እንደማስታዉሰዉ፣ ኢሳት ና ጭዱን አንድ ላይ አጣምሮ፣ የኢትዮጵያ አንድነት ሀይሎች ነን፣ ፀረ አንድነት ነን ባዮችን ና አገር ገንጣይ ነን ብሎ ትግል እያካጅሄድን ነን የምሉትን ና በአንድ ላይ ምንም አይነት የጋራ የሆነን አቋም የሌላቸዉን ሁሉንም ና በሁሉም ነገር ምንም አይነት ተመሳሳይነት የሌላቸዉን አንድ ላይ አምጥቶ ኢትዮጵያ ላይ ከዘመታችዉ እኔ አግዛችዋለሁ በማለት ኢሳያስ ሁሉን አይነት ተቋዋሚ ነን ባዮችን አደራጅቶ ልክቦናል። እንደማስታዉሰዉ ና በዚያኔ ፓርላማ ላይ የአደረገዉ ንግግር ትዝ ይለኛል።
መለስ አሁን ላይ በአጠገባችን በይኖርም ኢሳያስ አሁንም አለ፣ ስራዉ አሁንም ህያዉ ሆኖ ቀጥሎዋል። የትናንትናዉን የኢንተርኔት ስብሰባ ያየ ሰዉ ይህን ሐቅ መካድ አይችልም። የኢሳያስ አፈወርቂ ፊርማ በትልቁ ተቀምጦበታል።
ባንዳ ምን ጊዜም ይኖራል፣ አገር ወደድ ደግሞ ምን ጊዜም በአሸናፊነት ድል ነስቶዋቸዉ ይነሳል፣ አዲስ ነገር የለም!