ለ3 ቀናት የሚዘልቅ የተፈናቃዮች ሰላማዊ ሰልፍ በመቀሌ ሮማናት አደባባይ (እንዲሁም በመጪው ዓርብ ደግሞ በስዊዘርላንድ ጄኔቫ) - ዶቸ ቬለ
Posted: 18 Jun 2025, 16:15
መንግሥት ድህንነታቸው በተጠበቀ መልኩ ወደቀዬአቸው የማይመልሳቸው ከሆነ የራሳቸው እርምጃ እንደሚወስዱ በትግራይ የሚገኙተፈናቃዮችገለፁ። በትግራይ የሚገኙ ተፈናቃዮች በመንግስት ላይ ተቃውሟቸው የሚገልፁበት ትእይንት ዛሬ በመቐለ ማድረግ የጀመሩ ሲሆን በመጪው ዓርብ የዚሁ አካል የተባለ ሰልፍ በጄኔቫ እንደሚደረግ አስተባባሪው ፅላል ሲቪክ ማሕበረሰብ ትግራይ አስታውቋል። ተፈናቀዮቹ ከሚመለከታቸው አካላት አስቸኳይ ምላሽ እንደሚጠብቁ ገልፀዋል።
ዛሬ ጀምሮ ለተከታታይ ሶስት ቀንና ለሊት የሚቆይ ተቃውሞ በመቐለ ሮማናት አደባባይ ማድረግ የጀመሩት እነዚህ የጦርነቱ ተፈናቃዮች፥ ለአምስተኛ ክረምት በመጠልያ መቅየት እንደማይሹ፥ የኢትዮጵያ መንግስት እና የክልሉ ግዚያዊ አስተዳደር ለጉዳያቸው የመጨረሻ ምላሽ የማይሰጡ ከሆነ የራሳቸው እርምጃ እንደሚወስዱ ገልፀዋል።
በእነዚህ ተፈናቃዮች ጉዳይ የሚሰራ እናበተፈናቃዮቹ የተመሰረተው እንዲሁም የዛሬ የመቐለ እንዲሁም በመጪው ዓርብ ደግሞ በስዊዘርላንድ ጄኔቫ የሚደረጉ ሰልፎች ያስተባበረው ፅላል ሲቪክ ማሕበረሰብ ትግራይ የተሰኘ ሲቪክ ማሕበር፥ ትላንት መቀመጫቸው አዲስአበባ ላደረጉ የተለያዩ ሀገራት ኤምባሲዎች እንዲሁም በተለያየ የዓለም ክፍል ለሚገኙ ተላልቅ የሚመለከታቸው የተባሉ ተቋማት በትግራይ ተፈናቃዮች ጉዳይ በኢትዮጵያ መንግስት ላይ ጫና እንዲያኖሩ ደብዳቤ አሰራጭቷል።
የፅላል ሲቪክ ማሕበረሰብ ትግራይ ምክትል ዳይሬክተር ሙዑዝ በርሃ ከነዚህ ለተለያዩ መንግስታት እና ዓለምአቀፍ ተቋማት የተደረጉ ጥሪዎች አወንታዊ ምላሽ እንደሚጠበቅ ለዶቼቬለ ገልፀዋል።
ተፈናቃዩ የመጨረሻ ምላሽ እንደሚሻ፥ ቁርጥ ያለ ነገር የማያገኝ ከሆነ ግን የሚወሰዱ እርምጃዎች ተከትሎ ለሚፈጠረው ችግር ተጠያቂ መንግስት ነው ሲሉ ምክትል ዳይሬክተሩ ጨምረው ገልፀዋል።
ተመሳሳይ የተቃውሞ ሰልፍ ዓርብ በጄኔቫ እንደሚካሄድም ከአዘጋጆቹ ተረድተናል። በመቐለ የተጨመረው ሰልፍ እስከ ዓርብ ይዘልቃል ተብሏል።
ሚሊዮን ኃይለ ሥላሴ
ኂሩት መለሰ
https://www.dw.com/am/%E1%88%88%E1%88%A ... a-72964513?