Page 1 of 1
eden: እስቲ ይቺን ቀጭን ቅኔ ፍታት?
Posted: 16 Jun 2025, 21:53
by Horus
Re: eden: እስቲ ይቺን ቀጭን ቅኔ ፍታት?
Posted: 17 Jun 2025, 04:52
by Odie
ቂል!
ኤደን ኢንጂሩ!
ሁሉም ተወሽ

Re: eden: እስቲ ይቺን ቀጭን ቅኔ ፍታት?
Posted: 17 Jun 2025, 07:38
by sarcasm
In Tigrigna, when a couple get married, we say ተጻሚዶም meaning "yoked together". It refers to a partnership where both individuals share similar values, beliefs, and goals. The analogy of two oxen yoked together to pull a plow is often used to illustrate the importance of unity and shared purpose in marriage. When oxen are yoked, they are connected and work together to pull a load, just as a couple in marriage should be united in their goals and efforts. It signifies a harmonious union where partners are united in purpose and work together effectively.
The Greek word translated by most English Bibles as “joined” means so much more than simply uniting and bringing two individuals together.
Literally translated, the original Greek word means to yoke two individuals together. When a couple comes to be married in the church, we don’t simply join them but yoke them together. "So that they are no more two, but one flesh. What therefore God has
joined together, don''t let man tear apart." Matthew 19:6
ጥንድ ጥንድ ሆነው ባይ
ቀናሁ በሰዎች ላይ

Re: eden: እስቲ ይቺን ቀጭን ቅኔ ፍታት?
Posted: 17 Jun 2025, 10:48
by Horus
Re: eden: እስቲ ይቺን ቀጭን ቅኔ ፍታት?
Posted: 17 Jun 2025, 14:33
by sarcasm
አሁን ደግሞ እኔ ነኝ ባል ብለው ለ25 ዓመት እንዲጣሉ ፈልገህ ነው?

እኔ በየዓመቱ በተራ ነው ባል የምት ሆኑት ነው የምለው።
ነገር አታምጪ
Re: eden: እስቲ ይቺን ቀጭን ቅኔ ፍታት?
Posted: 17 Jun 2025, 14:56
by Horus
Re: eden: እስቲ ይቺን ቀጭን ቅኔ ፍታት?
Posted: 17 Jun 2025, 15:12
by Naga Tuma
sarcasm wrote: ↑17 Jun 2025, 07:38
The Greek word translated by most English Bibles as “joined” means so much more than simply uniting and bringing two individuals together.
Literally translated, the original Greek word means to yoke two individuals together.
"So that they are no more two, but one flesh. What therefore God has
joined together, don''t let man tear apart." Matthew 19:6
መምከር ሰለቸኝ። ሁለታችሁንም።
ሆረስ የጀመረዉን ርዕስ ኣንብቤ ይህን ቃል እና ትርጉሙን ትልቅ ኣድርጎ ጡስ ጡስ ይላል ኣልኩኝ። ጡስ ጡስ የሚለዉ እንጨት ጣጤሳ ይባላል።
በኣጭሩ ኣማኝ ነኝ ባይ ኣህዛብ ብዬ ልመልስለት ኣስቤ ነበር። አባይን ያላየ ምንጭ ያደንቃል ኣሉ ብዬ ኣሰብኩኝ። ለበጎ የሆነዉ መለኮታዊ ጽምዶ ያልተገለጠለት ስንቱን ጡስ ጡስ ይላል ብዬ ኣሰብኩኝ።
ኣንተ ብቅ ኣልክ እና ያሰብኩትን ኣጎላሀዉ። በጠቀስከዉ።
የግሪክ የሚባለዉ በብዛት ከጥንት ግብጥ የተዋሱት ነዉ።
ይህ ኣንዱ ሊሆን ይችላል።
ዳ ቭንቺ ኮድን ሳነብ በቅጽበት ግልጥ ያለልኝንን ነዉ እዝህ ያመጣሀዉ።
ጥንት ግብጥ ዉስጥ ሴክሬድ ዩንየን የሚባለዉን ጽንሰ ሀሳብ ወይም ኮንሰፕት ነዉ የጠቀስከዉ። ኣይዴለም?
የጠቀስከዉን ኣንብብ እና ስለ የአባት ኣምላክ ወይም አያነ አባ እና ደያብሎስ ኣጥና።
ኣንተ ያለህ ድክመት ከማህበረስብህ ባህል ድርፍት ማድረግህ ነዉ። እንደ በትለር የጎዳህ ያለ ኣይመስለኝም። የሚማር ነዉ?
ሆረስ ያለዉ ድክመት የፖለትካ ባህል በእሱ ዘመን የተጀመረ ወይም እሱ የጀመረዉ ይመስለዋል። የፕሮፌሰር ታደሰ ታምራት ዐይነት ሁሉን ኣዉቃለሁ ባይ ነዉ። ከሕዝባችን ረጅም ባህል ታሪክ ወዲህ ወድያ ዉልግድ ዉልግድ እያሉ።
Re: eden: እስቲ ይቺን ቀጭን ቅኔ ፍታት?
Posted: 17 Jun 2025, 17:49
by sarcasm
በዚህ ባልና ሚስት ርዕስ ወራጅ ብያለሁ

፥) ከዚህ በላይ ላበላሸው አልፈልግም።
የአብነት አጎናፍር ወንድም መሆኑ አላቅም ነበር። ያቺ ዘፈኑ ብቻ ነው የማውቀው። ሁለት የአብነት አልበሞች በመኪናየ fixture ሆነው ነበር።
Naga Tuma wrote: ↑17 Jun 2025, 15:12
ለበጎ የሆነዉ መለኮታዊ ጽምዶ
እቺን ነገር ወድጃታለሁኝ
ስለ አያነ አባ በፊት የጻፍከውን አንብቤ ነበር። እስካሁን ብዙ የማውቀው የለም።
Re: eden: እስቲ ይቺን ቀጭን ቅኔ ፍታት?
Posted: 17 Jun 2025, 21:33
by Horus
አቶ ሳርካስም፣
ወራጅ አለ ማለትህ መልካም! ጸመድ ጥማድ ሆኖ ማሰሩ ብቻ ሳሆን ገመድ ሆኖም ያስራል ይጠመጠማል! ደሞም በጋብቻ ማጻመዱ ብቻ ሳሆን ዘመድ ሆኖም ይስባል። እስቲ ይቺን አጭር ትብታብ ደሞ እግረ መንገድክን ፍታት!!
Re: eden: እስቲ ይቺን ቀጭን ቅኔ ፍታት?
Posted: 18 Jun 2025, 05:00
by Meleket
sarcasm wrote: ↑17 Jun 2025, 07:38
In Tigrigna, when a couple get married, we say ተጻሚዶም meaning "yoked together". It refers to a partnership where both individuals share similar values, beliefs, and goals. The analogy of two oxen yoked together to pull a plow is often used to illustrate the importance of unity and shared purpose in marriage. When oxen are yoked, they are connected and work together to pull a load, just as a couple in marriage should be united in their goals and efforts. It signifies a harmonious union where partners are united in purpose and work together effectively.
The Greek word translated by most English Bibles as “joined” means so much more than simply uniting and bringing two individuals together.
Literally translated, the original Greek word means to yoke two individuals together. .. .. ..
ጥንድ ጥንድ ሆነው ባይ
ቀናሁ በሰዎች ላይ
'መደመርም' በለው 'መጣመድ'፡
“ፊዚካል ዲማርኼሽን” ሳያስተናግድ፡
በግድም ሆነ በውድ፡
መሬቱ ላይ ሲወርድ፡
ሁለቱ ናቸው አንድ!
viewtopic.php?f=2&t=308857&
Re: eden: እስቲ ይቺን ቀጭን ቅኔ ፍታት?
Posted: 18 Jun 2025, 05:35
by Naga Tuma
sarcasm wrote: ↑17 Jun 2025, 17:49
Naga Tuma wrote: ↑17 Jun 2025, 15:12
ለበጎ የሆነዉ መለኮታዊ ጽምዶ
እቺን ነገር ወድጃታለሁኝ
ወደድኩት ካልክ እኔ ሌላ ምን ልበል?
ከመለኮታዊ ጽምዶዎች ዉስጥ ኣንዱ መለኮት መላኩን እና ደያብሎስን ቢጸምድ ምን ለማስተማር ይሆን?
Re: eden: እስቲ ይቺን ቀጭን ቅኔ ፍታት?
Posted: 18 Jun 2025, 18:19
by sarcasm
Naga Tuma wrote: ↑18 Jun 2025, 05:35
ከመለኮታዊ ጽምዶዎች ዉስጥ ኣንዱ መለኮት መላኩን እና ደያብሎስን ቢጸምድ ምን ለማስተማር ይሆን?
Horus wrote: ↑17 Jun 2025, 21:33
አቶ ሳርካስም፣
ወራጅ አለ ማለትህ መልካም! ጸመድ ጥማድ ሆኖ ማሰሩ ብቻ ሳሆን ገመድ ሆኖም ያስራል ይጠመጠማል! ደሞም በጋብቻ ማጻመዱ ብቻ ሳሆን ዘመድ ሆኖም ይስባል። እስቲ ይቺን አጭር ትብታብ ደሞ እግረ መንገድክን ፍታት!!
ሁለቱንም በጣም ከባድ ናቸው። አብዛናው ግዜ፤ ዓርብ አከባቢ ነበር brain dead የምሆነው፤ አሁን ግን ገና ሮብ እያለ ጭንቅላቴ ማሰብ ተሳነው

ሙቀቱ ነው መሰለኝ

Re: eden: እስቲ ይቺን ቀጭን ቅኔ ፍታት?
Posted: 18 Jun 2025, 18:29
by Selam/
ፕ/ሮ ታደሰ ታምራት “አፈ ታሪክ” ነው ያሉ ጊዜ ነው ዘጭ ያሉብኝ።
Naga Tuma wrote: ↑17 Jun 2025, 15:12
[quote=sarcasm post_id=1564190 time=1750160287 ። የፕሮፌሰር ታደሰ ታምራት ዐይነት ሁሉን ኣዉቃለሁ ባይ ነዉ። ከሕዝባችን ረጅም ባህል ታሪክ ወዲህ ወድያ ዉልግድ ዉልግድ እያሉ።
Re: eden: እስቲ ይቺን ቀጭን ቅኔ ፍታት?
Posted: 18 Jun 2025, 20:24
by Horus
sarcasm wrote: ↑18 Jun 2025, 18:19
Naga Tuma wrote: ↑18 Jun 2025, 05:35
ከመለኮታዊ ጽምዶዎች ዉስጥ ኣንዱ መለኮት መላኩን እና ደያብሎስን ቢጸምድ ምን ለማስተማር ይሆን?
Horus wrote: ↑17 Jun 2025, 21:33
አቶ ሳርካስም፣
ወራጅ አለ ማለትህ መልካም! ጸመድ ጥማድ ሆኖ ማሰሩ ብቻ ሳሆን ገመድ ሆኖም ያስራል ይጠመጠማል! ደሞም በጋብቻ ማጻመዱ ብቻ ሳሆን ዘመድ ሆኖም ይስባል። እስቲ ይቺን አጭር ትብታብ ደሞ እግረ መንገድክን ፍታት!!
ሁለቱንም በጣም ከባድ ናቸው። አብዛናው ግዜ፤ ዓርብ አከባቢ ነበር brain dead የምሆነው፤ አሁን ግን ገና ሮብ እያለ ጭንቅላቴ ማሰብ ተሳነው

ሙቀቱ ነው መሰለኝ
እንግዲያውስ ይሄውልህ ። ጽምዶ ጥማድ፣ መጠመድ መታሰር በሚለው ተስማምተናል ። ገመድ የሚለው ቃልም ከጸመድ ጋር አንድ ነው ። ገመደ ፣ ጸመደ (እኛ ጣጣ እንለዋለን) ፣ ጠመጠመ ማለት ነው። ደሞም ጸመድ ዘመድ ከሚለው ቃል አንድ ነው ። ዝመድ በጉራጌኛ ሳብ ፣ ጎትት ማለት ነው ። እሱን አምጥቼ ነው ዘመድ ሆኖ ይስባል ያልኩት ። እንደምታውቀው መዛመድ መተሳሰር ፣መሳሳብ ማለት ነው። የኢትዮፒክ ቋንቋን ላወቃቸው እጹብ ድንቅ ናቸው ። ይሀው ከግዕዙ ወደ ትግርኛው አማርኛው እና ጉራጌኛው እንደ ውሃ ይፈሳል ። ወጣጣ መግመድ መጽመድ ማለት ሲሆን በአማርኛ መከራ ጣጣ ስንል የተሳሰረ፣ ጥምጥም አስቸጋሪ ነገር ማለታችን ነው ። እንደ ኢትዮጵያ ቋንቋዎች በሜታፎር የጠገበ ልሳን ያለ አይመስለኝ። ሁለት ሃረጎች አንድ ላይ ሲጠማጠሙ፣ ሁለት በሬዎች በቀምበር አንድ ላይ ሲጠመዱ ፣ ሁለት ሙሽሮች በቃል ኪዳን አንድ ላይ ሲተሳሰሩ ሶስቱም በአንድ ሜታፎር ተገልጸዋል! ኬይር!
Re: eden: እስቲ ይቺን ቀጭን ቅኔ ፍታት?
Posted: 18 Jun 2025, 21:59
by Naga Tuma
Horus wrote: ↑18 Jun 2025, 20:24
የኢትዮፒክ ቋንቋን ላወቃቸው እጹብ ድንቅ ናቸው ። ይሀው ከግዕዙ ወደ ትግርኛው አማርኛው እና ጉራጌኛው እንደ ውሃ ይፈሳል ።
Often times, you assert and expect us to accept all that you assert.
We are in a new era about studying the origin of languages as well as studying the origin of Fidel or Ethiopia’s alphabet.
You excel in explaining about the latter.
I think you miss a lot about the depth of the former.
የፊደል አጀማመር ከቁስ ጋር የተያያዘ ነዉ ብለህ ነበር።
የቃላት አጀማመርም ተመሳሳይነት ያለዉ ይመስላል።
ለምሳሌ ቆንቆ የሚታይ እና የሚዳሰስ ነዉ። ቋንቋ ሲባል ጽንሰ ሀሳብ ይሆናል።
ገመድ መነሻዉ የሆነ ቁስ ምን እንደሆነ ታዉቃለህ?
ስለ ጋማ ታሪክስ ምን ያህል ኣጥንተሃል?
በኦሮምኛ ጨመዴ ማለት ለማረስ የተዘጋጀዉን ሙሉ ነዉ። ሁለት በሬዎች በቀንበር ዉስጥ ታስረዉ፣ ግንድ ላይ የተገጠመ ማረሻ ተደርጎ፣ ሁሉም ተገጣጥመዉ ነዉ። ጨመዲ ቆት ይባላል። ቆቶ ሌላ ቁስ ነዉ።
ጨመዴ ከተባለ ለማረስ ተዘጋጀ ማለት ነዉ። የኣርሶ ኣደር ልጅ ስለ ሆንኩኝ፣ ብዙ ግዜ ኣርሼ ስለማዉቅ ቃሉ በጣም ግልጽ ነዉ።
Re: eden: እስቲ ይቺን ቀጭን ቅኔ ፍታት?
Posted: 19 Jun 2025, 07:44

Thanks.