Horus wrote: ↑19 Jun 2025, 21:50
መጀመሪያ አንድ ሊያሳስት የሚችል ቃል እንመልከት ። እሱም አምባ ነው። በአማርኛ አምባ የተራራ ጫፍ ሲሆን በተለይ በተራራ አናት ላይ ያለ ለጥ ያለ መሬት ነው ። የአምቦ መልክአ ምድር በመሰረቱ ተራራማና በተራራ አናት ላይ ያለ መሬት አይደለም። አምቦ የሚለው ስም ከመናገሻ ተራሮችና ከንጦጦ ተራሮች ጋር ካልተያያዘ በተቀር። እንዲያም የመናገሻ ተራሮች ዳሞቴ (ተራራማ ቦታ ማለት ነው) ይባሉ ስለነበር አምቦ የሚለው ስያሜ በእንጦጦ ፣ መናገሻና በሜታ ተራሮች አካባቢ የለም ።
ሁለተኛውና ትክክለኛ ነው ብዬ የማምነው አምቦ የሚለው የክስታኔኛና ጋፋትኛ ቃል ነው ። አምቦ የሚለው ቃል በቀጥታና እንደ ወረደ መቅኔ ማለት ነው። ዛሬ ባለው ትርጉሙ አጽም ውስጥ ያለው ቦን ማሮው የሚባለው ቢሆንም ሌላው ትርጉሙ አቅም ፣ ጉልበት ፣ ጥንካሬ ማለት ነው ። ለምሳሌ አቅም የሚለው ቃልና አጽም አንድ ቃል ናቸው ። ስለዚህ በጥንት ዘመን አጽም፣ አቅም ፣ ጉልበትና ጥንካሬ የሚል ትርጉምና አግባብ የነበራቸው ይመስላል ። ስለሆነም አምቦ መቅኔ ወይም አቅም የሚለውን ትርጉም ከተከተልን ኣምቦ ጠንካራ የሚል ትርጉም ይሰጠናል።
መጀመሪያ ላይ ከተመለከትነው አምባ (የተራራ አናት) የሚለው ቃል ደሞ አምባ ጓሮ ጠበኝነት ወይም ጦረኝነት የሚል ትርጉም ሊሰጠን ይችላል ። የዛሬው አምቦ የጋፋቶች አገር ሆኖ ስሙ 'እንደ ገብጣን' ይባል ነበር ። ይህ ምድረ ገብጣን ወይም የገብጣኖች አገር ማለት ነው። ገብጣን የሚለው የጋፋት ቃል ትክክለኛ አጠቃቀሙ ምን እንደ ነበር ባይታወቅም 'ጠነ' የሚለው ቃል በጋፋትም በክስታኔን ጉልበት ፣ ኃይል ፣ ጥንካሬ ማለት ነው ። ለምሳሌ በጎንደር ግዛት ዘመን የኢትዮጵያ ጦር አዛዥ የነበሩት ጉራጌው ራስ ዘስላሴ የጉራጌ ጠቅላይ ግዛትን አጉራ ጠነ ይሉት ነበር ። አጉራ ጠነ ራስ ገዝ አገር ማለት ነው። አሁን ባለው የዘመኑ ክስታኔኛ ሰነ አቅም ማለት ነው ። ሰነ ና ጠነ አንድ ቃል ናቸው። ዛሬ ላይ ስልጣን ከሚለው ቃል ከዚያ የተያያዘ ነው።
ስለዚህ በእኔ ኤጅኬትድ ግምትን ባሉት የቋንቋ መረጃዎች በመታገዝ አምቦ ጠንካራ (ሕዝብ) ማለት ነው ብዬ አምናለሁ።
አምቦ አመጸኛነቱ ብቻ ሳይሆን ኢትዮጵያዊነቱም እንከን የለውም! እናም ይቺን አምቦነሽ ስሟት!!
ኣሁን ደግሞ አጽም እና አቅም እያልክ መዝናናት ጀመርክ?
አምቦን የአዲስ አበባ ኮሪደር ልማት ጅረ እያለ ነዉ ወይስ ተዋቅሮ ፌደራል መንግስት ዉስጥ ቢገባ የፌደራል መንግስቱን ዐቅም ያጠናክራል እያለ ነዉ ኣስብለሀኝ ነበር። አመጸኛዉ ያልከዉን ሳላነብ በፊት።
አምቦን አመጸኛ ስትል ስለ የትኛዉ አመጹ ነዉ?
የሙሶሊኒ ወራሪ ላይ አመጸኞች የሆኑትን ጀግኖቹ እነ ጃገማ ኬሎ፣ ገረሱ ዹኪ፣ ወዘተ እንዳልል በሰፈራችሁ ባንዳ ኣልነበረም ስትል ሰነበትክ።
እ አ አ ስለ 1991 ሎንደን ኮንፍረንስ ነዉ እንዳልል ኢትዮጵያን ወክሎ የሶስት አማጺ ድርጅቶች መሪዎችን ለማደራደር ሎንደን የሄደዉ የወቅቱ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ምንስትር የነበረዉ ተስፋዬ ድንቃ የአምቦ ሰዉ ነዉ።
ትግራይን ከኢትዮጵያ ነፃ ለማዉጣት የተደራጁት የሕወሃት ኣማጺያን አድስ አበባ ለመግባት በወለጋ በኩል የመጡ ግዜ ይህማ ወረራ ነዉ ብሎ ያመጸዉን የአምቦ ሕዝብ ነዉ እንዳልል ከሕወሃት ጋር ተሰልፈህ አምቦ የደረስክ ኣይመስለኝም።
የተመራመርኩ ምሁር ነኝ ማለትህን ፈትሸዉ ብዬ ብመክርህ ኣልሰማም ብለሃል። እዚህ ፎረም ላይ መሳተፍ ከጀመርኩኝ ግዜ ጀምሮ ነዉ ስታገስህ እና ስታዘብህ የኖርኩኝ። ቆጥሬህ ኣልሰማም ብለህ።
You recently posted that you love Ethiopia as a nation. If it is real instead of political opportunism, you should go back to school in earnest in order to answer the following two questions for the ages.
The day you correctly answer these two questions, you may become someone among Renaissance men. Currently, not only are you no one among Renaissance men, you are also an ignorant abuser of their labor.
የዘመናት ልፋታቸዉ በኣንተ ዘመን ብቻ ጉም ሆኖ የሚበን ይመስለሃል።
መመለስ ያለባቸዉ ሁለቱ ጥያቄዎች፥
1. ሞኖቴይዝም ግብጥ ዉስጥ፣ ኣፍርካ ዉስጥ የተጀመረ መሆኑ ከታወቀ ወዲህ ለምንድነዉ ጁድዮ፣ ክርስትያን፣ እስላም እስታብልሽመንት ተብሎ የታወቀዉ ኢጂይፕቶ፣ ጁድዮ፣ ክርስትያን፣ እስላም እስታብልሽመንት ተብሎ ያልታረመዉ?
2. ለምንድነዉ ከኣፍርካ ዉስጥ ስደት ኣፍርካ ዉስጥ የሚወደሰዉ?
ላለፉት ሁለት ሺህ ዓመታት ገደማ ዐለም በዚህ ጥያቄዎች ዙርያ ስትሽከረከር ነዉ የኖረችዉ።
ኣዎ፣ ከእኔ በፊት እነዚህን ሁለት ጥያቄዎችን የመለሰ ቀርቶ የጠየቀ ኣልሰማሁም። ከኢትዮጵያ ሆነ፣ ከኤርትራ ወይም ከሶማልያ። ምናልባት ተጠግቶ የነበረ ኣንድ ሰዉ ኑዛዜዉን ለዘላለም ጽፎ ኣልፏል።
ስለዚህ የእኔ የዕዉቀት ልማት ጥረት ኣንተ ከምትለጥፈዉ የኮሪደር ልማት ሪፖርቶች ሁለት ሺህ ግዜ ይበልጣል።
እነዚህን ሁለት ጥያቄዎቼን ኣንብበህም ኣልሰማም ካልክም ግድ ዬለም፣ የዛሬ ዐመት ይሁን መቶ ዐመት ሌላ ሰዉ ተወልዶ መጠየቁ ኣይቀርም። ከእሱ በፊት የተወለዱት የለፉትን ያህል ሳይለፋ።
የበትለር ገተቶዎች ሁለተኛ ቢወለዱ ይደርሱበት ይሆናል።
ለነገሩ ጣልያን ኣልወጣልኝም ቢል ወይም በቁጥር እንያችሁ የሚሉ ብቅ ቢሉ ማሳየትማ ባህላችን ነዉ የሚሉ ኣይጥፉ ማለት ይቻል ነበር።