Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Naga Tuma
Member+
Posts: 6143
Joined: 24 Apr 2007, 00:27

ሬይነሳንስ ማለት ምን ማለት ነዉ?

Post by Naga Tuma » 18 Jun 2025, 15:47

ይህን ቃል ብዙ ሰዎች፣ ብዙ ድርጅቶች፣ የቃሉ መሠረት እና ታሪክ የገባቸዉም፣ ያልገባቸዉም ይጠቀማሉ።

ቃሉ በሰፊዉ የታወቀዉ በፈረንሳይኛ ሲሆን ወደ እንግሊዘኛ ሲተረጎም ሪበርዝ ወይም የዳግም መወለድ ምሳሌ ሆኖ ይታወቃል።

በጣም ሰፊ ታሪክ እና ታሪካዊ ክስተቶች ኣሉት። አዉሮፓን እጅግ ያሳደገ ክስተት ነዉ።

የዳግም መወለድ ምሳሌ ያደረጉት የወደቀዉን የጥንት ግሪክ ስልጣኔን ኣጥንቶ መልሶ ማንሳት ማለት ነዉ።

ይህ ክስተት በቀላሉ የሚመጣ ኣለመሆኑን በደንብ ኣዉቃለሁ። በቅጽበት ሳይሆን በሂደት የሚስተዋል መሆኑን ኣዉቃለሁ።

በኣጭሩ ሂደቱን የምያመጣዉ ሀይማኖት ቤት ሳይሆን ወጣ ብሎ ባህልን መቃኘት ነዉ። ሎሬት ጸጋዬ ቦረና ሄዶ ባህልን ቃኝቶ ለካ ኣንተ ነህ እንዳለዉ ማለት ነዉ።

የእኔ ወጣ ብሎ ባህልን የመቃኘት ሂደት የጀመረዉ ኢትዮጵያ የመጨረሻ ዐመት የኮሌጅ ተማሪ ሆኜ ነዉ።

ኢትዮጵያ ዉስጥ የለዉጥ ግዜ ስለነበረ ያየሁኝን እና የሰማሁኝን ታዝቤ ነዉ ወጣ ብሎ ባህልን መቃኘቱን የጀመርኩኝ።

ከኢትዮጵያ ሳልወጣ ስራ ቦታ የተዋወኩት ሰዉ ኣንድ ቀን የፕሮቴስታንት ሀይማኖት ቤት እንሂድ ብሎ ጋበዘኝ። ግብዣዉ በቅጽበት ኣሳዝኖኝ ሀይማኖት ከሆነ ለምን ተዋህዶ ቤት ኣትሄድም ብዬ ጠየኩት።

ደፍሮ የጠየቀኝ እሺ ባለማለቴ ተከፍቶብኝ ተመለሰ። እነ ፕሮፌሰር እከሌ እየመጡ ኣንተ ለምንድነዉ እምቢ የምትለዉ ብሎኝ።

እኔ በወቅቱ ባህል የመቃኘት ሂደት ዉስጥ ነበርኩኝ።

አሜሪካ ደርሼ ብዙም ሳልቆይ ኣንድ ቀን የናሽናል ጂኦግራፊክን ዶክመንታሪ ፒ ቢ ኤስ ላይ ሳይ ትዬ የሚልን ስም በኣጋጣሚ ኣየሁኝ። ዶክመንታሪዉ ስለ ጥንት ግብጥ ነበር።

በቃሉ ተገረምኩ እና ስለ አከባቢያችን ጥንት ታሪክ የበለጠ መቃኘቱን ቀጠልኩኝ። ትርፍ ግዜን ሳገኝ።

ይህ ባህልን መቃኘት ነዉ አዉሮፓ ዉስጥ የጨለማ ዘመን የተባለዉ ስለምን እንደነበረ ያነበብኩኝ።

እኔ እንደገባኝ ከሆነ ከሞላ ጎደል ከጥንት ግሪክ ስልጣኔ መዉደቅ ጀምሮ እናጥና እና እንመልሰዉ እስከተባለበት የባከነ ግዜ ነዉ።

እንመልሰዉ ብለዉ ከተለፋ በኋላ ብዙ ነገሮች ተከስተዉ፣ ብዙ ኣዲስ ነገሮች ተገኝተዉ እና ተፈጥረዉ፣ የጥንቱ የግሪክ ስልጣኔ እንደገና ተወለደ ተባለ። ሬይነሳንስ ሆነ ተባለ።

ባህልን መቃኘት ሀይማኖትን ከማስተማር ጋር የሚጋጭ የመሰላቸዉ የሀይማኖት መሪዎች ሳይንቲስቶችን፣ የሬይነሳንስ ሰዎችን ተጋፍተዋል።

ይህ መጋፋት ነዉ ለ ሴፓሬሽን ኦፍ ቸርች ኤንደ ስቴት ጽንሰ ሀሳብ መሠረት የሆነዉ።

የሚገርመዉ ባህልን መቃኘት ራሱ ኣዙሮ ስለ መለኮታዊ ጥልቀት የምያስተምር መሆኑ ነዉ። ባህልን ከመቃኘት የወጣዉ ሳይንስ ለሃይማኖት ማስተማርያ ድምጽ ማጉያ መሳርያ፣ ለዝማሬ መሳርያዎችን የሚፈጥር መሆኑ ነዉ።

ሎሬት ጸጋዬ ቦረና ሄዶ ባህልን ሲቃኝ ለካ ኣንተ ነህ ብቻ ብሎ ኣላቆመም። ቃሉ የማይቀለበስ ቃሉ ማለትንም ጨምሮበታል።

የማይቀለበስ ቃሉ ያለዉ ስለ ማን እንደሆነ መጠየቅ እንጂ ማወቅ ኣልቻልኩም።

ስለ ትዬ ታሪክ ሳነብ የፈረኦ አክናተን እናት እንደነበረች ተጽፎ ኣነበብኩኝ። እናቱ የነበረች ብቻ ሳይሆን ከእሷ ጋር በቅርበት ስለኣደገ ስለ ሞኖቴይዝም ሀሳብ ከእሷ ነዉ የተማረዉ የሚል ተጽፎ ኣነበብኩኝ።

ስለ ሙሴ እና ሞኖቴይዝም ወይም ኣንድ ኣምላክ ካነበብኩኝ በኋላ ከስደት በኋላ ስሙን ቀይሮ ሙሴ የተባለዉ ከስደት በፊት ፈረኦ አክናተን ተብሎ ይታወቅ እንደነበረ ተጽፎ ኣነበብኩኝ።

ፈረኦ አክናተን ማለት በሰዉ ታሪክ ዉስጥ ለመጀመርያ ግዜ ሞኖቴይዝምን ማስተማር የጀመረ ነዉ ተብሎ ይታወቃል።

ኣሁን ይህን ሀሳብ ለኣንባቢዎች የምጽፈዉ እስከዛሬ ድረስ ያልተጠየቀ ጥያቄ ይስተዋል ለማለት ነዉ።

ጥያቄዉ ሞኖቴይዝም ወይም ኣንድ ኣምላክን በሰዉ ታሪክ ለመጀመርያ ግዜ የጀመረዉ ኣፍሪካዊ ፈረኦ አክናተን መሆኑ ከታወቀ በተለምዶ ጁድዮ፣ ክርስትያን፣ እስላም እስታብልሽመንት በመባል የሚታወቀዉ ለምንድነዉ ኢጅይፕቶ፣ ጁድዮ፣ ክርስትያን፣ እስላም እስታብልሽመንት ተብሎ ያልታረመዉ?

ይህን ጥያቄ በጥልቁ ማስተዋል ሁለተኛዉ ሬይነሳንስ ስለምን እንደሆነ ማወቅ ነዉ።

ይህ ጥያቄ ከዚህ በፊት ተጠይቆ መሆኑን ባዉቅ ወይም ብሰማ ይስተዋል ብዬ ኣልለፋም። እንዲስተዋል መላልሼ በመጻፍ ኣላሰለችም።