ወጣሪና ኮርኳሪ ጥያቄ በተለይ ለትግራይ ሊቃዉንት!
Posted: 01 Jul 2025, 12:03
ክልል ትግራይ ወልቃይትን ጠ(ጸ)ገዴና ጠ(ጸ)ለምት ያካትታል ስትሉ እንሰማለን። የነዚህ ኣካባቢ ሰዎች 90% ትግርኛ ተናጋሪ ናቸውም ስትሉ ይሰማል።
እስቲ ለጨዋታ ያህል ይህ ያላችሁት ትክክል ነው እንበል። በስሌታችሁ መሰረት የተቀረው 10% ኣማርኛ ወይ ኣገውኛ ወይ ቅማንትኛ ተናጋሪ ሳይሆን ኣይቀርም ብለን እንገምታለን።
ትግራይ ክልል ውስጥ 3 ብሄረሰቦች እነሱም ትግሬ ኩናማና ኢሮብ ነው የሚገኙት ስትሉም ትደመጣላችሁ! የሕወሓት ማኒፌስቶ ሳይቀር እንዲያ ነው የሚለው ሲባልም እንሰማለን!
ታዲያ ወልቃይት ጠ(ጸ)ገዴና ጠ(ጸ)ለምት ውስጥ ያሉት ከትግርኛ ውጭ ኣማርኛ ኣገውኛ ወይ ቅማንትኛ የሚናገሩት ሰዎች ከኩናማ ትግሬና ኢሮብ ጋር ክልል ትግራይ ውስጥ ይገኛሉ ለምንድን ነው የማትሉት? ለምንድን ነው ትግራይ ውስጥ 3 ብሄሮች ነው ያሉት የምትሉት? ከ3 በላይ ኣይሆኑም እንዴ? የሆነ የተዘባረቀ ነገርማ ኣለ!
ማብራሪያ እስቲ ከትግራይ ሊቃዉንት ይሰጥበት፡ መቼም ስለ ጐረቤቶቻችን ማወቅና መጠዬቅ ኣይቻልም ኣይባልም፡ ምክንያቱ ዘመኑ “ዘመነ-ጽምዶ” ነው እያላችሁ ስለሆነ፡ ጥያቂያችን ተገቢነት ያለው ይመስለናል። እዉነተኛ ጽምዶ፡ እዉነትን በመሸፋፈን እዉን ኣይሆንም። ገለጥለጥ አድርጋችሁ እስቲ ንገሩን! ያልገባንን እንዲገባንም ኣስረዱን! ለጨዋታ ያህል ነው!