የኢትዮ ጂቡቲ ባቡር ትራንስፖርት ኩባንያ ዓለም አቀፍ ስምምነቶችን እንዲያከብር
የጂቡቲ መንግሥት ጠየቀ
ኩባንያው የኢትዮጵያና የጂቡቲ የጋራ ንብረት በመሆኑ ነፃ፣ ግልጽና ከአድልኦ የፀዳ የጭነት አገልግሎት እንዲሰጥ ይጠበቅበታል ተብሏል፡፡

የኢትዮ ጂቡቲ ባቡር ትራንስፖርት ኩባንያ ዓለም አቀፍ ስምምነቶችን እንዲያከብር ተጠየቀ፡፡ የጂቡቲ ወደብ ባለሥልጣን እንዳስታወቀው የኢትዮ ጂቡቲ ምድር ባቡር ትራንስፖርት አክስዮን ማኅበር የባቡር መሠረተ ልማትንና የአገልግሎት አሰጣጥ ሒደትን እንዲለይ ጠይቋል፡፡
ሪፖርተር የተመለከተው የጂቡቲ ወደብና ነፃ ዞን ባለሥልጣን ለኢትዮ ጂቡቲ ምድር ባቡር ትራንስፖርት አክሲዮን ማኅበር በጻፈው ደብዳቤ፣ ኩባንያው በጭነት ማስተላላፍና በጉምሩክ ክሊራንስ ላይ እያደረገው ያለው እንቅስቃሴ እንዳሳሰበው ገልጿል፡፡
የጭነት አስተላላፊ ድርጅቶችና የጉምሩክ ደላሎች አስመጪዎችንና ላኪዎችን ወክለው ጉዳይ እንዲያስፈጽሙ የሚፈቅድ በመሆኑ፣ የኢትዮ ጂቡቲ ባቡር ትራንስፖርት አክሲዮን ማኅበር ድርጊት እነዚህን ስምምነቶች እንዲከተልም ጠይቋል፡፡
ከአንድ ወር በፊት የጭነት አስተላላፊዎች ከኩባንያው ጋር ውል እንዲገቡ የጠየቃችሁት ጉዳይ ከምን ደረሰ በሚል ለቀረበላቸው ጥያቄ ዳይሬክተሩ ምላሽ ከመስጠት ተቆጥበዋል፡፡
የጭነት አስተላላፊ ድርጅቶች ከአንድ ወር በፊት የኢትዮ ጂቡቲ ባቡር ትራንስፖርት ኩባንያ ጭነቶችን በሙሉ ራሱ ለመቆጣጠር እየሞከረ ነው ማለታቸው ይታወሳል፡፡ እነዚህ የግል ሎጂስቲክስ ድርጅቶች የኢትዮ ጂቡቲ ባቡር ትራንስፖርት ኩባንያ እንቅስቃሴ በኢትዮጵያ
ያሉ የግል ሎጂስቲክስ ድርጅቶችን ከገበያ የሚያስወጣ፣ በመንግሥትና በሕዝብ ገንዘብ የተገነባ የባቡር መሠረተ ልማትን ተቆጣጥሮ የጭነት አገልግሎቶችን ብቻውን ለመቆጣጠር በጥረት ላይ መሆኑን አስታውቀው ነበር፡፡