Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
-
DefendTheTruth
- Senior Member
- Posts: 12459
- Joined: 08 Mar 2014, 16:32
Post
by DefendTheTruth » 26 Jun 2025, 14:38
ሴትዬዋ ምንም ለአገር ተመስጦ ነበራቸዉ ለማለት ያስቸግረኛል፣ የአገር መሪ ሆኖ ስያበቁ፣ የአገሪቷ የስልጣን ቁንጮ ላይ ተቀምጦ ለአማፅያኖች ስያስቡ ኖሩ። መጨረሻም ላይ ደግሞ ያ ሁሉ አልበቃ ብሎዋቸዉ "ዝምታ ነዉ ምርጫዬ " የምል ቬዝ የምመስል ንግግር አደረጉ፣ አደርባይነት ያለባቸዉ ይመስለኛል። ለምመሩት አገር ምንም አይነት ፓሽን ያልነበራቸዉ የስም ብቻ ፕሬዝደንት ሆኖ አለፉ። ያሳዝናል!
ክቡር ታዬ አስቀስላሴ በሄዱበት ሁሉ ለአገራቸዉ ተቆርቋሪ ና የወደ ፊት እጣ ፋንታዋ የምያሳስባቸዉ ትልቅ የአገር መሪ ናቸዉ። ለአገራቸዉ ማሰባቸዉን ጥርጥር የለኝም፣ አብይን ይዉደዱት አይዉደዱት የማዉቀዉ ጉዳይ የለኝም፤ ያ ወሳኝም አይደለም። ለአገሪቷ ማሰብ ና መቆርቆር በቂ ነዉ፣ የአገር መሪ ለመባል።
ክቡር አምባሳደር ታዬ የኔን ክብር አግኝቶዋል። ከርቤሏ ፕሬዝደንት ጋር በምንም አይነት አይወዳደሩም።