ኦሮሙማ ማለትን ማንም ሰዉ መጠቀሙን ሳላዉቅ በፊት መጠቀሜን ኣስታዉሳለሁ።
የተጠቀምኩኝ ህወሃትን ለመቃም ያለክፍፍል ይሁን የሚል ሀሳብን ለማስተጋባት ነበር።
የእኔ ህወሃትን መቃወም ቀልድ ኣልነበረም። ወጣት ሆኜ መቃወም ኣልፎ ለመቃወም ተንቀሻቅሼኣለሁ።
ለመቃወሜ ከማስታዉሳቸዉ ዉስጥ ኣንድ ቀን አዲስ አበባ ከምሳ ሰዓት በኋላ ከዛ በፊት ሰምቼ የማላዉቀዉን ሬድዮ ጣብያ ኣንድ ሰዉ ከፈተ። በህወሃት የሚሰራጭ ነበር።
ድርጅቱ ከጎጃም ወደ ወለጋ ተሻግሮ የነበረ ግዜ ነዉ።
የዛን ቀን ነበር ሬድዮ ስርጭቱ ብሔር ኦሮምያ ስል ለመጀመርያ ግዜ የሰማሁኝ።
ገና እንደሰማሁኝ ያሉት ሳይሆን እኛ እናዉቅልሃለን ማለታቸዉ ዉርደት ነዉ ያልኩኝ።
በወጣትነቴ የጀመርኩኝ መቃወም ሃገር ዉስጥም ሆነ ከሃገር ዉጪ ያልተቋረጠ ነበር።
ደጃ ኒዉስ የተባለ መድረክ ላይ የኢትዮጵያዊያን ክርክርን አሜሪካ ትምህርት ቤት ኣዲስ ተማሪ ሆኜ ግዜ ሳገኝ ኣነብ ነበር።
ክርክራቸዉ ስለ ሀሳብ ዉይይት በላይ ስለ ጎሳ ንትርክ መሆኑን ኣስተዉዬ በወጣትነቴ የጀመርኩኝን መቃወም ሆነ መደገፍ ትቼ የማዉቀዉ አካዳሚ ላይ ለማተኮር ወስኜ ነበረ።
በዚህ መሃል ዶክተር አለማየሁ ብሩ የተባለ በአካል የማላዉቀዉ ሰዉ ሰምቼ የማላዉቀዉን ታሪክ የጻፈዉን በአጋጣሚ ኣነበብኩኝ።
የዛን ቀን ነበር በገን ዱኤ አርጌ ብዬ በወጣትነቴ የጀመርኩኝን መቃወም የቀጠልኩኝ።
በዚህ ሂደት ዉስጥ ነበር ያለክፍፍል ለመቃወም ኦሮሙማ ይቅደም ብዬ የነበረዉ።
በዚህ የመቃወም ሂደት ዉስጥ ነበር በኣጋጣሚ ከፕሮፌሰር አሰፋ ጃለታ ጋር ዋሺንግተን ዲ ሲ ዉስጥ ለኣጭር ግዜ የተገናኘነዉ። ስለባለሙያዎች ስብሰባ ምክንያት።
የማስታዉሰዉ አረት ሰዎች ነበርን በአጋጣሚ ለኣጭር ግዜ የተገናኘነዉ።
በዛች ኣጭር ግዜ ዉስጥ ነበር ፕሮፌሰሩ ኢትዮጵያ ያሉትን ግልጽ ባልነበረ አሽሙር ለመዝለፍ የቃጣዉ። ሰምቼዉ ርካሽ አሽሙር ነዉ ብዬ መልስ ኣልሰጠሁትም። ኣብሮን የነበረ የአከባቢዉ ሰዉ ለተናገርካት ይቅርታ በል ብሎ መከረዉ። የአከባቢዉን ሰዉ ምክር ሰምቶ ይቅርታ ኣላለም።
እኔ ታዝቤዉ መልስ ኣያስፈልገዉም ብዬ ተዉኩኝ። ግዜ መልሶለታል ብዬ ኣስባለሁ።
ኣሁንም ስለዛ ገጠመኝ ሳይሆን ስለዚህ ግዜ ዉይይት ነዉ።
ከእኔ የወጣትነት ዕድሜ መንቀሳቀስ የዚህ ዘመን ወጣቶች ልምድ የሚቀስሙ ከሆነ።
ነብሱን ይማር የሲሳይ እብሳን ጽሑፎች በወጣትነቴ ኣጋጥሞኝ ማንበብ ጀመርኩኝ። የመጻፍ ችሎታዉን ባደንቅም ኣንድ ቀጭን ክርክሩን ኣልረሳም። በእንግልዘኛ ፒፕል ማለት እና ፒፕልስ ማለት ልዩነት ኣላቸዉ ብሎ ይከራከር ነበር።
ያኔ እንደዛ ዐይነት ቀጭን ክርክር ቢገርመኝም ሰንብቼ ነዉ አሜሪካ ወደ ጂኦ ስቴሽነሪ ኦርቢት የተባለ ጠረፍ ሳተላይቶችን በምትወነጭፍበት ዘመን ሲሳይ እብሳ ፒፕል እና ፒፕልስ ማለት ልዩነት ኣላቸዉ ማለትን በቁነምቲ በኩል ከዋሺንግተን ዲ ሲ ወደ ኢትዮጵያ ይወነጭፍ ነበር ያልኩኝ።
ኣንድ ቀን ተገናኝተን በጥለቀት በተወያየን እያልኩ እያሰብኩ ነበር ሕይወቱ ሳያልፍ በፊት ኣንድ ቀን ደዉሎልኝ ትንሽ ያወራኝ። ብዙም ሳይቆይ ሕይወቱ ማለፉን ሰምቼ ኣዘንኩኝ።
ለምን እንደደወለልኝ እስከዛሬ ድረስ በዉል ባላዉቅም በመብት ስም ዉይይቱ ቀጥሏል።
ፕሮፌሰር አሰፋ ጃለታ እስከዛሬ ድረስ ያወራል።
እኔ ፕሮፌሰር ኣይዴለሁም። ከስታ ሳይንትስት ነኝ ባይ ነኝ። የሚላስን እምቢ ባልል ኪሳም መሆን እችል ነበር ብዬ ኣስባለሁ። የሚላስን እምቢ ማለት ይቻላል።
ስለዚህ የትኛዉንም ፕሮፌሰር ጨምሮ ጥያቄ ለመጠየቅ የሞራል ብቃት ኣለኝ ብዬ ኣስባለሁ።
ብዙ ሰዎች ፒ ኤች ዲ ማለት ለችሎታ ብቃት ዕዉቅና ማግኘት ሳይሆን ለጉራ የሚሆን ፈቃድ ይመስላቸዋል።
እኔ የማዉቀዉ አሜሪካ ዉስጥ ተመራምሮ ኣዲስ ዕዉቀትን የማመንጨት ችሎታ በአምስት ፕሮፌሰሮች ተገምግሞ ዕዉቅና ይሰጠዋል። ለዚህ ዕዉቅና ምስክርነት የሚሆን ተመራማሪዉ ያመነጨዉ ኣዲስ ዕዉቀት በሌሎች ሶስት ሳይንቲስቶች ተገምግሞ በታወቀ የሳይንስ መጽሔት ወይም ጆርናል ዉስጥ ለሕትመት ተቀባይነት ማግኘት መቻል ኣለበት።
ይህ የመመራመር ችሎታ ዕዉቅና የሚገኘዉ ዕንዴት ነዉ ለማለት ሳይሆን ዕዉቅናዉ ከተገኘ በኋላ መምጣት ያለበት ምንድነዉ ለማለት ነዉ።
በኣጭሩ ኣዲስ ዕዉቀትን እያመነጩ መኖርን ነዉ።
በእኔ አስተሳሳብ ኣዲስ ዕዉቀትን የማመንጨት ዕዉቅናን ወይም ፒ ኤች ዲን ያገኘ ማንኛዉም ኢትዮጵያዊ በህይወቱ ዉስጥ ለዕዉቅናዉ ማጽኛ ወይም ቫሊዴሽን የሚሆን ብያንስ ኣንድ የምርምር ዉጤቱን በታወቀ የሳይንስ መጽሔት ወይም ጆርናል ዉስጥ ማሳተም መቻል ኣለበት።
ካልሆነ የመኪና መንጃ ፈቃድን ኣግኝቶ መኪናን ሳያሽከረክሩ መኖር እንደማለት ነዉ።
ፕሮፌሰር አሰፋ ጃለታ ምን ኣዲስ ዕዉቀቶችን ስያመነጭ እንደኖረ ኣላዉቅም።
እያሳተመ ስለኖረ ብሩታል ፒር ሪቪዉ ወይም ርህራሄ ዬለሽ የእኩያ ወቀሳ ወይም ሂስ ምን እንደሆነ እንደምያዉቅ እርግጠኛ ነኝ። ፕሮፌሰር ስለሆነ።
ኣዲስ ነገር ለማወቅ ባደረኩኝ ጥረት ዉስጥ ነዉ ኦሮሞ የሚለዉ ቃል መሠረቱ ምንድነዉ የሚል ጥያቄ የጠየኩኝ።
ኣንድ ሰዉ ኦርመ ከማለት የመጣ ነዉ የሚል መልስ ሰጥቷል። ይህን መልስ ትክክለኛነቱን ማረጋገጥ ኣልቻልኩም።
ከእኔ ይልቅ እነ ፕሮፌሰር አሰፋ ጃለታ ማወቅ እና ማረጋገጥ ይችላሉ። የሶሻል ሳይንስ ባለሙያዎች ስለሆኑ።
በቅርቡ ቢዛሞ የሚባል ቃልን ሰማሁ። መኖሩን ኣላዉቅም ነበር። ስለዚህም ቃል ፕሮፌሰሩ ከእኔ የበለጠ ያዉቅ ይሆናል።
ስለዚህ ቃል ካወኩኝ በኋላ ነዉ ዶክተር አለማየሁ ብሩ ጽፎት ለእኔ እንቆቅልሽ ሆኖብኝ የሰነበተዉ ሌላ መላምት የሆነልኝ።
ለእንቆቅልሹ ቢዛሞ በየትኛዉ ግዛት ስር እንደነበረች ሌላ ጥያቄን ኣምጥቷል።
ሌሎች ጥያቄዎችን እየጠየኩኝ በፊት የማላዉቀዉ የሚከተለዉ ኣዲስ ዕዉቀት መነጨ።
ኩት (ኦሮምኛ)
ኩረት [ቁረጥ] (ኣማርኛ)
ከት (እንግልዘኛ)
ፕሮፌሰር አሰፋ ጃለታ ይህን ኣዲስ ዕዉቀት ከዚህ በፊት ኣስተዉሎ እንደሆነ ኣላዉቅም። ሆነም ኣልሆነም ይህን ኣንብቦ ኦሮሞ የትኛዉ እንደሆነ መመለስ ይችላል? ኩት የሚለዉ ነዉ? ኩረት የሚለዉ ነዉ? ከት የሚለዉ ነዉ? ወይስ ሁላቸዉም ናቸዉ?
ጉድ ፈላ
ጉዲ ፉላሳ
ጉድ ፉል
ጋG
ፕሮፌሰር አሰፋ ጃለታም ሆነ ፕሮፌሰር ኣስፋዉ በየነ ቢዛሞ ዉስጥ ሀረግ ኖሮኣቸዉ ህፕኖሲስ ዉስጥ የኖሩ ናቸዉ ወይስ የቦረና ተወላጆች ናቸዉ?
በተለይም ፕሮፌሰር አሰፋ ጃለታ የሶሻል ሳይንስ ባለሙያ ስለሆነ ኦሮሞ የሚለዉን ቃል መሠረቱን፣ ኩት፣ ኩረት፣ እና ከት ከሚሉት ኦሮሞዉ የትኞቹ እንደሆኑ፣ ቢዛሞዎች ማን እንደነበሩ ማብራራት የሙያ ሀላፊነት ኣለበት።
ኣንድ ሰዉ እንዳለዉ የኦሮሞ ቃል መሠረቱ ኦርመ ከሆነ ኦሮሙማ ኦርሙማ ወይም ባዕድነት ማለት ይሆናል።
ይህን ከመሠረቱ ኣጥንቶ ማብራራቱ ዛሬ እኔ ወጣት የነበርኩኝ ዕድሜ ላይ ያሉት ኢትዮጵያዊያን በሙሉ የተሻለ ግልጽ የሆነ ዕዉቀት እንዲኖራቸዉ ያደርጋል።
እነዚህ የዛሬ የኢትዮጵያ ወጣቶች የነገዎቹን የኢትዮጵያ ሳይንቲስቶችን የምያፈሩ ናቸዉ።
ፕሮፌሰር አሰፋ ጃለታ እነዚህን ሶስት ጥልቅ ጥያቄዎችን መመለስ ካልቻለ በብሩታል ፒር ሪቪዉ ቋንቋ በቴንሲ ነዋሪ ኢትዮጵያዊ ወይም መሠረቱ ኢትዮጵያ የሆነ ወስላታ አሜሪካዊ ነዉ ማለት ይቻላል።