Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Selam/
Senior Member
Posts: 16892
Joined: 04 Aug 2018, 13:15

ዕርጉሙ ጭልፊት ለሚሰድባቸው እናቶች!

Post by Selam/ » 28 Jun 2025, 14:44

ወላጅ እናትን የሚሰድብ የተረገመ ይሁን።

ንፁህ ፍቅር ያላት……ገራገር ልቦና
ዘግና የማትጨርሰው……የደግነት ቁና!
በድህነቷ ውስጥ……ያላትን አካፍላ
ራሷን በድላ……ለልጆቿ ብላ!
ችግር መከራውን……ስቃዩን ተጋትራ
በኩሽና ተቃጥላ……ጥቢኛዋን ጋግራ!
ለልጆቿ ብላ……ራሷን ረስታ
ይቺ የህይወት ጀግና……የእግዚአብሄር ስጦታ!
ጥልቅ የኑሮ ምስጢር……የማንነት ዋልታ
የፍጡራን ብድር……ታላቅ ባለውለታ
ዕድሜ ልኳን ለልጅ……ስትኖር ተንከራታ
ከፊቷ አይጠፋም……የፍቅር ፈገግታ!!







Post Reply