Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
DefendTheTruth
Senior Member
Posts: 12431
Joined: 08 Mar 2014, 16:32

የዘፈን ምርጫ ለአክሱምዒዛና

Post by DefendTheTruth » 12 Jun 2025, 17:27

ሃቲ ኬኛ ቶኮ ማልቱ አዳን ኑ ባሴ፣ ወል ጂባ ዲሲቲ ኮቱ ወል ጎርፈና
ዋቃ ሞ ነሙማ ከን ሴራ ጀልሴ፣ ሃቲ ኬኛ ማልቱ አዳን ኑ ባሴ

እግዚያብሔር ይሁን ወይስ ሰዉ ማነዉ ሕጉን ያጠመመዉ
እናታችን አንድ ናት፣ ምንድነዉ የለያየን፣ ጥላቻን አስቀርተን ና እንመካከር

listen to this song and watch the video I came across today which shows how Field Marshal Berhanu Jula is greeting his own long time comrade in the Army Lt. General Tsedqan Gebretensae, after that long and devastating war between the brotherly people of Ethiopia.

There was some madness, and that madness didn't separate the children of one mother, Ethiopia!

ፃድቃን፣ ዎክ ስለከረምክበት፣ ችግር የለዉም ብዬ ነዉ!

These words will be recorded in the history book for generations to come, which was used after the immediate aftermaths of that war.

Axumezana
Senior Member
Posts: 17357
Joined: 27 Jan 2020, 23:15

Re: የዘፈን ምርጫ ለአክሱምዒዛና

Post by Axumezana » 12 Jun 2025, 23:23

DefendThe Truth ,

When hundreds of thousands displaced people are crying in Tigray unable to return home after almost five years & when hundreds of thousands of Tigrayans were killed ( still dying) due to the genocide committed in Tigray but no justice so far, those songs are like putting salt in the wounded heart of Axumezana. Abiy decided not to reconcile with Tigray & I have decided to oppose him both spiritually & in this physical world.

Meleket
Member
Posts: 4572
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: የዘፈን ምርጫ ለአክሱምዒዛና

Post by Meleket » 13 Jun 2025, 04:03

የወያኔ ትግራይ ካድሬዎች “ጀኖሳይድ ጀኖሳይድ” ብለው ሲያላዝኑ ያስቃሉ። ኣሁን ደግሞ “ጽምዶ ጽምዶ” እያሉ ሊያደነቁሩንም ይሻሉ። የ”ጽምዶ” ጥቅም ኣሁን ኣቅማችሁ ሲጓደል ነው ወይ ፍንትው ብሎ ዬታያችሁ? ብንላቸው መልሳቸው ምንድን ነው።

እኛ ኤርትራዉያን የመሃልና የመስመር ዳኞች ከ “ጽምዶ” ጠብ ዬለንም፡ ከኢትዮጵያዉያን ጋር የሚደረግ እውነተኛ ጽምዶ፡ ለፊዚካል ዲማርኬሽን ትግባሬ ቀዳሚነትን ካልሰጠ፡ እንደ የሳውዲ አረቢያዉ ጽምዶ መካኝ ጽምዶ ነው እያልን ያለነው፡ በኤርትራዊ ጭዋነት ኩራትና ትህትና ጭምር።

ጐበዝ እውነት እንነጋገር ከተባለ፡ እየተባለ እንዳለው “ጀኖሳይድ” ትግራይ ውስጥ ኣጋጥሞ ከሆነ ያሳዝናል። የ"ጀኖሳይዱ" ተጠያቂዎች ደግሞ፡ ጦርነት ኣያዋጣችሁም ብለው ከጦርነቱ በፊት የሕወሓትን መሪዎች የመከሩት “የኤርትራ መንግስት” እና የሃይማኖት ኣባቶችን እንዲሁም እነ ሬድዋንን ሳይቀር ወደ ትግራይ በመላክ፡ ሕወሓቶች ሁሉንም ነገር በሰላም እንዲከናወን ይሁንታቸውን እንዲሰጡ የተማጠኑት የኢትዮጵያ ፌደራል መንግስት ኣካላት ኣይደሉም። ይልቅስ “የጀኖሳይድ” ተጠያቂ ጦርነት ጫሪዋ፡ ወደ ኤርትራ ሚሳይል ተኳሿ፡ ሕወሓት ነች፡ ከሕወሓትም ውስጥ ያኔ “የፖለቲካና የወታደራዊ” ጉዳዮችን ይመሩ የነበሩት፡ ኣሁን ደግሞ “ጽምዶ ጽምዶ ሰላም ሰላም ስምረት ስምረት” መጫወት የወሰኑት፡ የተወሰኑ የሕወሓት ኣካላት ብቻና ብቻ ናቸው[4 ሚልየን ነጥቦች]

Axumezana wrote:
12 Jun 2025, 23:23
DefendThe Truth ,

When hundreds of thousands displaced people are crying in Tigray unable to return home after almost five years & when hundreds of thousands of Tigrayans were killed ( still dying) due to the genocide committed in Tigray but no justice so far, those songs are like putting salt in the wounded heart of Axumezana. Abiy decided not to reconcile with Tigray & I have decided to oppose him both spiritually & in this physical world.
Last edited by Meleket on 13 Jun 2025, 05:45, edited 1 time in total.

DefendTheTruth
Senior Member
Posts: 12431
Joined: 08 Mar 2014, 16:32

Re: የዘፈን ምርጫ ለአክሱምዒዛና

Post by DefendTheTruth » 13 Jun 2025, 05:43

መለከት፣ እግዚያብሔር ይስጥህ፣ እዉነቱን ስለተናገርክ፣ እንደምረደህ ከሆነ እያልክ ያለሀዉ፣ እዉነትን እየደበቁ ፍትህን መፈለግ አይቻልም፣ ነዉ አይደለም?
ይህን ነገር ብዙ ጊዜ ብያለሁ። ፍትህን መፈለግ ጥሩ ነገር ነዉ፣ እዉነትን መደበቅ ግን አይቻልም፣ እዉነትን ተንተርሶ ነዉና ፍትህ የምመጠዉ፣ በእኔ አረዳድ።

እኛ ከትግራይ ዉጪ የለነዉ ኢትዮጵያኖች የትግራይ እናቶችን ና ሌሎቹንም እምባ ምንም ነገር የምመስለን እንደልሆነ አድርጎ ለመሳል መሄድ፣ ጥሩ ጉዳይ አይደለም። ፍትህ ከተፈለገ፣ ከልብ!

ትንሽ ምክር ለወንድም አክሱምዒዛና፤ አብይን ተቀወመዉ፣ ግን ምክንያታዊ ሁን ነዉ፣ ለራስህ ስትል የምል ይሆናል።

Meleket
Member
Posts: 4572
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: የዘፈን ምርጫ ለአክሱምዒዛና

Post by Meleket » 13 Jun 2025, 08:29

ለምርቃቱ “ኣሜን” ብለናል ወዳጃችን DefendTheTruth!

ኣዎን "እውነትን ደብቆ ፍትህን መሻት"፡ በሌላ ኣማርኛ “ኢትዮጵያዊ ተሁኖ ቀይባህርን እንደመሻት ይቆጠራል” ነው እያልን ያለነው፡ እኛ ኤርትራዉያን የመሃልና የመስመር ዳኞች፡ በተለመደው ኤርትራዊ ጭዋነት ኩራትና ትህትና ጭምር።

ይህም ማለት ለኣብነት፡ “በብልጽግና በኩል ኣሰብን መሻት ጥሩ ነገር ነው። አሰብ የኤርትራ በዅር የመሆኗን እውነትነት ግን በፍጹም በምንም ተኣምር መደበቅና መካድ ኣይቻልም።” የወደብ ተጠቃሚነትን ለማቀላጠፍ፡ ብልጽግና በቁንጮው በዶ/ር ኣብዪ ኣሕመድ ዓሊ ኣፍ፡ በፓርላማ ስብሰባ መካከል፡ ተቀብየዋለው እተገብረዋለውም ያለውን የአልጀርስ ውልና የሄግ ብያኔ ሙሉ በሙሉ በመተግበር፡ ለኢትዮ ኤርትራ የድንበር ብይን ትግባሬ መትጋት ይገባዋል። ለዚህ እውነት የማይተጋ የብልጽግና ኣመራር ሆነ ኣባል፡ ጠቅላይ ሚኒስትርም ይሁን መከላከያ ሚኒስትር ወዘተ፡ ‘እምነቱ’ ፕሮቴስታንት ይሁን ካቶሊክ፡ ኦርቶዶክስ ይሁን እስላም፡ ኵነኔን የመረጠ ዘፀአት 20፡17 ላይ ቍልጭ ብሎ የተጻፈ የእግዚኣብሔር ትእዛዝና ቁርዓን ላይ ትልቅ ሓጢኣት ከተባሉት መካለል አንዱን የጣሰ፡ የቆሪጥ ውርንጭላ ብቻ ነው ብንል ማነው “ውሸት” ለማለት ዬሚደፍር፡ በበላበት ዬሚጮህ ካድሬ ካልሆነ በስተቀር ነው እያልን ያለነው DefendTheTruth ወዳጃችን ።

DefendTheTruth wrote:
13 Jun 2025, 05:43

ኣዅሱመጫላ ሆኑ ጠቅላይ ኣብዪ፡ ብልጽግና ሆኑ ስምረት፡ ኣብን ሆኑ ሕወሓት ወዘተ ኢትዮጵያዉያን በሙሉ፡ በቅንነትና በሰላማዊ መንገድ “የሄግ ብያኔን መሬት ላይ ወርደው ችካሎች በማድረግ የአልጀርስን ውል እልባት ላይ እንዲያውሉ” ይመከራሉ፡ ከዚያ በኋላም ኤርትራዉያን ወደቦቻችንን ለኢትዮጵያዉያን ወንድሞቻችንና እህቶቻችን በርትዓዊና ስማዊ ዋጋ ክፍት በማድረግ፡ የቀጠናችን ህዝቦች ባጠቃላይ በጋራ እጅለእጅ ተያይዘው በብልጽግና ጎደና እንዲራመዱ የበኩላችንን ጥረት እንደምናደርግ ቃል እንገባለን። :mrgreen:

DefendTheTruth
Senior Member
Posts: 12431
Joined: 08 Mar 2014, 16:32

Re: የዘፈን ምርጫ ለአክሱምዒዛና

Post by DefendTheTruth » 13 Jun 2025, 08:41

የኤርትሪያኖች በሽታ፣ ሁላቸዉም በምባል ደረጀ፥

"የእኔ የእኔ ነዉ፣ የአንተ ግን የእኛ ነዉ" በምል ከመጣን ያለፈ ራስ ወዳድነት ላይ መቸከር።

የሌላዉን ጉሮሮ ዘግቶ ፍትህ እጠብቃለሁ ማለት፣ ከ አክሱምዕዛና የባሳ ፍትህን ማዛባት ነዉ። ይህን ሐቅ በጊዜ መረዳት ለራስ ይጠቅማል፤ በእኔ አረዳድ!
Meleket wrote:
13 Jun 2025, 08:29

Post by Meleket » 13 Jun 2025, 09:31

ወዳጃችን DefendTheTruth ኤርትራዉያን ኣንድ ብሂል ኣለን “የራሳችንን ለማንም ኣንሰጥም፡ የሌላ ደግሞ ኣንሻም።” . . . “ቀይባሕር የኛ ነው ኣባይ ግድብ ደግሞ የናንተ ነው!” እያልን ያለነው። “ቀይባህር ጉረሮ፡ ኣባይ ግድብ ደግሞ መቀመጫ ቂ* ነው” የሚል ኣባባል የደርጎችና የተራ የጦርነት ጥቅመኛ (ጦ.ጥ.) ሆድ ኣደር ተራ ካድሬዎች ኣባባል ነው።

ኢትዮጵያዉያን 120 ሚልየን ጉሮሮ እንዳላችሁ እናውቃለን፡ ለሟ ሃገረ ኢትዮጵያም 120 ቢልየን ጉረሮዎችን ሊያስተናግድ የሚችል አምላክ የቸራት ጸጋ እንዳለም እናውቃለን። ኣምላክን ስለተቸራችሁ ጸጋ ኣለማመስገን ሌላ ምንም ሊባል ኣይችልም “የቆሪጥ ባለሟልነት” ካልተባለ በስተቀር፡ በኛ በኤርትራዉያን የመሃልና የመስመር ዳኞች ነጻ ኣተያይ!

DefendTheTruth wrote:
13 Jun 2025, 08:41
የኤርትሪያኖች በሽታ፣ ሁላቸዉም በምባል ደረጀ፥

"የእኔ የእኔ ነዉ፣ የአንተ ግን የእኛ ነዉ" በምል ከመጣን ያለፈ ራስ ወዳድነት ላይ መቸከር።

የሌላዉን ጉሮሮ ዘግቶ ፍትህ እጠብቃለሁ ማለት፣ ከ አክሱምዕዛና የባሳ ፍትህን ማዛባት ነዉ። ይህን ሐቅ በጊዜ መረዳት ለራስ ይጠቅማል፤ በእኔ አረዳድ!
Meleket wrote:
13 Jun 2025, 08:29
ለምርቃቱ “ኣሜን” ብለናል ወዳጃችን DefendTheTruth!

ኣዎን "እውነትን ደብቆ ፍትህን መሻት"፡ በሌላ ኣማርኛ “ኢትዮጵያዊ ተሁኖ ቀይባህርን እንደመሻት ይቆጠራል” ነው እያልን ያለነው፡ እኛ ኤርትራዉያን የመሃልና የመስመር ዳኞች፡ በተለመደው ኤርትራዊ ጭዋነት ኩራትና ትህትና ጭምር።

ይህም ማለት ለኣብነት፡ “በብልጽግና በኩል ኣሰብን መሻት ጥሩ ነገር ነው። አሰብ የኤርትራ በዅር የመሆኗን እውነትነት ግን በፍጹም በምንም ተኣምር መደበቅና መካድ ኣይቻልም።” የወደብ ተጠቃሚነትን ለማቀላጠፍ፡ ብልጽግና በቁንጮው በዶ/ር ኣብዪ ኣሕመድ ዓሊ ኣፍ፡ በፓርላማ ስብሰባ መካከል፡ ተቀብየዋለው እተገብረዋለውም ያለውን የአልጀርስ ውልና የሄግ ብያኔ ሙሉ በሙሉ በመተግበር፡ ለኢትዮ ኤርትራ የድንበር ብይን ትግባሬ መትጋት ይገባዋል። ለዚህ እውነት የማይተጋ የብልጽግና ኣመራር ሆነ ኣባል፡ ጠቅላይ ሚኒስትርም ይሁን መከላከያ ሚኒስትር ወዘተ፡ ‘እምነቱ’ ፕሮቴስታንት ይሁን ካቶሊክ፡ ኦርቶዶክስ ይሁን እስላም፡ ኵነኔን የመረጠ ዘፀአት 20፡17 ላይ ቍልጭ ብሎ የተጻፈ የእግዚኣብሔር ትእዛዝና ቁርዓን ላይ ትልቅ ሓጢኣት ከተባሉት መካለል አንዱን የጣሰ፡ የቆሪጥ ውርንጭላ ብቻ ነው ብንል ማነው “ውሸት” ለማለት ዬሚደፍር፡ በበላበት ዬሚጮህ ካድሬ ካልሆነ በስተቀር ነው እያልን ያለነው DefendTheTruth ወዳጃችን ።

DefendTheTruth wrote:
13 Jun 2025, 05:43
መለከት፣ እግዚያብሔር ይስጥህ፣ እዉነቱን ስለተናገርክ፣ እንደምረደህ ከሆነ እያልክ ያለሀዉ፣ እዉነትን እየደበቁ ፍትህን መፈለግ አይቻልም፣ ነዉ አይደለም?
ይህን ነገር ብዙ ጊዜ ብያለሁ። ፍትህን መፈለግ ጥሩ ነገር ነዉ፣ እዉነትን መደበቅ ግን አይቻልም፣ እዉነትን ተንተርሶ ነዉና ፍትህ የምመጠዉ፣ በእኔ አረዳድ።

እኛ ከትግራይ ዉጪ የለነዉ ኢትዮጵያኖች የትግራይ እናቶችን ና ሌሎቹንም እምባ ምንም ነገር የምመስለን እንደልሆነ አድርጎ ለመሳል መሄድ፣ ጥሩ ጉዳይ አይደለም። ፍትህ ከተፈለገ፣ ከልብ!

ትንሽ ምክር ለወንድም አክሱምዒዛና፤ አብይን ተቀወመዉ፣ ግን ምክንያታዊ ሁን ነዉ፣ ለራስህ ስትል የምል ይሆናል።
ኣዅሱመጫላ ሆኑ ጠቅላይ ኣብዪ፡ ብልጽግና ሆኑ ስምረት፡ ኣብን ሆኑ ሕወሓት ወዘተ ኢትዮጵያዉያን በሙሉ፡ በቅንነትና በሰላማዊ መንገድ “የሄግ ብያኔን መሬት ላይ ወርደው ችካሎች በማድረግ የአልጀርስን ውል እልባት ላይ እንዲያውሉ” ይመከራሉ፡ ከዚያ በኋላም ኤርትራዉያን ወደቦቻችንን ለኢትዮጵያዉያን ወንድሞቻችንና እህቶቻችን በርትዓዊና ስማዊ ዋጋ ክፍት በማድረግ፡ የቀጠናችን ህዝቦች ባጠቃላይ በጋራ እጅለእጅ ተያይዘው በብልጽግና ጎደና እንዲራመዱ የበኩላችንን ጥረት እንደምናደርግ ቃል እንገባለን። :mrgreen:

Selam/
Senior Member
Posts: 15409
Joined: 04 Aug 2018, 13:15

Re: የዘፈን ምርጫ ለአክሱምዒዛና

Post by Selam/ » 13 Jun 2025, 09:37

እጨጌ መጎጡ ፣ በእማሆይ ተቀጡ
እዚህ እዚያ እያሉ ፣ ስለቀላወጡ
በሾለው አፋቸው ፣ ህዝብ ስላናውጡ

የወያኔዎች አይምሮ በጣም ይገርመኛል፣ ‘ጂኖሳይድ ጂኖሳይድ’ ሲሉ ከርመው፣ አቶ ዓብዮት ፍርፋሪ ሲያሳያቸው ‘አይ በቃ አሁን ይቅር ተባብለናል፣ ሰላምም ወርዷልና ፒፒና ትህነግ ተባብረው አማራን ይደፍቃሉ’ ባሉ ዓመት ሳይሞላቸው ተመልሰው ቅራኔ ውስጥ ገቡ። ‘ይቅር ብያለሁና ከዓብዮት ጋር ወደፊት’ ብሎ የነበረው አይተ ዓይጠ መጎጡሙ፣ የጄኖሳይድ ካርዱን መልሶ መዘዘ። በህገ-አራዊት ካልሆነ በስተቀር ይቅርታ የተደረገ ጉዳይ አይቀለበስም።

ደግሞም የአንድ ወገን ጄኖሳይድ ላይ ይቅር ተባብለህ፣ የሌላው ኢትዮጵያ ወገንህ ላይ የተፈፀመውን ጄኖሳይድ ጆሮ ዳባ ልበስ ማለት የሚያሳየው፣ ይቅርታ ሰጪውም ይቅርታ ተቀባዩም አጭበርባሬ ሌባዎች መሆናቸውን ነው። በአጠቃላይ በሃገሪቷ ስምምነት እስካልሰፈነ ድረስና የሁሉም ሰዎች የመናገር፣ የመሰባሰብ፣ በነፃነት የመኖር መብት ካልተከበረ፣ አጥፊዎች በህግ እስካልተቀጡ ድረስ፣ ሁለት አብሮ አደግ ወጀለኞች ብቻ በድብቅ በሚፈራረሙት የወረት ስምምነት ምንም የሚያመጣው ለውጥ አይኖርም።

ባለ ኮሪዶሩ ካድሬ ዲዲቲም ሲያጭበረብር፣ ‘የትግራይ እናቶች እንባ ያሳዝነኛል’ አለ። Really? የመላው ኢትዮጵያን እናቶች እንባ እስከ አሁን እየፈሰሰ እኮ ነው — ስለሚራቡ፣ ስለሚፈናቀሉ፣ ልጆቻቸው ወጥተው በየሜዳው ስለሚቀሩ፣ ስለሚሳደዱ፣ ስለሚሰደዱና ስለሚታሰሩባቸው። ለኮሪዶር በየቀኑ ከምታንቋልጥ፣ ለፍትህ ማልቀስ በተገባህ፣ ወንጀለኞቹ እንዲቀጡ እንደኔ መጮህ በተገባህ። ኤርትራውያኖች ‘እኔ እኔ ብቻ ይላሉ’ ብሎ የከሰሰውን ምላስህን በመስተዋት እየው፣ ቀንጥበህ ለመጣል ያስመኝሃል።

የወደብና የድንበር ጥያቄ ሊፈታ ያልቻለው ሁለቱም መሪዎች ዕርጉሞች ስለሆኑ ነው። የሻቦው መሪ ሁሌም ነዳጅ ሳይሞላ በዜሮ ማርሽ መንዳት ነው የሚፈልገው። አቶ ዓብዮት ኢትዮጵያን ማተራመሱን እስካላቆመ ድረስ አይደለም በጉልበትና በፉከራ፣ እየተንፏቀቀ ቢለምን እንኳን ወደብ አይገኝም። ለዚህ ምስክር የሚሆነው ደግሞ፣ ከየትኛውም ጎረቤት ሃገር ጋር ስምምነት መፍጠር አለመቻሉ ነው።

በሃገር ውስጥ ሰላም ሳይኖር በተለይ ስለ ዓሰብ ማውራት ጉንጭ ማልፋት ነው። የካድሬ ስራ ደግሞ ይኸው ነው!

Axumezana
Senior Member
Posts: 17357
Joined: 27 Jan 2020, 23:15

Re: የዘፈን ምርጫ ለአክሱምዒዛና

Post by Axumezana » 13 Jun 2025, 14:50

መለከት ራስክን ዳኛ አድርገህ ከሾምክ በኻላ ፍርድ ገምድል የሆነ አስተያየት ትሰጣለህ! ጆኖሳይድ ትግራይ እንደተፈፀመ በጥናት የተደገፈ ውሳኔ ነው። ያላቅምህ ስለገጠምክ ለደረሰብህ ጆኖሳይድ አንተ ተጠያቂ ነህ የሚለው አባባል ትርጉም ሳይገባህ የግራ የማኸል ዳኛ ነኝ እያልክ መመፃደቁ ድንቁርናህን ያረጋግጣል! ራስን መከላከል ሰብኣዊ መብት መሆኑን እንዴት ዘነጋኸው?
። የፅምዶ ዘፈን መጀመርያ የተዘፈነው ከኤርትራ በኩል ስለሆነ ትግረዋዩ ገዢህን ኢሳያስን ጠይቀው። ስለ ዲማርኬሽን ስታስብ የሚከተለውን ካርታ ተመልከት።

[/quote]
[/quote]
Last edited by Axumezana on 13 Jun 2025, 17:28, edited 2 times in total.

DefendTheTruth
Senior Member
Posts: 12431
Joined: 08 Mar 2014, 16:32

Re: የዘፈን ምርጫ ለአክሱምዒዛና

Post by DefendTheTruth » 13 Jun 2025, 15:29

ወንድም መለከት፣

አንድ ነገር ብዬ ይህን ዉይይት ልዝገዉ። የአባይ ወንዝ ና የቀይ ባሕር የተፈጥሮ ፀጋዎች ናቸዉ፣ ሁለቱም ለሰዉ ሕይወት አስፈላጊ ናቸዉ። አንደኛዉ የዉሃ ምንጭ በመሆን ና ሌላኛዉ ደግሞ በተለይ ወደ አለም ገቢያ ለመዉጣት። የአከባቢዉ ሕዝቦች ለዘመናት እነኚህን የተፈጥሮ ፀጋዎች ስጠቀሙ ና የሕይወት ፍላጎታቸዉን ስያሟሉበት ኖሮዋል፣ የወደ ፊቶችም ይኖራሉ። ይህ መሰረታዊ ሐቅ ነዉ፣ ማንም መካድ ወይም መፍረስ አይችልም።

ከእነዚህ ሁለቱ ፀጋዎች አንዱን ብቻ ስለለህ ሌላኛዉ አያስፈልግህም የምባል አይነት ምልከታ ልኖር አይችሉም። ኮት ስለለህ የለሱሪ ገቢያ ወጥተህ ህድ እንደማይባል ሁሉ ማለት ነዉ። የሁለቱ ፀጋዎች አገልግሎቶች የተለያዩ ና ሁለቱም አስፈላጊዎች ስለሆኑ ማለት ነዉ።

ሌላኛዉ መሰረታዊ የሰዉ ልጆች ሕይወት መስታጋብር ደግሞ ያለህን ገቢያ ወስደህ ሽጠህ፣ የሌላህን ገዝትህ ትገባ ና ለኑሮህ የምያስፈልጉትን ታሞላለህ፣ ይህ ማለት ፊታዊ ነዉ፣ ለሰላም መሰረት ነዉ፣ ለእድገት አስፈላጊ ነዉ። ይህን ያዛባ ሰላምን አድፍርሶዋል ማለት ነዉ።

ኢትዮጵያ በአልም ፊት ያለኝን አካፊዬ የሌለኝን ደግሞ ስጡኝ ስትል አይ አሻፈረኝ ያለን ጉጠቱ ኢሳያስ አፈወርቂ የምባል ደንቆሮ ሰዉ ነዉ። የሱ ፍላጎት፣ የኢትዮጵያ ሐብት የጋራችን ነዉ፣ የኤርትሪያ ሐብት ግን የኤርትሪያ ብቻ ነዉ በምል እኩይ ምልከታ ላይ የተመሰረተ ራስ ወዳድነት ነዉ።

ኢትዮጵያ ቀጥሎ የምትችለዉን ማድርግ ነዉ የምጠበቅባት፤ ኦኬ፣ ለህይወቴ አስፈላጊ የሆነን ነገር ሁሉ ለመገኘት ስል የምችለዉን ሁሉ አደርጋለሁ ብላ መጣች፣ ሌላ ምን አማራጭ አላት ነዉ የምትለን? ወደ ባሕር በምንም አይነት ሁኔታ መጠጋት የለባትም የምትሉን በምን አግባብ ነዉ? በምን ምክንያት ነዉ?

የዚህ አለም ሕዝብ ሁሉ የባሕር በር የስፈልገዋል፣ ታዲያ ኢትዮጵያ አይ አያስፈልጋትም የምትሉን በምን አግባብ ነዉ? ምክንያቱስ ምንድ ነዉ? ፍትሕን ማጓዳል ታዲያ ከዚህ በላይ እንዴት ነዉ? ከተፈጥሮ ፀጋ ኢትዮጵያን ለይታችዉ ፍትህን አዛብታችዉ ስታበቁ ደግሞ ኢትዮጵያን እንደ ጥፋተኛ አድርጋችዉ ለመሳል መሞከራችዉ የጥፋት ሁሉ ጥፋት ነዉ።

ኢትዮጵያ የባሕር በር ያስፈልገኛል ብላለች፣ ይህን ጥያቄ ማንም ሰዉ በዚህ አለም ላይ ልያስቆም አይችልም፣ ለማስቆም መሞከር ከተፈጥሮዋዊ ሕግጋት ጋርም ይቃረናል። ይህ ማለት ፍትህን ማጓዳል ነዉ።
ፍትህን አጓድለህ ስታባቀ ደግሞ ተበዳይ መስለህ ለመቅረብ መሞከር ከእግዚያብሔርም ሆነ ከሰዉ ሰራሽ ህግ ጋር መፀረር ነዉ። ሀቁ ይህ ነዉ!

ኢትዮጵያ ፍትህን አለጓደለችም፣ በሰዉም በፈጣሪ ፊትም አሻናፊ ትሆናለች። ጉጠቱ ኢሳያስ አፈወርቂ ና የሱ አጨብጫቢዎች ናቸዉ በአፍረት ና ክሳራ ወደ መጡበት የምመለሱት። ከጠፈጥሮ ና ከሰዉ ሕግጋት ጋር ተፃርሮ በመቆማቸዉ።

ይህን በመዛበትህ ነዉ አቋምህን የስፈተንከዉ፣ ምንም በቃላት ለመሳመር ብትጥር ይህን ሐቅ መደበቅ አትችልም!

ቸር ሁን፣ ወንድም!

Axumezana
Senior Member
Posts: 17357
Joined: 27 Jan 2020, 23:15

Re: የዘፈን ምርጫ ለአክሱምዒዛና

Post by Axumezana » 13 Jun 2025, 17:25

መለከት በማንነት ቀውስ ማእበል ውስጥ የሚናወጥ ሲሆን፥ እውቆ የተኛን መቀስቀስ አይቻልም እንደሚባለው በኢትዮጵያና ኤርትራ ድምበር ማካለል ቅዥት ውስጥ የሚኖር የበግ ለምድ የለበሰ ተኩላ ነው።

Meleket
Member
Posts: 4572
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: የዘፈን ምርጫ ለአክሱምዒዛና

Post by Meleket » 14 Jun 2025, 03:45

Axumezana wrote:
13 Jun 2025, 17:25
መለከት በማንነት ቀውስ ማእበል ውስጥ የሚናወጥ ሲሆን፥ እውቆ የተኛን መቀስቀስ አይቻልም እንደሚባለው በኢትዮጵያና ኤርትራ ድምበር ማካለል ቅዥት ውስጥ የሚኖር የበግ ለምድ የለበሰ ተኩላ ነው።
የተኩላ 'ለምድ' የደረብከው በጉ ወዳጃችን ኣዅሱመጫላ ምልከታህ ግሩም ነው!
Axumezana wrote:
13 Jun 2025, 14:50
መለከት ራስክን ዳኛ አድርገህ ከሾምክ በኻላ ፍርድ ገምድል የሆነ አስተያየት ትሰጣለህ! ጆኖሳይድ ትግራይ እንደተፈፀመ በጥናት የተደገፈ ውሳኔ ነው።
..
"ውሳኔ" ወይስ እውነታ? "ውሳኔ" ወይስ ሓቅ? ወይ "ውሳኔ"!
Axumezana wrote:
13 Jun 2025, 14:50
ያላቅምህ ስለገጠምክ ለደረሰብህ ጆኖሳይድ አንተ ተጠያቂ ነህ የሚለው አባባል ትርጉም ሳይገባህ የግራ የማኸል ዳኛ ነኝ እያልክ መመፃደቁ ድንቁርናህን ያረጋግጣል! ራስን መከላከል ሰብኣዊ መብት መሆኑን እንዴት ዘነጋኸው?
..
"ኣቅምን ኣዉቆ መኖር ጥሩ ነው፡
ታላቅ ችሎታ ነው!”

የተባለው እኮ እንዲህ እንዳያጋጥም ነበር። በል በዓምዱ ርእስ መሰረት እኛም ይህንን የአቶ ኣሕመድ ልጅን ሙዚቃ ጋብዘንሃል። ባልተቤቱ ከትግሬ ሆና እያለ ግን እንዴት ይህን ብርቅ ሙዚቃ ሳትሰሙትና ሳታጣጥሙት ቀራችሁ ጃል!

Axumezana wrote:
13 Jun 2025, 14:50
..ራስን መከላከል ሰብኣዊ መብት መሆኑን እንዴት ዘነጋኸው?
የገዛ ሃገርህን የመከላከያ ሰራዊት ማጥቃት ሰብኣዊ መብት ኣለመሆኑንስ እንዴት ዘነጋኸው? የተኩላ 'ለምድ' የደረብከው በጉ ወዳጃችን Axumezana!

Naga Tuma
Member+
Posts: 6143
Joined: 24 Apr 2007, 00:27

Re: የዘፈን ምርጫ ለአክሱምዒዛና

Post by Naga Tuma » 14 Jun 2025, 15:12

DefendTheTruth wrote:
12 Jun 2025, 17:27
… after that long and devastating war between the brotherly people of Ethiopia.

There was some madness, and that madness didn't separate the children of one mother, Ethiopia!

DefendTheTruth:

I listened to Ali Bira’s song once again and realized for the first time that the first word out of his mouth, ዐመል, is a common word in both ኦሮምኛ and አማርኛ። I am not sure it is different in ትግርኛ።

Does this single word inform about what you now call one mother?

Does it also inform how much Ali Bira was uninformed when he released this song? If he were informed deeply, his domain for his lyrics wouldn’t be limited and disproven by the first word out of his mouth in his song.

Did you get a chance to read a potential answer for his question in the song that I recently posted on this forum?

Here is part of it with one additional line.

ጋራ ኣዴ ጄዸ፣ ደካ ኣዴ ጄዸ
አቺ ኣብ ጄዸ፣ አሲ አባ ጄዸ
ኩን ዉዳሴ ኦለ፣ ሱን ዌድሳ ኦለ
አሲ ሸግዬ ጄዸ፣ አቺ ሸጎዬ ጄዸ
ካን ፈወሴ ጄዸ፣ ካንሞ ፍይሴ ጄዸ

That said, in my view, Hararghe was a kind of a model Ethiopian federal state during the time of Dergue.

When I was in college, students from Hararghe had an outstanding fame of the most friendly of any other place in Ethiopia. I stand to be corrected by anyone who was in college at the time.

I realized later on that people from Hararghe are mostly fluent bilinguals.

For good or bad, three successive Ethiopian leaders was either born or have lived in Hararghe for a while.

It also produced bilingual musicians like Bizunesh Bekele and Hamelmal Abate.

I imagine that these are traits of a model federal state or two that could have been built up if what you called political insanity didn’t visit the children of one mother.

Axumezana
Senior Member
Posts: 17357
Joined: 27 Jan 2020, 23:15

Re: የዘፈን ምርጫ ለአክሱምዒዛና

Post by Axumezana » 14 Jun 2025, 16:58

መለከት ይህችን እስካሁን አይትሃታል ብዬ እጠብቃለሁ። viewtopic.php?f=2&t=363425#p1563384
[/quote]

የትግራይ ህዝብ ራሱን ተከላከለ እንጂ ጦርነት አልጫረም። ሁለት አመት ተዋግቶም የጠላቶቹን ህልም ከንቱ አድርገዋል። ትናንት የተበተነ ዱቄት አድርገነዋል ካሉት ጠላቶቹ ጋር ተደራድሮ አለም አቀፍ ውል አድርገዋል። Game over / ተኾሊፍና ያሉትም ፅምዶ ፅምዶ እንዲዘምሩ አድርጓቸዋል።
Last edited by Axumezana on 14 Jun 2025, 18:10, edited 3 times in total.

Dama
Member
Posts: 4604
Joined: 22 Jun 2024, 21:05

Re: የዘፈን ምርጫ ለአክሱምዒዛና

Post by Dama » 14 Jun 2025, 17:03

DefendTheTruth wrote:
12 Jun 2025, 17:27
ሃቲ ኬኛ ቶኮ ማልቱ አዳን ኑ ባሴ፣ ወል ጂባ ዲሲቲ ኮቱ ወል ጎርፈና
ዋቃ ሞ ነሙማ ከን ሴራ ጀልሴ፣ ሃቲ ኬኛ ማልቱ አዳን ኑ ባሴ

እግዚያብሔር ይሁን ወይስ ሰዉ ማነዉ ሕጉን ያጠመመዉ
እናታችን አንድ ናት፣ ምንድነዉ የለያየን፣ ጥላቻን አስቀርተን ና እንመካከር

listen to this song and watch the video I came across today which shows how Field Marshal Berhanu Jula is greeting his own long time comrade in the Army Lt. General Tsedqan Gebretensae, after that long and devastating war between the brotherly people of Ethiopia.

There was some madness, and that madness didn't separate the children of one mother, Ethiopia!

ፃድቃን፣ ዎክ ስለከረምክበት፣ ችግር የለዉም ብዬ ነዉ!

These words will be recorded in the history book for generations to come, which was used after the immediate aftermaths of that war.
This ebbet Galla copypastes the US policy of using Hollywood to manipulate and tame diffucult political situations for which it will likely fail in normal diplomatic discourse.

Meleket
Member
Posts: 4572
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: የዘፈን ምርጫ ለአክሱምዒዛና

Post by Meleket » 16 Jun 2025, 05:36

የወዳጃችን ኣዅሱመጫላ እና የሕወሓት ‘ፈላስፎች’ ኣመክንዮ ብዙ ግዜ የተንጋደደ መሆኑን እስቲ በምሳሌ እናስረዳ!

ታዬ ደንደኣ ከነ ኣብዪ ኣስተሳሰብ ጋር ስለተጣላ አሁን ላይ የሚሰጠውን ገለጻ እመኑት” ትትሉናላችሁ። በሌላ በኩል ደግሞ “ጌታቸው ረዳ ከነ ደብረጽዮን ኣስተሳሰብ ጋር ስለተጣላ አሁን ላይ የሚሰጠውን ገለጻ ኣትመኑት ትላላችሁ” ገራሚዎች ናችሁ! :mrgreen: እኛኮ ማንን መቼና እንዴት እንደምንሰማ እናውቃለን። ለማንኛውም ወዳጃችን ኣዅሱመጫላ ስለ ጥቆማህ እናመሰግንሃለን፡ እኛ ኤርትራዉያን የመሃልና የመስመር ዳኞች፡ በኤርትራዊ ጭዋነት ኩራትና ትህትና ጭምር።

Axumezana wrote:
14 Jun 2025, 16:58
መለከት ይህችን እስካሁን አይትሃታል ብዬ እጠብቃለሁ። viewtopic.php?f=2&t=363425#p1563384

የትግራይ ህዝብ ራሱን ተከላከለ እንጂ ጦርነት አልጫረም። ሁለት አመት ተዋግቶም የጠላቶቹን ህልም ከንቱ አድርገዋል። ትናንት የተበተነ ዱቄት አድርገነዋል ካሉት ጠላቶቹ ጋር ተደራድሮ አለም አቀፍ ውል አድርገዋል። Game over / ተኾሊፍና ያሉትም ፅምዶ ፅምዶ እንዲዘምሩ አድርጓቸዋል።

Axumezana
Senior Member
Posts: 17357
Joined: 27 Jan 2020, 23:15

Re: የዘፈን ምርጫ ለአክሱምዒዛና

Post by Axumezana » 16 Jun 2025, 05:55

ዳኛ ታየነም ጌቾንም ማመን አይጠበቅበትም ጭብጥ ማግኘት እንጂ አንተ ግን የፌዝ ዳኛ ነህ!

Meleket
Member
Posts: 4572
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: የዘፈን ምርጫ ለአክሱምዒዛና

Post by Meleket » 16 Jun 2025, 09:09

ኣዅሱመጫላ ስለ “ጭብጥ” ማለት ማስረጃ ኣንተም ታወራለህ ለካ።

ለአብነት እዚህ ላይ viewtopic.php?f=2&t=341494 ተራቁጥር 2 ላይ ላስቀመጥከው ሃሳብ እኮ ጭብጥ ወይም ማስረጃ ኣቅርብ ብትባል ምንም እንደማታቀርብ እናውቃለን እኛ ኤርትራዉያን የመሃልና የመስመር ዳኞች!

ስለዚህ ታዬንም ሆነ ጌቾን የሚያወሩትን ያውሩ፡ ከዚህ በፊት ያወሩትም ኣለ፡ እና እኛ ምናደርገው ሁሉንም ሚዛን ላይ ዱቅ ኣድርገን ነው የምንመዝነው ለማለት ያህል ነው። የአንዱ ኣባባል በጭፍን ኣምኖ ያንዱን ኣባባል በጭፍን ማውገዝ ኣይቻልም። ሚዛን ላይ ነው የምናደርገው ለማለት ያህል ነው! ለምሳሌ ያንተን ኣባባል እዚህ ላይ https://mereja.com/forum/viewtopic.php?f=2&t=280152ላቦራቶሪ ውስጥ አስገብተን ፈትሸን ምን ዓይነት ድምዳሜ እንደደረስን ጠንቅቀህ ታውቀዋለህ፡ የትላንት ታሪክ ስለሆነ!

Axumezana wrote:
16 Jun 2025, 05:55
ዳኛ ታየነም ጌቾንም ማመን አይጠበቅበትም ጭብጥ ማግኘት እንጂ አንተ ግን የፌዝ ዳኛ ነህ!
Last edited by Meleket on 17 Jun 2025, 05:46, edited 1 time in total.

Selam/
Senior Member
Posts: 15409
Joined: 04 Aug 2018, 13:15

Re: የዘፈን ምርጫ ለአክሱምዒዛና

Post by Selam/ » 16 Jun 2025, 09:44

እጨጌ ዓይጠ መጎጡ

Axumezana
Senior Member
Posts: 17357
Joined: 27 Jan 2020, 23:15

Re: የዘፈን ምርጫ ለአክሱምዒዛና

Post by Axumezana » 16 Jun 2025, 11:55

መለከት ዞር ብሎብሃል! የት አገር ነው ዳኛ ያለ ጭብጥ የሚዳኘው? የበግ ለምድህን አውልቀህ ማነትህን ግልጽ አድርጓል!9

Post Reply