴ አይሆንም የምል ግምት ስለነበረኝ ነዉ።

ከዚያ ቦኃላ ለዉጡ መጣ ና ተቃዋሚዎች ወደ አገር ቤት ገብቶ በነፃነት አለማቸዉን ማራመድ ይችላሉ ተብሎ ተፈቅዶ እነ ፕሮፌሰር ብርሃኑም ወደ አገር ቤት መግበትን መርጦ ወደ አገር ቤት ገቡ። ፕሮፌሰሩ ገና ቦሌ አየር ማረፊያ ደርሶ ቃለ መጠይቅ አድርጎ ነበር፣ እስከ አሁን ትዝ የምለኝ። ከተናገራቸዉ ነጥቦች ሁሉ ትዝ የምለኝ "አሁን ጊዜዉ ና ሁኔታዉ ስለ ስልጣን የምንሽቀዳደምበት ሳይሆን፣ አገሪቷ ላይ የተገረጠዉን የመበታተን አደጋን ለምግታት መረባረብ ያለብን ጊዜ ዉስጥ ነን" ብሎ መናገሩ በጊዜዉ ትልቅ አድናቆት ለሱ እንድኖረኝ አድርጎዋል። የአገር መሪ ማለት እንደዚህ ከራስ ጥቅም በፊት የአገርን ጥቅም ማስቀደም መቻል ስለሆነ።

ኢትዮጵያ ላይ ያኔ በጣም የምያስፈራ ሁኔታ ተጋርጦባት ነበር። ሁሉም ብላዉን ስሎ ትራስጌዉ ስር ያስቀመጠበት ጊዜ ነበር ብባል ማጋነን አይደለም ና። በአንፃሩ እነ ዳዉድ ኢብሳ ተብዬዉ ፖለቲከኛ ግን "ማን ማንን ያስፈታል" የምል አጉል ድንፋታ ዉስጥ ነበሩ። ጃንጆ ሞሃመድም በአቅሟ "እኔ ሁለተኛ መንግስት ነኝ" የምል ትብዕት ታራምድ ነበር። ሁሉም አለፈ አሁን ላይ። ኢትዮጵያ በጣም የተሻለ ቦታ ሆናለች፤ ዜጎች ሕልማቸዉን ለማሟላት የምተጉበት ሁኔታ ተፈጥሮዋል፣ የዞረባቸዉ እንደ የጎጃም ወሮበላዎች አሁንም ለፍቶ እንደመብላት ዘርፎ መብላትን መርጦ ደፋ ቀና ይላሉ። የኦሮሚያ ሻኔም ይህንኑን ተልካሻ ተልዕኮ አንግቦ ደፋ ቀና ይላል። ወያኔም ወደ ስልጣን በጠመንጃ አፈሙዝ እመለሳለሁ ብላ የሻቢያ አሽከር ሆና ተቀጥራለች። የትም አይደርሱም።

ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የአገር በለዉለታ ተብሎ ስሙን ከፍ አድርጎ ለማስፃፍ ይተጋል፣ የኢትዮጵያን ስርዓተ ትምህርት ለማቃናት ሌተ ቀን ይለፋል፣ የበኩሉን ለማበርከት ይታክታል። አንድ ቀን ስሙ ከፍ ብሎ መፃፉ አይቀሬ ነዉ።

የአንተ ብጤ ቱልቱላዎች እሱን ስኮንኑ ዉሎ ብያድሩ ማንን ይደንቃል? ዉድቀታችሁን አልቀበልም ማለታችዉ እንጂ ነገሩ እኮ በግልፅ ተፅፎ ተሰቅሎዋል። ዳክር እዛዉ ላይ!

ብርሃኑ ነጋን ልትደርስበት በምንም አይነት አትችልም! ዋጠዉ!

Tiago
Member
Posts: 2712
Joined: 30 Jul 2018, 02:09

Re: "ጥራዝ ነጠቅ" ማለት ምን ማለት ነዉ?

Post by Tiago » 03 Jul 2025, 14:14

ጥራዝ ነጠቅ- superficially knowledgeable

ካለ በቂ ችሎታና እውቀት ገብቶ የሚፈተፍት ማለት ነው

አዋቂ ወይም የተማረ ለመባል የእንግሊዘኛ ቃላቶች በአማርኛ ላይ ጣል ጣል ማድረግ (የአማርኛ ቃል ያልሆነ የሳይንስ ወይም የቴክኖሎጂ ቃላትን አይመለከትም)

አብይ አህመድ በምክር ቤት ተወካዮች አድናቆትና ጭብጨባ የሚያገኘው አስፈላጊ ያልሆኑ የባእድ ቃላቶችን በመወርወር ነው
አብይ አስተማሪዎች ሐኪሞች ሰብስቦ ምንም በቂ እውቀት ሳይኖረው
ስለውሃና ተውሳክ በማቡካት ጥራዝ ነጠቅነቱን አረጋግጧል
:lol: :lol: :lol: I tell you no lies.

DefendTheTruth
Senior Member
Posts: 12459
Joined: 08 Mar 2014, 16:32

Re: "ጥራዝ ነጠቅ" ማለት ምን ማለት ነዉ?

Post by DefendTheTruth » 03 Jul 2025, 14:32

Tiago wrote:
03 Jul 2025, 14:14
ጥራዝ ነጠቅ- superficially knowledgeable

I tell you no lies.


Why you add that? I didn't expect that you are going to tell me a lie, but you are for some reason no self-confident, yeah?

If someone of superficial knowledge can also build a nation from bottom up, like Abiy Ahmed is doing in Ethiopia, then the term is essentially not bad at all, I assume.

አስመሳዮች!

Affable
Member
Posts: 457
Joined: 15 Jul 2023, 13:21

Re: "ጥራዝ ነጠቅ" ማለት ምን ማለት ነዉ?

Post by Affable » 03 Jul 2025, 14:58

ብርሀኑ ነጋና የህወአት ካድሬዎች ፍቅር አይጋሩም።

Selam/
Senior Member
Posts: 15512
Joined: 04 Aug 2018, 13:15

Re: "ጥራዝ ነጠቅ" ማለት ምን ማለት ነዉ?

Post by Selam/ » 03 Jul 2025, 15:58

አይ ቱስ ቱስ ጭልፊቱ

አንተም ሰው ሆነህ፣ ስለ ጥራዝ ነጠቅነት ሃሳብ መስጠት አሰኘህ። ቁሬማ!


viewtopic.php?t=303030
Horus wrote:
02 Jul 2025, 21:50
ይሄ መሃይም ጠያቂ ነው! ሳይንስ ምን ማለት እንደ ሆነ እንኳን አያውቅም! ሳይንሳዊ እውቀት ምን እንደ ሆነ አያውቅም። ይህ ደደብ ባህላዊ መድሃኒትና የኬሚስትሪ ሳይንስ እንዴት እንደ ሚያያዙ ብቻ ሳይሆን ሳይንሳዊ ምርምር እንዴት እንደ ሚደረግ ጉግል ማድረግ ማድረግ ያልቻለ ጠያቂ ነው። እውቀት የሚያድገው እንዴት ነው ብሎ እንኳን መጠየቅ የማይችል ደደብ ነው!

Abere
Senior Member
Posts: 13922
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

Re: "ጥራዝ ነጠቅ" ማለት ምን ማለት ነዉ?

Post by Abere » 03 Jul 2025, 16:34

የአራዳ ልጆች ሲቀልዱ አልሰማህም እንዴ? :mrgreen: እንደ ጠጅ ቤት እንግሊዘኛ የሚነገርበት ቦታ የለም። እንግሊዘኛ ተናጋሪ ይበዛል። ሰካራም እንግሊዘኛ እየፈጠፈጠ አንድ 2 ቃላቶች የሚያውቃቸው ካለ ከዚያ በድፍረት ይማላበታል። የተማረ ይመስላል። ትምህርት የለም። ጠጅ ቤት ነው ት/ቤቱ። :lol:


Tiago wrote:
03 Jul 2025, 14:14
ጥራዝ ነጠቅ- superficially knowledgeable

ካለ በቂ ችሎታና እውቀት ገብቶ የሚፈተፍት ማለት ነው

አዋቂ ወይም የተማረ ለመባል የእንግሊዘኛ ቃላቶች በአማርኛ ላይ ጣል ጣል ማድረግ (የአማርኛ ቃል ያልሆነ የሳይንስ ወይም የቴክኖሎጂ ቃላትን አይመለከትም)

አብይ አህመድ በምክር ቤት ተወካዮች አድናቆትና ጭብጨባ የሚያገኘው አስፈላጊ ያልሆኑ የባእድ ቃላቶችን በመወርወር ነው
አብይ አስተማሪዎች ሐኪሞች ሰብስቦ ምንም በቂ እውቀት ሳይኖረው
ስለውሃና ተውሳክ በማቡካት ጥራዝ ነጠቅነቱን አረጋግጧል
:lol: :lol: :lol: I tell you no lies.

DefendTheTruth
Senior Member
Posts: 12459
Joined: 08 Mar 2014, 16:32

Re: "ጥራዝ ነጠቅ" ማለት ምን ማለት ነዉ?

Post by DefendTheTruth » 04 Jul 2025, 04:05

ሌላ ጥራዝ ነጠቅ?

አንድ ሰዉ ሚዲያ ላይ ወጥቶ ያምያሰራጨዉን በትንሹም ብሆን ግንዛቤ ሳይኖረዉ የአገኘዉን ነገር ሁሉ የምለቅ ከሆነ ምን ማስተላለፍ ፈልጎ ነዉ?

ይህ አፃፃፍ ምን ለማለት ነዉ? በቀለ ገርባ ይባላል፣ ሰዉዬዉ። በላቲን ፊደል ስፃፍ ደግሞ መሆን Bekele Gerba (in English) or Baqalaa Garbaa (in Afan Oromo) አለበት መሰለኝ፣ በእንግልዚኛም ሆነ በአፋን ኦሮሞ ይህ አባባል በምንም አይነት ተቀራራቢነት የለዉም። ሁሉን ነገር አርመንም አንዘልቅም። በቀለ ገርባ እንደሆነ ድሮ ነዉ፣ never disappoint to disappoint ብዬ የገለጽኩት፣ አሁንም አላሰፈረኝም።
Obbo bekale garba jawar mahammad irratti yaada kanne

Selam/
Senior Member
Posts: 15512
Joined: 04 Aug 2018, 13:15

Re: "ጥራዝ ነጠቅ" ማለት ምን ማለት ነዉ?

Post by Selam/ » 04 Jul 2025, 06:56

ካድሬው
መጠይቁ በአማርኛ የአንተ ማረሚያ በቁቤኛ፤ ስንቱን አረም ነቅለን እንዘልቃለን?

DefendTheTruth wrote:
04 Jul 2025, 04:05
ሌላ ጥራዝ ነጠቅ?

አንድ ሰዉ ሚዲያ ላይ ወጥቶ ያምያሰራጨዉን በትንሹም ብሆን ግንዛቤ ሳይኖረዉ የአገኘዉን ነገር ሁሉ የምለቅ ከሆነ ምን ማስተላለፍ ፈልጎ ነዉ?

ይህ አፃፃፍ ምን ለማለት ነዉ? በቀለ ገርባ ይባላል፣ ሰዉዬዉ። በላቲን ፊደል ስፃፍ ደግሞ መሆን Bekele Gerba (in English) or Baqalaa Garbaa (in Afan Oromo) አለበት መሰለኝ፣ በእንግልዚኛም ሆነ በአፋን ኦሮሞ ይህ አባባል በምንም አይነት ተቀራራቢነት የለዉም። ሁሉን ነገር አርመንም አንዘልቅም። በቀለ ገርባ እንደሆነ ድሮ ነዉ፣ never disappoint to disappoint ብዬ የገለጽኩት፣ አሁንም አላሰፈረኝም።
Obbo bekale garba jawar mahammad irratti yaada kanne

Naga Tuma
Member+
Posts: 6201
Joined: 24 Apr 2007, 00:27

Re: "ጥራዝ ነጠቅ" ማለት ምን ማለት ነዉ?

Post by Naga Tuma » 10 Jul 2025, 15:59

DefendTheTruth wrote:
02 Jul 2025, 16:15
ድሮ እንደዚህ ስባል እሰማ ነበር፣ እኔንም እንደዚህ ብሎ የምተርቡኝ "ጓደኞች" ነበሩኝ፣ ትርጉሙን ግን በደምብ ተረድቻለሁ ለማለት አልደፍርም። ይህን ጋዜጠኛ አየሁኝ ና አባባሉ ትዝ አለኝ። ስለምናገረዉ ጉዳይ በደምብ የተረዳ አይመስለኝም።

ይህን ቃለ መጠይቅ ኣዳመጥኩኝ።

በኣንድ በኩል ከእርስ በእርስ መዋጋት ንትርክ ተላቆ ስለ ዕዉቀት ማዉጋት፣ መወያየት ኣቅጣጫ ማየት፣ ማሳየት በጎ ነዉ።

ያለፉትን የሃገር መንግስታትን ስራዎች ከዜሮ በታች ወይም ኔጋቲቭ ኣድርጎ ማዉራት የተለመደ ነበር ማለት ይቻላል።

ፕሮፌሰር ብርሃኑ የኣፄ ሀይለስላሴ ዘመን፣ የደርግ ዘመን፣ እና የኢህኣዲግ ዘመን ትምህርትን ለማስፋፋት ጥረቶች እንደነበሩ መናገሩ ኢትዮጵያ ዉስጥ መንግስት ጠንካራም ሆነ ደካማ ትምህርትን ለማስፋፋት ቀጣይነት የነበራቸዉ ጥረቶች መኖራቸዉን ያመለክታል።

እንደዚህ ዐይነት ቀጣይነት ደካማዉን እና ጠንካራዉን ፈትሾ ለማጠናከር ይረዳል።

በሌላ በኩል የዉይይቱ ይዘት ለእኔ ኣስደንጋጭ ነዉ። ለዚህም ነዉ ያለኝን ሀሳብ ማካፈል የፈለኩኝ።

መልሼ መላልሼ ኣስቤ የጋዜጠኛዉን ርዕሶች መነሻዎች እና መድረሻዎች ምንድናቸዉ ኣስባለኝ።

ከዚህ በፊት የታዘብኩትን ሁለት ቁምነገር የሆኑ ዉይይቶችን ኣስታወሰኝ።

ኣንዱ ቁምነገር እዚሁ ፎረም ላይ ተነስቶ የዉይይቱ ይዘት እስከ መጨረሻዉ የተማሩት ኢትዮጵያዊያን በኣፍታ ኣንድ አፍ መናገር ኣለመቻላቸዉ ነበር። ርዕሱም ፒ ኤች ዲ ምን ማለት ነዉ የሚል ነበር። ይህን መግለጽ ክርክር ሲሆን ኣስቡት።

ሁለተኛዉ ቁምነገር በቅርቡ ፒ ኤች ዲ ያገኘ ማንኛዉም ኢትዮጵያዊ በህይወት ዘመኑ ብያንስ ኣንድ የሳይንስ ጥናት ሰርቶ ብያሳትም በጎ ነዉ ብዬ እዚሁ ፈረም ላይ የጻፍኩኝ ነዉ።

ሀሳቤን የበለጠ ለማስረዳት እያሰላሰልኩ እያለሁ ነዉ ይህን ዉይይት ያየሁኝ።

እዚህ ዉይይት ዉስጥ ሁለቱም በኣንድ ኣፍታ በኣንድ አፍ የሰዉ ልጅ የዕዉቀት ዉቅያኖስ ኣንድ ነዉ እንደማለት መከራከር ሆነ። የዕዉቀት ዉቅያኖስ ያልኩኝ በእንግልዘኛ ቦዲ ኦፍ ኖዉሌጅ የሚባለዉን ነዉ።

ፒ ኤች ዲ የማግኘት ዕዉቅና መነሻዉ ወይም መጀመርያዉ ወይም ኦሪጅኑ የኣንድ ሰዉ ኣዕምሮ ሆኖ፣ መሆኑ በፍሮፌሰሮች እና ሳይንቲስቶች ተመስክሮለት፣ በሳይንስ መጽሔት ዉስጥ ታትሞ እንደ ትንሽ ጠብታ ወደ ዕዉቀት ዉቅያኖስ የሚወረወር ኣዲስ ዕዉቀትን የማበርከት ችሎታ ነዉ ማለት ይቻላል። ምስክርነቱ ኣንዴ ኣዲስ ዕዉቀትን ማበርከት የቻለ በቀሪዉ የህይወት ዘመኑ ኣዳዲስ ዕዉቀትን እያበረከተ ሊኖር ይችላል ማለት ነዉ።

የዕዉቀት ዉቅያኖስ የአሜሪካ ወይም የቻይና ወይም የህንድ ወይም የኢትዮጵያ ወይም የሌላ ሃገር ሳይሆን የሰዉ ልጅ ነዉ።

እኔ በቅርቡ እዚህ ፎረም ላይ የጻፍኩኝ ጥሪ የሰዉ ልጅ የዕዉቀት ዉቅያኖስ ዉስጥ የኢትዮጵያዊያን ሳይንትስቶች ጠብታዎች እንዲበዙ ምርምር የመስራት ችሎታቸዉ የተመሰከላቸዉ ወይም ፒ ኤች ዲ ያገኙ በህይወት ዘመናቸዉ ብያንስ ኣንድ ጠብታ ይጨምሩ የሚል ነዉ።

ይህ እየተጠናከረ ሲሄድ፣ የኢትዮጵያዊያን ኣስተዋጽኦዎች እየጎሉ ሲሄድ፣ ሃገር ጠንካራ ምርምር እያካሄደች ነዉ ይባላል።

በቅርቡ በኣንድ የምርምር ረድፍ ቻይና ለመጀመርያ ግዜ ከኣሜሪካ ቀደመች የሚል ዜና ነበረ።

ይህ ማለት ዕዉቀቱ የቻይና ነዉ ማለት ሳይሆን በቻይና ዩኒቨርዚቲዎች ዉስጥ የሚስሩ ተመራማሪዎች እንግልዝ ሃገር ዉስጥ በሚታተም ኔቸር የተባለ በጣም ታዋቂ የሳይንስ መጽሔት ዉስጥ ያበረከቱት ኣዳዲስ ሀሳቦች በአሜርካ ዩኒቨርዚቲዎች የሚሰሩ ተመራማሪዎች ካበረከቱት በለጠ ማለት ነዉ።

በቅርቡ ለብቻዬ ሳሰላስል እዚህ ፎረም ዉስጥ ኣልፎ ኣልፎ የሚጻፉት ኣዳዲስ ሀሳቦች የአሜሪካዉ ሃርቫርድ ዩኒቨርዚቲ ያልደረሰባቸዉ ዕዉቀት ነዉ ብዬ በዚህ ረገድ የኤልያስ ክፍሌ ዩኒቨርዚቲ ከሃርቫርድ ዩኒቨርዚቲ ይበልጣል ኣልኩኝ። ለራሴ።

የዕዉቀቱ ጥልቀት ምን ያህል ለብዙዎች መገለጡን ባላዉቅም ሃርቫርድ ዩኒቨርዚቲ ስለ መጀመርያዉ ሬይነሳንስ በደንብ የምያዉቅ ቢሆንም ስለ ሁለተኛዉ ሬይነሳንስ የኤልያስ ክፍሌ ዩኒቨርዚቲ ያህል ኣያዉቅም ብዬ መከራከር እችላለሁ። ለምሳሌ ያህል ስለ ኩት፣ ኩረት፣ ከት የተጻፈዉን መጥቀስ ይቻላል።

ይህ ኣዲስ ማስተዋል ከታተመ ቀን ጀምሮ የሰዉ ልጅ የዕዉቀት ዉቅያኖስ ዉስጥ ጠብ ብሏል።

የሰዉ ልጅ የዕዉቀት ዉቅያኖስ ዉስጥ ዕዉቀትን መፈለግ በጣም ፈታኝ ስራ ነዉ። ፒ ኤች ዲን ለማግኘት የሚሰራ ሰዉ ኣንዱ ትልቁ ፈተናዉ የምርምር ችሎታ ዕዉቅና ለማግኘት መጀመርያ ኣዲስ ሀሳብን ያመነጨዉ የተመራማሪዉ ኣዕምሮ መሆኑን ማረጋገጥ ነዉ። ለዚህ ፈተና ሊትሬቸር ሪቪዉን ማለፍ ኣለበት።

ጉግል ሳይፈጠር በፊት ርፈረንስ የተባሉትን የምርምር ኣመልካቾችን ማጥናት ትልቅ ስራ ነበረ።

ጉግል የዕዉቀት ዉቅያኖስን ለመቃኘት የምያስችል ኣዲስ ቴክኖሎጂ ነዉ።

ካልተሳሳትኩ ጉግል ዉስጥ የታተመ ዕዉቀት ሲፈለግ ይህ የአሜሪካ ዕዉቀት ነዉ፣ ይህ የቻይና ነዉ፣ ይህ የኢትዮጵያ ነዉ ብሎ ደርድሮ ኣይመልስም።

ኣዲስ ዕዉቀት የመነጨዉ አሜሪካ ዉስጥ ሆነ ኢትዮጵያ ዉስጥ ከታተመ ቀን ጀምሮ የሰዉ ልጅ ዕዉቀት ነዉ። የታተመ ከሆነ ኣልታወቀም ማለት የታተመዉ ዕዉቀት ዉቅያኖሱ ዉስጥ ዬለም ማለት ኣይዴለም።

ስለዚህ በእኔ አስተሳሰብ መሠረታዊ ጥያቄ መሆን ያለበት የሰዉ ልጅ የዕዉቀት ዉቅያኖስ ዉስጥ ምን ያህል ጠብታዎችን ጨምረናል ነዉ።

ለዚህ ደግሞ ሜዳዉም ይሀዉ፣ ፈረሱም ይሀዉ እንደሚባለዉ ነዉ። በአለም ዙርያ ያሉ ተመራማሪዎች ኣዲስ ዕዉቀትን እንግሊዝ ሃገር የሚታተመዉ ታዋቂ የሳይንስ መጽሔት ዉስጥ ማሳተም ከቻሉ ኢትዮጵያዊያን ተመራማሪዎችም ማሳተም ይችለሉ። ይህ የሳይንስ መጽሔት ኣድሎ ያለዉ ከሆነ ተቀባይነትን ማግኘት የሚችልን የሳይንስ መጽሔት የኢትዮጵያ የሳይንስ ድርጅት መጀመር ይችላል። ይህ ሜዳዉ ነዉ።

ፈረሱ ደግሞ የኢትዮጵያ ዩኒቨርዚቲዎች በሙሉ ሊሆኑ ይችላሉ።

እኔ የማዉቃቸዉ የተከበሩ ኣስተማሪዎች ልጆችዋን በፍቅር እንደምታሳድግ የተከበረች እናት ናቸዉ። የተከበረች እናት ቤት ያፈራዉን ለፍታ ለልጆችዋ ኣቅርባ በበሉልኝ የምትል ናት። የሚጠግቡ ኣይመስላትም። በደንብ ቢበሉላት በደንብ የምያድጉላት መሆኑን ነዉ የምታዉቀዉ።

የተከበረ አስተማሪም የምያስተምራቸዉን ዕድሜ ጠገብ ያልሆኑ ተማሪዎቹን ከዕዉቀት ዉቅያኖስ እየጨለፈ ምነዉ የበለጠ ባወቁልኝ ባይ ነዉ።

እኔ እንደሚገባኝ ከሆነ የትምህርት ምንስቴር ለዚህ ሁሉ ሂደት ፕሮቶኮልን ማስተካከል ነዉ።

ጋዜጠኛዉ ይህቺን መጣጥፍ ኣንብቦ ከአፉ የወጡትን አረፍተ ነገሮች ሁሉ እንደገና ኣዳምጧቸዉ፣ በደንብ ኣጥንቷቸዉ፣ ሌላ ቃል መጠይቅ ማድረግ ይችላል?

እንደ እኔ ዐይነት ኣዳማጮች ያልገባንን እንዲገቡን ለማድረግ ያህል።

Post Reply