Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Za-Ilmaknun
Member
Posts: 4380
Joined: 15 Jun 2018, 17:40

BBC-ብርጋዴር ጄነራል ገብረ እግዚአብሄር በየነ (ወዲ አንጥሩ) ከሌሎች የትግራይ ሠራዊት አመራሮች ጋር ህወሓትን የመጣል ዓላማ እንዳላቸው ሲያብራሩ

Post by Za-Ilmaknun » 10 Jun 2025, 12:16

ከትግራይ ኃይሎች በመለየት ከአፋር ክልል ጋር በሚዋሰን አካባቢ የራሳቸውን ሠራዊት እየገነቡ መሆናቸውን የሚናገሩት ብርጋዴር ጄነራል ገብረ እግዚአብሄር በየነ (ወዲ አንጥሩ) "ከፓርቲ [ህወሓት] ነጻ የሆነ ኃይል" ለመፍጠር ወደ ነጻ መሬት መውረዳቸውን ተናገሩ። ጄነራሉ ከቢቢሲ ትግርኛ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ "አዲስ ነገር ለመፍጠር" ወደ በረሃ መውደረዳቸውን ሲያብራሩ "ከፓርቲ ነጻ የሆነ ኃይል ለመፍጠር፣. . . ፓርቲ የማያዝዘው ሠራዊት ለመፍጠር " እየተንቀሳቀሱ መሆኑን ተናግረዋል።

በአፋር እና በትግራይ ክልሎች ውስጥ አራት ክፍለ ጦር ያለው ሠራዊት ማደራጀታቸውን የሚናገሩት ጄነራል ገብረ እግዚአብሄር በየነ፣ ከትግራይ ሠራዊት አመራሮች ጋር የተለያዩት ከጥር 15/20017 ዓ.ም. ጀምሮ መሆኑን ይናገራሉ።

የትግራይ ሠራዊት ከፍተኛ አመራሮች ጥር 15 ተሰብስበው በአቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራውን ጊዜያዊ አስተዳደር ሲያወግዙ፣ ተቃውመው ስብሰባውን ረግጠው ከወጡ አመራሮች መካከል አንዱ ጄነራል ገብረ እግዚአብሄር በየነ ናቸው።

"የትግራይ ሕዝብ በነጻነት እና ወገንተኝነት በሌለበት መንገድ የመረጠውን አካል ነው የምናገለግለው" ብለዋል።

ከሌሎች የትግራይ ሠራዊት አመራሮች ጋር ያላቸው ልዩነት በንግግር ለመፍታት ሞክረው "እምቢ" እንደተባሉ የሚናገሩት ጄነራሉ፤ የተወሰዱ እርምጃዎችንም መቃወማቸውን ገልጸዋል።

https://www.bbc.com/amharic/articles/c8d136gld16o