አምቦ ምን ማለት ነው? አምቦነሽ ስለ ግብጽ ስለላ ምን አለች?? ስለ ታዬ ደንድአስ?
Posted: 19 Jun 2025, 21:50
መጀመሪያ አንድ ሊያሳስት የሚችል ቃል እንመልከት ። እሱም አምባ ነው። በአማርኛ አምባ የተራራ ጫፍ ሲሆን በተለይ በተራራ አናት ላይ ያለ ለጥ ያለ መሬት ነው ። የአምቦ መልክአ ምድር በመሰረቱ ተራራማና በተራራ አናት ላይ ያለ መሬት አይደለም። አምቦ የሚለው ስም ከመናገሻ ተራሮችና ከንጦጦ ተራሮች ጋር ካልተያያዘ በተቀር። እንዲያም የመናገሻ ተራሮች ዳሞቴ (ተራራማ ቦታ ማለት ነው) ይባሉ ስለነበር አምቦ የሚለው ስያሜ በእንጦጦ ፣ መናገሻና በሜታ ተራሮች አካባቢ የለም ።
ሁለተኛውና ትክክለኛ ነው ብዬ የማምነው አምቦ የሚለው የክስታኔኛና ጋፋትኛ ቃል ነው ። አምቦ የሚለው ቃል በቀጥታና እንደ ወረደ መቅኔ ማለት ነው። ዛሬ ባለው ትርጉሙ አጽም ውስጥ ያለው ቦን ማሮው የሚባለው ቢሆንም ሌላው ትርጉሙ አቅም ፣ ጉልበት ፣ ጥንካሬ ማለት ነው ። ለምሳሌ አቅም የሚለው ቃልና አጽም አንድ ቃል ናቸው ። ስለዚህ በጥንት ዘመን አጽም፣ አቅም ፣ ጉልበትና ጥንካሬ የሚል ትርጉምና አግባብ የነበራቸው ይመስላል ። ስለሆነም አምቦ መቅኔ ወይም አቅም የሚለውን ትርጉም ከተከተልን ኣምቦ ጠንካራ የሚል ትርጉም ይሰጠናል።
መጀመሪያ ላይ ከተመለከትነው አምባ (የተራራ አናት) የሚለው ቃል ደሞ አምባ ጓሮ ጠበኝነት ወይም ጦረኝነት የሚል ትርጉም ሊሰጠን ይችላል ። የዛሬው አምቦ የጋፋቶች አገር ሆኖ ስሙ 'እንደ ገብጣን' ይባል ነበር ። ይህ ምድረ ገብጣን ወይም የገብጣኖች አገር ማለት ነው። ገብጣን የሚለው የጋፋት ቃል ትክክለኛ አጠቃቀሙ ምን እንደ ነበር ባይታወቅም 'ጠነ' የሚለው ቃል በጋፋትም በክስታኔን ጉልበት ፣ ኃይል ፣ ጥንካሬ ማለት ነው ። ለምሳሌ በጎንደር ግዛት ዘመን የኢትዮጵያ ጦር አዛዥ የነበሩት ጉራጌው ራስ ዘስላሴ የጉራጌ ጠቅላይ ግዛትን አጉራ ጠነ ይሉት ነበር ። አጉራ ጠነ ራስ ገዝ አገር ማለት ነው። አሁን ባለው የዘመኑ ክስታኔኛ ሰነ አቅም ማለት ነው ። ሰነ ና ጠነ አንድ ቃል ናቸው። ዛሬ ላይ ስልጣን ከሚለው ቃል ከዚያ የተያያዘ ነው።
ስለዚህ በእኔ ኤጅኬትድ ግምትን ባሉት የቋንቋ መረጃዎች በመታገዝ አምቦ ጠንካራ (ሕዝብ) ማለት ነው ብዬ አምናለሁ።
አምቦ አመጸኛነቱ ብቻ ሳይሆን ኢትዮጵያዊነቱም እንከን የለውም! እናም ይቺን አምቦነሽ ስሟት!!