ስለዚህ ርዕስ ለረጅም ግዜ ሳቀነቅን እና እንዲስተዋል ስጥር ኖርኩኝ።
በዚግ ግዜ የርዕሱ ጭላንጭሎች እዛም እዚህም ቢጠቀሱም ንጥር ያለ አይመስለኝም።
ንጥር ለማለት መስመር የያዘ ቢመስልም።
እኔ እንደገባኝ ከሆነ ኢትዮጵያ በተዘዋዋሪ ለሆሎኮስት በታሪክ ተጠያቂ ሆናለች።
እንዴት ሆኖ ኣላችሁ?
መጠየቅ በጎ ነዉ።
ሆሎኮስት ሁለተኛዉ የዐለም ጦርነት ግዜ የኣርያን ጎሳ ነን ያሉት ከሁሉ እንበልጣለን በማለት በእግዝኣብሔር የተመረጡ የተባሉት ጎሳ ላይ ያደረሱት ዘግናኝ እልቂት ነዉ።
ከሁሉ እንበልጣለንን እና በእግዝኣብሔር የተመረጡ ማለትን ማሰላሰል ከባድ ኣይዴለም።
ከሁሉ እንበልጣለን ያሉት በእግዝኣብሔር የተመረጡ የተባሉት ላይ የተነሱ ዋዜማ ላይ መሠረቱ እስራኤላዊ የሆነ ጀርመን ሃገር ይኖር የነበረ ስግመንድ ፍሪዩድ እ አ አ በ1939 ኣንድ መጽሓፍ ኣሳተመ።
እኔ የገባኝ የመጽሓፉ ዐላማ በእግዝኣብሔር የተመረጡ የተባለዉን የእስራኤል ሕዝብ ያላዉ ሳይሆን ከግብጽ ተሰዶ እስራኤል የሄደ የግብጽ ፈረኦን ነዉ የሚል ነዉ። ስለዚህ ሕዝቤን ባላለዉ ኣትወንጅሉት የሚል ዐይንውት ዉትወታ ነዉ።
መጽሓፉ ኣሳማኝ ሆኖ ነዉ ያነበብኩኝ።
መሠረቱ ግብጻዊ የሆነ አህመድ ኦስማን የተባለ ሰዉ ስግመንድ ፍሪዩድ ከእስራኤል ሕዝብ ላይ ኣንስቶ ወደ ግብጽ የወረወረዉን ወቀሳ ልክ ነዉ ብሎ እሱ ደግሞ ይህ የግብጽ ፈረኦን ከስደት በፊት የጥንቷ ኢትዮጵያ ግዜያዊ ንጉስ የነበረ ነዉ ብሎ ለስደቱ ምክንያት የጥንቷ ኢትዮጵያ ንግስትን ተጠያቂ ኣድርጓል።
ከእስራኤል ወደ ግብጽ የተወረወረዉ ወቀሳ በተራዉ ከግብጽ ወደ ጥንቷ ኢትዮጵያ ተወረወረ።
ሆረስን በአካል ባላዉቀዉም ስለ ኢትዮጵያ ጥንታዊ ታሪክ ኣዉቃለሁ ስለሚል በተረህ ስለዚህ ታሪክ ኣስተዉል እና ለታሪክ ይታረም እያልኩ ስማጸነዉ ሰነበትኩ።
ኣሁን መለኮታዊ ክስተቱ ይህንንም እያረመ ይሁን እላለሁ።
መሠረታዊ ጥያቄዉ ፈጣሪ ሰዉን በራሱ ኣምሳየ ፈጠረ ከተባለ ከፈጠራቸዉ ጎሳዎች ዉስጥ ኣንዱ የተመረጠ ሌሎቹ ያልተመረጡ ማለት ፍትሓዊነት የሌለዉ ስህተት ነዉ።
ይህ ስህተት እንደነበረ ስግመንድ ፍሪዩድ ያስረዳዉ ከሰማንያ ስድስት ዓመታት በፊት ነዉ።
ከታረመ ይህን ሁሉ ዓመታትን ያስቆጠረዉን ማወደስ ታሪካዊ ስህተት ነዉ።